Home » Archives by category » አማርኛ ዜና (Page 2)

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

 

በአሁኑ ጊዜ አቶ አንዱዓለም አራጌ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ ይገኛል፡፡ ከአስተማማኝ ምንጮች በተገኘ መረጃ መሠረት የካቲት 7 ቀን 2ዐዐ4 ዓም ከቀኑ 8፡ዐዐ ሰዓት ገደማ ለህይወቱ የሚያሰጋ ከባድ ድብደባ ተፈጽሞበታል፡፡ ድብደባውን የፈፀመው አቶ አንዱዓለም በታሰረበት ክፍል ውስጥ የሚገኝ ኢባስ አስፋው የሚባል ፍርደኛ ነው፡፡ ይህ ሰው አቶ አንዱዓለም በክፍሉ ውስጥ የግል ጉዳዩን በማከናወን ላይ በነበረበት ጊዜ በአልታወቀ ምክንያት መጀመሪያ  በእርግጫ መትቶ ከጣለው በኋላ በወደቀበት ላይም አሁንም ጫማ በአደረገ እግሩ በስሚንቶ ወለሉ ላይ ደጋግሞ በመርገጥ ነፍሱን እስከመሳት የሚያደርስ ድብደባ እንደፈፀመበት ተገልፆልናል፡፡ ህይወቱ የተረፈውም በክፍሉ ውስጥ በነበሩ ታራሚዎች ገላጋይነት መሆኑም ታውቋል፡፡

ድብደባውን የፈፀመው ግለሰብ ቀደም ሲል በነፍስ ግድያ ወንጀል ተከስሶ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት የነበረ ሲሆን በኋላ ግን ይኸው ፍርድ ተሻሽሎ ቅጣቱ ወደ እድሜ ልክ እስራት የተለወጠለት እንደሆነና በማረሚያ ቤቱ ሌሎች ክፍሎች ውስጥ ለረጅም ዓመታት ታስሮ  እንደነበር፤ እነ አቶ አንዱዓለም ወደ አሉበት ክፍል የመጣውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ለምን ከነበረበት ቦታ ተዛውሮ እንደመጣ ግን አልታወቀም፡፡

አቶ አንዱዓለም በተፈፀመበት ድብደባ ምክንያት ከፍተኛ የአካልና የሥነ-ልቡና ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ለህይወቱ በመሰጋት እስካሁን ድረስ ወደ ሆስፒታል ለመሔድ አልፈለገም፡፡ ምርመራና የሕክምና ርዳታ እንዲያገኝ ለማድረግ ግን በቤተሰብ በኩል ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በአቶ አንዱዓለም አራጌ ላይ የደረሰው አካላዊና ሥነ-ልቡናዊ ጉዳት ግልጽ የሚያደርጋቸው ሁኔታች አሉ፡፡ የአቶ አንዱዓለም ደህንነት አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ በሕግ ጥበቃ ሥር ያሉ ዜጎች በህይወታቸው ላይ ጉዳት እንዳይደርስባቸው የሚከላከሉ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሕጎች ቢኖሩም እየተከበሩ አይደለም፡፡

ለምሳሌ፡-

v  በኢፌድሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 2ዐ(3) ላይ እንደተገለፀው እስረኞች እስኪፈረድባቸው ድረስ በተከሰሱበት ወንጀል እንደጥፋተኛ የማይቆጠሩ፤ ከወንጀል ንፁህ እንደሆኑ እንደሚቆጠር ተደንግጓል፡፡ ሆኖም ‹‹በአኬልዳማ›› ድራማ በግልጽ እንደታየው መንግሥት ሙሉ በሙሉ በሚቆጣጠረው ሬዲዮና ቴሌቪዥን በወንጀለኝነት ዘመቻ አካሂዶባቸዋል፡፡

v  በዚሁ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 21(1) ላይ በግልጽ እንደተደነገገው በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሠሩ ሰዎች ሰብአዊ ክብራቸውን በሚጠብቁ ሁኔታዎች መያዝ እንዳለባቸው ተደንግጓል፡፡ ሆኖም በአቶ አንዱዓለም ላይ የደረሰው ድብደባ ያሳየው በማረሚያ ቤት ውስጥ  ሰብአዊ መብትን የሚፃረርና ለህይወት አደገኛ የሆነ ሁኔታ መኖሩን ነው፡፡

v  በ1997 ዓ.ም የወጣው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ አንቀጽ 110(3) ላይ ውሳኔ ያላገኙ እስረኞች ውሳኔ ከአገኙ ሌሎች እስረኞች ጋር አይቀላቀሉም በማለት በግልጽ ደንግጓዋል፡፡ እንዲሁም በኢፌድሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ተሰባስቦና ተተርጉሞ በ1998 ዓም በታተመውና ኢትዮጵያ በአፀደቀቻቸው  የዓለም አቀፍ ሰነዶች በአንቀጽ 85(1) ላይ እንደተገለፀው  ፍርድ በመጠባበቅ  ላይ  የሚገኙ እስረኞች እና የፍርድ ውሳኔ  የተሠጣቸው እስረኞች በአንድ ክፍል አይታሠሩም በማለት በግልጽ ተጽፎ ይገኛል፡፡ ሆኖም ከባድ ወንጀል ፈጽሞ ከባድ ፍርድ የተሰጠው ሰው ገና ፍርዳቸውን ከአላገኙ ሰዎች ጋር እንዲታሰር ተደርጎ በደል ተፈጽሟል፡፡

v  ከላይ በተገለፀው ዓለም አቀፍ ሰነድ ውስጥ በተራ ቁጥር 84(2) ላይ በግልጽ እንደተደገገው፤ የፍርድ ውሳኔ ያልተሠጠባቸው እስረኞች ከወንጀል ድርጊት ነፃ እንደሆኑ እንደሚገመቱ  ከመደንገጉም በተጨማሪ የሚደረግላቸውም አያያዝ በዚሁ ላይ የተመሠረተ መሆን እንደሚገባው ይገልፃል፡፡  ይህ ድንጋጌ አልተከበረም፡፡

በዚሁ ዓለም አቀፍ ሰነዶች አንቀጽ 67(ሀ) ላይ የእስረኞችን አመዳደብ ሲገልጽ ታሪኮቻቸው በወንጀል ድርጊቶች የተሞሉና መጥፎ ጠባይ ያላቸው እስረኞች ሌሎች እስረኞችን በመጥፎ ጠባያቸው  እንዳይበክሉ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ተደንግጓል፡፡  ይህም ድንጋጌ ተጥሷል፡፡ በአቶ አንዱዓለም ላይ ድብደባ የፈፀመው ግለሰብ ከባድ ወንጀል የፈፀመ ከመሆኑም በላይ በማረሚያ ቤት ህይወቱ ፀበኛና ችግር ፈጣሪ መሆኑ ይነገራል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በተገኘው መረጃ መሠረት በአቶ አንዱዓለም ላይ ድብደባ የፈፀመው እስረኛ ከእነ አቶ አንዱዓለም ጋር  ከነበረበት ክፍል ተወስዶ 3ዐዐ ያህል ታራሚዎች ወደሚገኙበት ሌላ ቤት መዛወሩ ታወቋል፡፡  እዚህ ላይ የተከሰተው አዲስና አሳሳቢ ጉዳይ  ይህ ፍርደኛ በዚሁ ቤት ውስጥ ከሚገኘው የአንድነት አመራር አባል ከአቶ ናትናኤል መኮንን ጎን እንዲተኛ መደረጉ ነው፡፡ በአቶ አንዱዓለም ላይ የፈፀመውን ድርጊት በአቶ ናትናኤል ላይም ይፈጽም ይሆናል የሚል ስጋት አለን፡፡

በአቶ አንዱዓለም ላይ የተፈፀመው በደል እንዲጣራና በደል ፈፃሚው ግለሰብ ላይ ተገቢው ርምጃ እንዲወሰድ፤ ከሁሉም በላይ ግን የማረሚያ ቤቱ አስተዳደርና መንግሥት  ሕገ መንግሥቱንና አግባብ ያላቸው ሕጎችን፤ እንዲሁም ሀገሪቱ ያፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ሕጎችን በማክበር  በህግ ጥበቃ ስር ላይ የሚገኙ  ዜጎቻችን  ህጉ በሚያዘው መሠረት ደህንነታቸው እንዲጠበቅ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) አጥብቆ ይጠይቃል፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

የካቲት 13 ቀን 2ዐዐ4 ዓም

አዲስ አበባ

Continue reading …

የቻይናው ደራጎን (dragon can be translated to “zendo” like St. George killing zendo on his horse with a spear; also the image of zendo suggests that one day he will face the spear of Ethiopian people) (ጭራቅ) ከአፍሪካውያን ጅቦች ጋር አሸሸ ገዳሜ ጭፈረውን እያስነካው ነው፡፡ለዚህ (zendo) ደራጎን አፍሪካ በምንም መልኩ ተስማሚ ሁኔታ አትፈጥርለትም፡፡ታሪክ እንደሚያስረዳው በአንድ ወቅት የአፍሪካውያን መኩሪያና መመኪያ የነበረችው ምድር አሁን የጅቦች መሰባሰቢያ ትልቅ ዋሻ ፈጥራ (የአፍሪካ ሕብረት) የጅቦቹ መፈንጪያ መናሃርያ ሆናለች፡፡ለዚህ የጅቦች መገናኛ፤መዶለቻ፤መለመኛ፤ሕዝባዊ ማነቆ መፍተያው ሁሉ ለሚከናወንበት ግንባታ የሚያስፈልገውን ወጪ 200 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተሸፈነው በቻይና ነው፡፡ ሲባልም፤ ይህ ቻይና ለአፍሪካ የሰጠችው የሰው በላዎቹ (ጅቦች) የአፍሪካ መሪዎችልመና መልስ ነው በማለት ጅቦቹ የታላቁን ye zendo ደራጎን ስጦታ ለማመስገን በተሰበሰቡበት ወቅት የተሰነዘረ አባባል ነው፡፡
(space between paragrpahs)
Indent to show quotation
ይህ ውብ ግንባታ………ከእንግዲህ የአህጉራችን የሕብረት አባላት የሚሰበሰቡበት ማዕከላዊ ቢሮ ሲሆን፤የተገነባውም በቀድሞው የሃገራችን ዓለም በቃኝ በመባል ይጠራ በነበረው ነፈሰ ገዳዮች፤ ሌቦች፤አስገድዶ ደፋሪዎች፤ፍትህን የሚያዛቡ፤አጭበርባሪዎች፤ወዘተ ይታሰሩበት በነበረበት የወህኒ ቤቱ ፍራሽ ላይ ነው፡፡ ይህ ታላቅና ግዙፍ ሕንጻ የሚያመላክተው የአህጉሪቱ መሪዎች ለዓመታት በሕዝብና በሃገር ላይ ጭነውት ያለው መከራና ስቃይ፤የነዚህ ሰው በላዎች የጅብነት ዘመን ማለቂያውንና እንደፈረሰው የወንጀለኞች ማጎርያ የነሱም የግዛት ዘመን አብቅቶ፤ አህጉሪቱና ሕዝቦችዋ ለዘመናት ከተጫነባቸው ሰቆቃ ነጻ የሚሆኑበት ዘመን መቃረቡን ነው፡፡ ስለዚህም ቻይና ይህን ግንብ ማስገንባቷ ትክክልና ተገቢም ነው፡፡ምክንያቱም ተከታዩ ዘመን የአፍሪካ ትንሳኤ ነውና፡፡ ዘመኑ ያለቀባቸውም በግፍ ሥልጣን ላይ ያለሕዝባዊ ፈቃድ የተጎለቱት መሪዎችም ለፍርድ የሚቀርቡበት ወቅት መዳረሻው በመሆኑ፡፡
(space)
ይህን የአፍሪካን ትንሳኤ የሚያመላክት አዳራሽ፤የአፍሪካን ራዕይ የሚጠቁመውን ግንባታ በመገንበታችሁ……… ለቻይና መንግስትና ሕዝብ ከፍተኛ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፤ ይህ ግኑኝነታችንም ዘላቂነት ያለው ሆኖ በየጊዜው እንዲያብብ እንመኛለን ስልም የምናገረው ሁላችንንም በመወክል ነው፡፡
(space)
ስለቻይና መንግሥት ችሮታ ምስጋናውና ጫማ መላሱ መጨረሻ አልነበረውም፡፡‹‹ስጦታው›› በአፍሪካና በቻይና መሃል የተገነባውን ወዳጅነት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መሄዱን አመላካች ነው፡፡የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ፕሬዜዳንትና ከ1979 አንስቶ የኤኳቶሪያል ጊኒ ፈላጭ ቆራጭ ፕሬዜዳንት ቴዎድሮ ኦቢያንግ ኢንጉዌማም በባለ 20 ባለመስታወት ፎቅ ላይ ሆነው መጪው በሚገባ ታየይቷቸዋል፤ለዚህም ነው…… የአዲሲቱ አፍሪካ የነገው ነጻ አፍሪካና አፍሪካውያን የብርሃን ፍናጣቂ፤ ለወደፊቷ አፍሪካ የምንፈልገው›› በማለት ሳይገባቸው እውነቱን የተናገሩት፡፡

Zendowum ደራጎኑም በበኩሉ ተስማምቷል!
‹‹………በቻይናና በአፍሪካ መሃል የቆየ ልማዳዊና ባሕላዊ ግንኙነት አለ፡፡ቻይና ምንጊዜም ቢሆን የአፍሪካ ጥሩ ወዳጅ፤መልካም አገር፤እና ታማኝ ወንድም ነች፡፡አንድነትና መረደዳት ልማታዊ ድጋፍ በቻይናና በአፍሪካ መሃል የኖረና ወደፊትም ቢሆን ዘለቄታ ያለው እንዲሆን እቅዳችን ነው፡፡ ……. ሠላም መረጋጋትና ልማት ቅድሚያ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባን ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃም አፍሪካውያን ችግራቸውንና አለመግባባታቸውን በራሳቸው እንዲፈቱ ምርጫቸውን እናከብራለን፡፡ በአፍሪካ የውስጥ ጉዳይ በራስ ወዳድነት በመነሳትና የራስን ጥቅም በማስቀደም መግባት ችግሩን በመፍታት ፈንታ ይበልጡን ያወሳስበዋል፡፡ ሶስተኛም አፍሪካውያንን በህብረት ጥንካሬያቸውን እንዲያጎለብቱ ድጋፋችን አይለያቸውም፤አራተኛ የአፍሪካን ልማት በማስቀደም የበለጠ ድጋፍ ልናደርግ ተገቢ ነው፡፡ በቻይና አፍሪካ ወዳጅነት ዕድገት ሂደት ውስጥ ጣልቃ አለመግባትንና የየሃገራቱን ልእልና አክብረን በውስጥ ጉዳያቸውም ላላመግባት ውሳኔያችንን እናከብራለን……….ለአፍሪካ ከምናደርጋው ድጋፍ ጋር የፖለቲካን ክር እንደማነቆ ጨርሶ አናያይዝም……….የአፍሪካንና የቻይና ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርም ከምንም ነጻ የሆነ የ600 ሚሊዮን ብር እርዳታችንን ለአፍሪካ ሕብረት በሚቀጥለው ሶስት ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ እናደርጋለን፡፡››
በአፍሪካ የ‹‹ቻይና ሞዴል››
የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች በቻይና ሞዴል የኤኮኖሚ ልማት በሚለው መርሃ ግብር ላይ የእኔ እቀድም እኔ እቀድምና የቻይና ፍቅር ለእኔ ለእኔ ማለትንና መሽቀዳደምን እንደፈሊጥ ይዘውታል፡፡ የሕዝብን ይሁንታ አግኝቶ የማያውቀውና የኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ ገዢው መለስ ዜናዊ የቻይና ሞዴል የሚለውን በመከተል ታማኝነቱን አረጋግጧል፡፡
(space)
ሁላችንም ስንመኘውና ስንጓጓለት የነበረው የአፍሪካ ትንሳኤ እውን ለመሆን መንገዱን ጀምሯል፡፡ለዚህም ማስረጃ ሊሆን የሚችል አልኩ ባዮችና ምሁራን በአደባባይ ስለአፍሪካ ዳግም ወደ ቅኝ ግዛትነት መመለስን ሲያውጁ ቢከርሙም አሁን ግን መታቀብ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡ የአህጉራችን ይህ ውብና ድንቅ ሆኖ የታነጸው አዲሱ ማከላችን የአፍሪካ ሕብረት በትግላችን መሀላ በመተግበሩ የአፍሪካን ትንሳኤ አመላካች ነው፡፡
የቻይና ሞዴል ማለት ግን በእርግጠኝነት ምንድን ነው?
የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች የቻይና ሞዴል የሚለውን ቃል በግልጽና በትክክል ለማስረዳት ፈቃደኛ ከመሆን ይልቅ፤ እንደ ኮከብ ቆጣሪና መወድስን እንደማያውቀው አጭበርባሪ ጠምጣሚ ከንፈራቸውን በማላወስ ብቻ ያልፉታል፡፡ እነዚህን ፈላጭ ቆራጭ ሰው በላ ጅቦች የማመን ትንሽም ቢሆን ፈቃደኝነቱ ካለን፤‹‹የቻይና ሞዴል አፍሪካን ከተጫናት ድህነትና ችጋር አላቆ፤ የሕዝቡን መሰረታዊ ፍላጎት አሟልቶና ነጻነቱን አስረክቦ፤በኢኮኖሚና በኢንዱስትሪው ዘርፍ እድገቱን ለማፋጠን የሚያስችል ነው፡፡››ቻይና የዓለም የኦኖሚ ሃይል ልትሆን የበቃችው፤ ለሃገር ውስጥና ለውጭ ተወላጆች ኢንቬስተሮች በሯን በመክፈትና ታክስን በመቀነስ፤ አስፈላጊ በሆኑትም ሂደቶች የጋራ አዋ|ጪ (spelling)በመሆን፤እንዲሁም የጉልበት ሥራን ሰፋ በማድረግ ነው፡፡ይህ ነው ለቻይናና ለአፍሪካ የእኩል በእኩል ሁኔታን ይፈጥራል የሚባለው፡፡
እዚህ ላይ ግን አንድ ማነቆ ተቀምጧል፡፡ ቻይና ይህን እመርታ ልታሳይ የሄደችበት መንገድ እኮ ማንኛውንም ጉዳይ በአንድ ፓርቲ ስርአት ውስጥ ጠፍራ በመያዝና፤ማንኛውንም እንቅስቃሴ፤የሲቪል ማህረሰቡንም፤ ወታደራዊ ተቋማትን፤የደህንነቱን መዋቅር፤በአጠቃላይ ስርአቱ ሥር ያሉትን ሁሉ የመንግሽትን ጥቅምና ፍላጎት፤ ደህንነት ጠባቂዎች በማድረግና ሕዝቡን በማግለል የሕዝቡን የእለት ተእለት እንቅስቃሴና ሃሳቡን የመግለጽ ፍላጉተቱን ሁሉ መቆጣጠርያና የቅድሚያ ማክሸፊያ መዋቅር በመዘርጋት ነው፡፡

ስለ የቻይና ሞዴል ወደ አፍሪካ ስለመምጣቱ ጉዳይስ ቻይና ምን እሳቤ አላት?

‹‹ብዙ እሳቤ የለንም›› ይላሉ በአፍሪካ ጉዳይ ልዩ የቻይና ወኪል የሆኑት ሊዩ ጉጂን በእርግጠኝነት ሲገልጹ ‹‹አሁን እያደረግን ያለነው ልማዳችንን ማካፈል ብቻ ነው፡፡እውነት እላችኋለሁ እመኑኝ ቻይናውያን የፖለቲካ እምነታችንን፣ የአገዛዝ ስርአታችንን፤ ወደ አፍሪካ እንደውለታ ክፍያ ለማስተላለፍ ሃሳብም ሆነ ፍላጎት የለንም፡፡ እኛ ራሳችን ገና ሞዴላችን የዳበረና የተዋጣለት፤ ብቃቱ የተረጋገጠለት የቻይና ሞዴል ነው ብለን አናምንም››
ታዲያ የቻይናውያን መሪዎች እምነታቸው ይህ ከሆነ፤ በአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ሞዴል እያሉ የሚያጨበጭቡለትንና ሰማየ ሰማያት እያወጡ የሚጨፍሩለትን ሞዴል ባለቤቶቹ ገና ያላደገ ያልለማ፤… ነው የሚሉትን ሞዴል ይዘው አሸሸ ገዳሜ የሚያምቧርቁት? ምናልባት እነዚህ ደም መጣጭ የሆኑ የአፍሪካ ዲክታተሮች የቻይና ሞዴል የሚሉትን እንደአይነርግብ መከለያቸው በማድረግ ኢኮኖሚውን ከአፍሪካ ጥገት አላበው ለመጨረስ ማስመሰያ የእድገት መስመር አድርገውት ይሆን?‹‹ቀልቀሎ ስልቻ ስልቻ ቀልቀሉ›› እንዲሉ አይነት ነው እንጂ የ‹‹ቻይና ሞዴል›› ያው እንዳለው ye and gezi የአንድ ፓርቲ ስርአት ከ1960 የቅኝ ግዛት ማነቆ ወጡበት ጊዜ ጀምሮ የነበረና ያለ ነው፡፡የዩጋንዳው ዩዌሪ ሙሴቪኒ፤የሩዋንዳው ፖውል ካጋሚ፤የ86 ዓመቱ የዝምባዌው ሮበርት ሙጋቤ የግዛት ዘመናቸውን ለማራዘም የተጠቀሙበት ሞዴል ነው አሁንም ተመልሶ የቻይና ሞዴል ተብሎ የሚለፈፈው፡፡ባለፉት የፍቅር ወቅቶች መለስ፤ሙሴቪኒና ካጋሚ (በክሊንተንና በብሌር ይሁንታ በተጫነላቸው ክብረ ዘውድ) ‹‹የአዲሲቱ አፍሪካ አዲስ ትውልድ መሪዎች›› በመባል የግዛት ዘመናቸውን ለማራዘም እንዲችሉ ተብሎ ይጠሩበት ነበር፡፡አሁን ደሞ የምእራቡ ዓለም መልእክተኞችና ጉዳይ ፈጻሚ በመሆን በየተላኩበት ሰብአዊ መብትን በመግፈፍ፤ የሕግን ልዕልና በመድፈር፤ ሰብአዊ መብትን በመጣስ የተልእኮ ክፍያቸውን ግብር ከፋዩ ሕዝብ በማያምንበት ቦታ እንዲውል እየተደረገ ለነዚህ ሰው በላ ፈላጭ ቆራጮች የአገልጋይነታቸውን እየተከፈሉ ነው፡፡ create paragraph here)
በሌላ በኩሉ ግን ጉዳዩ ያሳሰባቸው ሁሉ ስለነዚህ አፍሪካውያን አገልጋዮች ተግባር በአግባቡ ከማጋለጥና አለአግባብ ከሕዝብ የሚሰበሰብም ክፍያ መቆም እንዳለበት ትግላቸውን አላቆሙም፡፡የአንድ ሰው ለገዢነት የአንድ ፓርቲ መመሪያነት ተጨፍልቆና አዲስ ስመ ጥምቀት ተሰጥቶት አሁን ‹‹የቻይና ሞዴል›› የሚባለው ቀደም ሲል ክዋሚ ንክሩማህ የሰብ ሰሃራው አፍሪካ መሪ ሞክሮት ተስፋ በሚያስቆርጥ መልኩ የከሰፈ (keshefe) ተሞክሮ ነው፡፡ንክሩማህ ልክ እንዳሁኑ ወቅታዊው የቻይና ሞዴል አራጋቢ ብርማ መሳይ ምላስ፤ ንክሩማህም በዚያን ወቅት ኒኦ ኮሎኒያሊስምን (ንክሩማህ የፈጠረው የማስጠያ ቃል) እና ኢምፔሪያሊዝምን አፍሪካን በመበዝበዛቸውና ለድህነት በመዳረጋቸው ይረግምና ያወግዝ ነበር፡፡ የንክሩማህ ፈጣን የኢንደስትሪያላይዜሽን ፕሮጋራም ጋናን ከውጭ ምጸዋትና እርዳታ፤ በሀሃገሪቱ የካካዋ የዓለም ግብይት ላይ ከፍተኛ ውድቀት አድርሶ ነበር፡፡ሌሎችም ተግባራዊ ያደረጋቸው የኤኮኖሚ ልማት እቅዶችም በማያዳግምና ትንሳኤ በሌለው መልካቸው ለውድቀት ተዳረጉ፡፡
በ1966 ዓም በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን በወረደበት ጊዜ ጋና በአፍሪካ ከፍተኛ ሃብታም ከመባል ደረጃ ወርዳ Ghana ዝቅተኛ የችጋር ሃገር ሆና ነበር፡፡በተመሳሳይም በአፍሪካ ከፍተኛ የእርሻ ምርት ውጤት ላኪነት አሽቆልቁላ ወደ ከፍተኛ የእርሻ ምርት ውጤት ገዢነት ወርዳለች፡፡የአንድ ሰው አንድ ፓርቲ መኖር እንደብሔር ግጭት አስወጋጅ፤የዘር ግጭት ፈጪ ከመሆን ይልቅ በይበልጥ አጉልቶ ያሳየው የጭግሩ አባባሽና የግጭቶቹ አመንጪና አባባሽ መሆኑን ነው፡፡እንዲያውም ከበርካታ ተሞክሮዎች እንደታየው የዚህ አገዛዝ ዋናው ተግባር እነዚህን ችግሮችና ግጭቶች በመፍጠር በሕብረተሰብ መሃል አለመግባባትና ግጭት ተጠናክረው የሃገሮች የአንድነት ነቀርሳ እንዲሆኑ ማድረግ መሆኑ ታይቷል፡፡ይህ እውነታም በአፍሪካ አህጉር ከሃገር ሃገር እንደ ሰደድ እሳት በመያያዝ ተዳርሶ የሃገሪቱን መኩሪያን ታሪካዊነት የሚመሰክሩትን፤ የውጭ ጎብኚዎችን የሚስቡትን የዱር አራዊት ጭምር ለስደትና ለርሃብ ዳርጓል፡፡ያም ሆኖ ግን የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች፤የወታደራዊ ጁንታ ገዢዎች፤አለ ያሉትን ዘዴያቸውን ሁሉ አንድ ገዢ አንድ ፓርቲ ያለውን ጠቀሜታ ለማሳመን የቱንም ያህል ቢፍጨረጨሩ ውጤቱ ግን ከገሃዱ እውነታ ሊያልፍላቸው አልቻለም፡፡ያም እውነታ ባለብዙ ፓርቲ መሆንን ብቻ ማዋጣቱንና ጠቀሜታው ነው፡፡ አሁን ያሉት ፈላጭ ቆራጭ የአፍሪካ እርባና ቢስ ገዢዎች ደግሞ እንደገና ወደ ኋላ መልሰው አፍሪካን ሊገድል ማነቆ አስሮባት ሲያስጨንቃትና አላላውስ ብሎ እንደግመል ሽንት ወደኋላ ሲጎትታት የኖረውን ስርአት ሊያመጡ ያረጀውንና የአግልግሎት ዘመኑን የጨረሰውን የማይላስ የማይቀመሰውን ጉዳይ በአዲስ ካባ ደርተው ‹‹ምርጡ የቻይና ሞዴል›› ብለው ሊያለብሱን ይዳዳቸዋል፡፡ያንኑ ተዝካሩ የተባላውን አንድ gezhi ሰው አንድ ፓርቲ፡፡
የ‹‹ቻይና ሞዴል›› በአፍሪካ ያለው ሁኔታ
መለስ ዜናዊና ሌሎቹ የተባበሩት የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ይህን ገና ‹‹እምቦቀቅላ›› የሆነውን ‹‹ቻይና ሞዴል›› በእውነት መልኩ እየተቀበሉትና እየተከተሉት ነው? የሃገር ውስጥና የውጪ ኢንቬስተሮች በአፍሪካ ሥራቸውን ለማከናወን ነጻ እንቅስቃሴና ትግበራ አላቸው? ባልተብብራሩና ምንነታቸው በግልጽ መረዳት በማይቻል፤ ባቃዣቸው ቁጥር በሚወጡ ደንቦችና መመርያዎች ሳይታሰሩና ለችግር ሳይዳረጉ ይንቀሳቀሳሉ? እውቀት የለሽ የባለስላጣኑ ጃዊሳዎች ሳይጎሽሟቸውና መላ ቅደሱን ሳያጠፉባቸው ድርጅቶቻቸውን ይነራሉ? የነገው አዋጅና ደንብ ምን ይለን ይሆን ብለው ከማሰብ ይልቅ ለገበያው አስፈላጊው፤ ለፈላጊው ጠቃሚው ምን ይሆን ብለው ማቀድስ ይችላሉ? ለመሆነጁ በኢትዮጵያ ካለው ሥራ ውስጥ ስንቱ ነው ለመደራደር በሚያመችና ግልጽ በሆነ መመርያ የታቀፈው የኢንቬስትመንት አካል? የ2011ዱ የዓለም ባንክ ያወጣውና 183 ሃገራትን የፈረጀበት መመዘኛ (The 2011 World Bank Ease of Doing Business Index) በኢትዮጵያ ያሉትን ሁኔታዎች መመዘኛው በአሳዛኝ ደረጃ ላይ ያስቀምጣል፡፡በአጠቃላይ ግምገማው 111ኛ ያደርጋትና፤”ሥራን ለመጀመር (99) የግንባታ ፈቃድ ለማከናወን (56) የመብራት ተጠቃሚ ለመሆን (93) ንብረትን ለማስመዝገብ (113) ብድር ለማግኘት (150) ኢንቬስተሮችን ጥቅም ማስጠበቅ (122) ታክስ ለመክፈል (40) ወደ ውጭ ገበያ ለማቅረብ (157) ውልን ማስከበር (57) አለመግባባትን ለመፍታት (89)

የ‹‹ቻይና ሞዴል›› ለመለስ ዜናዊና ለግብረአበሮቹ ፈላጭ ቆራጮች በስልጣን ለመቆየት የሚያጠልቁት ጭንብላቸው ነው፡፡ ይህንኑ ጭምብል ደሞ በሕዝቡ አመለካከት ላይ አጥልቀው እውነቱን እንዳያውቅ ሊያደርጉታ ይሞክራሉ፡፡ ይህን በማድረግም ግልጥነትና ተጠያቂነት እንዳይኖራቸው፤ተወዳዳሪና ተቀናቃኝ ያሉበት ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ እንዳይኖር፤ሕዝቡ የንብረት ባለቤትነት መብት እንዳይኖረውና ሁል ጊዜ የስርአቱ ለማኝና የሃገሩ ባይተዋር እንዲሆን፤ሃሳብን በነጻነት እንዳይገልጽ፤ነጻ ፕሬስ እንዳይኖር፤የፍትህ አካላት ታዛዥነታቸው ለፍትህ ስርአቱ ሳይሆን ለገዢዎች ጥቅም ማስጠበቂያ እንዲሆን የሚያደርጉትን ጸረ ህዝብና ጸረ ሃገር ድርጊታቸውን ለመሸፈን ይጠቀሙበታል፡፡ በዚህ ድርጊታቸው ሕዝቡ የስርአቱ ተገዢና አገልጋይ እንዲሆን፤ ለመቆጣጠርያነት ፖለቲካውን በማነቆነት በማስቀመጥ፤ ኤኮኖሚውን ተብትበው በማሰርና በኪሳቸው በመክተት ሃገሪቱን ለችጋርና ለምድረባዳነት፤ ሕዝቡን ለመከራ ስቃይና ኑሮን ለመጥላት ማድረጊያነት ሆን ብለው ይጠቀሙበታል፡፡የ‹‹ቻይናን ሞዴል›› የኤኮኖሚ ልማትን በመቃዠት ደረጃ እያራገቡ የፖለቲካ ነጻነትን በገሃድ ለመጨፍለቅ የሕዝቡን ዴሚክራሲያዊ ነጻነት መርገጥ ስለሚያስችላቸው ሕዝቡን በዚህ እያማለሉ የሃገሪቱን ብሔራዊ ኤኮኖሚ በግላቸው ይመገምጉታል፤ያደርቁታል፡፡
(space)
በቅርቡ፤ፋይናንሻል ግሎባል ኢንተግሪቲ ሲጽፍ፡- ‹‹ ……ኢትዮጵያዊያን ደማቸው ተመጦ ተመጦ ባዷቸውን እየቀሩ ነው፡፡ከአዘቀጠው የድህነት አረንቋ ለመውጣት ምንም ያህል ቢጠሩና ቢድሁ ዋናቸው ወንዙ ወደሚፈስበት ሳይሆን ወደሚመነጭበት ስለሆነ እስከማዕዜኑ ከዚያ መውጣት ዘበት ነው፡፡›› ይህ ነው እንግዲህ ለኢትዮጵያና ለአብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሃገራት የ‹‹ቻይና ሞዴል›› የሚባልላቸው፡፡

Continue reading …

በሽብርተኝነት ስም በእስር ላይ ሚገኘው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አንዱአለም አራጌ ቃሊቲ በሚገኘው እስር ቤት ውስጥ በተቀመጠበት በታህሳስ 7 ቀን 2004ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ለጠያቂዎች ገለፁ፡፡ ፊታቸው ላይም ጠባሳው የሚታይ ሲሆን ጭንቅላታቸው አካባቢም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
አቶ አንዱአለም ለወንድሙ አቶ አብርሀም አራጌ በብስጭት እንደነገሩት በማረሚያ ቤቱ የተቀነባበረና የታቀደ ጥቃት እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ጠቁመው ለማስረጃ የሰበሰቡዋቸው ወረቀቶችም ሆን ተብሎ ክፍላቸው አብሮ እንዲታሰር በተደረገ ግለሰብ ተወስደዋል፡፡ ‹‹በዚህ ጉዳይ ብበሳጭም የግለሰቡ ተልኮ ስለገባኝ ዝም ከማለት ውጭ ምንም አላልኩም፡፡›› ያሉ ሲሆን እንደገና ‹‹በተቀመጥኩበት ሳላስበው በቦክስና በእርግጫ በግለሰቡ ተደብድቤያለሁ፡፡ ህይወቴን ያተረፉትም አቶ በቀለ ገርባ ናቸው፡፡ ለማረሚያ ቤቱ አቤት ብልም መፍትሄ ሊሰጡኝ አልቻሉም፡፡ በዚህ አይነት ለህይወቴም እንደሚያሰጋኝ እና በዚች ሀገር ላይ አየተፈፀመ ያለውን ግፍ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቅልኝ እጠይቃለሁ፡፡›› ብለዋል፡፡

 

Contact Fnote Gazeta: fnotenetsanet@yahoo.com

Continue reading …

  PDF- የአፍሪካ ሕብረት ህንጻ ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ሃገሬ

 

Continue reading …

ይቅርታ አድርጉልኝ፡፡ በሰው ስቃይ የመደሰት ባሕርይ አለኝ ብዬ አላምንም፡፡ ግን ሰው ነኝና በኔ ግንዛቤ መሠረት ክፉ ሠሩ የምላቸው ሰዎች ወይም ሕይወት ያላቸው ሌሎች ፍጡራን የሥራቸውን ሲያገኙ ይከፋኛል ብል ራሴን ማሞኘት ይሆንብኛል፡፡ አለበለዚያ ሰው መሆኔ ይቀርና ሌላ ‹ነገር› ነኝ ማለት ነው – በምድር ላይ እንደሰው እዬተንቀሳቀስኩ ሌላ ነገር ልሆን በፍጹም ላይቻለኝ፡፡ ይህ አባባሌ ከግለሰባዊ አንድምታ ወጥቶ በሀገራዊ የፖለቲካ ምህዋር ዙሪያ ብቻ እንዲሽከረከር እፈልጋለሁ፡፡ አለበለዚያ የ‹ፉኣድ› መሰቃየት ወይም መሞት ከ‹ሀብተ ማርያም› መሾም ወይም መሸለም ጋር በተገናኝ መልኩ ልከፋ ወይም ልደሰት /ልደሰት ወይም ልከፋ/ ይጠበቅብኛል ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለኔ ስህተት ነው፡፡ ከዚህ ወደሚሻል ሌላ ነገር እናምራ፡፡…

ሊቢያ፤ ጋዳፊ በውነትም ዕብድ ነበር ማት ይቻላል፡፡ ለ42 ዓመታት ያህል ራሱንም ሀገሪቱንም አሳብዶ በመጨረሻው መጨረሻ በሰውኛ ዓለም ላይ የመጨረሻውን ውርደት ተዋርዶ ሞተ፤ የመሰሎቹ ዕጣ ፋንታም ይዋል ይደር እን ከዚህ ቢከፋ እንጂ የተለዬ እንደማይሆን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ቃዛፊም በሉት ጋዳፊ እንደሰውነት ተፈጥሮው ያሳዝናል፡፡ እንደጭራቃዊ ባሕርይው ግና በሠፈረው ቁና መሠፈሩ – ስለአይቀሬውና ስለአይጠረጠሬው የፈጣሪ ፍርድ – በእጅጉ ያስደስታል፡፡ እያዘኑ እስክስታ ማለት ይህንን ነው፡፡ በሰው አምሳል ተፈጥሮ ሳለ ጭራቅ መሆኑና የጭራቅነቱን ዋጋ ማግኘቱ ያስደስታል፤ በሰው አምሳል ተፈጥሮ ሳለ በገንዘብና በሥልጣን ስካር ምክንያት እንደአንድ ጤናማ ሰው ሕይወቱን መርቶ ዘመኑን በአግባቡ ባለማጠናቀቁና ዐይጦች በሚላቸው ወገኖች እንደዐይጥ ከተደበቀበት የመስኖ ውኃ መተላለፊያ  ደረቅ የስሚንቶ ቱቦ ውስጥ ተይዞ አላግባብና አለፍርድ መገደሉ ያሳዝናል፡፡ በኢትዮጵያ ላይ የሠራው አንዳች ነገር መኖሩንም አንዘንጋ ታዲያ! አንድ በሉ – ከሁለት በላይ እንጂ ሁለት ባይኖርም፡፡

ኢራቅ፤ ዝርዝር ውስጥ መግባት አያስፈልግም፡፡ በአጭሩ ግን ሀገሪቱ ጃርት የበላው ዱባ ይመስል   ቡትርፍርፏ ወጥቷል፡፡ የቀድሞውን ጨካኝ መሪ በሚያስናፍቅ ሁኔታ የሀገሪቱ ሕዝብ ክፉኛ ተቸግሯል፡፡ ‹የወደዱትን ሲያጡ የተሉትን ይቀላውጡ› እያለ ይመስላል – እንደኢትዮጵያ     ሕዝብ ወይም ‹ሕዝቦች›፡፡ የቀድሞው የሀገሪቱ አምባገነን መሪ ሣዳም ሁሴን በኢትዮጵያ   ላይ የሠራው አንዳች ነገር መኖሩን ግን አንዘንጋ! ‹ለኃጥኣን የመጣ ለጻድቃን     ይተርፋል›፡፡ ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም፡፡

የመን፤ ዝኒ ከማሁ ( እንደላይኛው ማለቴ ነው – እንደኢራቅ)

አሜሪካ፤ ዝኒ ከማሁ

ኢራን፤ ዝኒ ከማሁ

ሱዳን፤ ዝኒ ከማሁ

ሶማሊያ፤ ዝኒ ከማሁ

ሦሪያ፤ ዝኒ ከማሁ

ሳዑዲ ዐረቢያ፤ ዝኒ ከማሁ

ግብጽ፤ ዝኒ ከማሁ ( ትናንት እግር ኳስ ጨዋታ ምክንያት የተላለቁትን ወንድምና እህቶቻችንን      ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይማር)

ሶቪየት ኅብረት(የቀድሞዋ)፤ ዝኒ ከማሁ

እንግሊዝ፤ ዝኒ ከማሁ

እስራኤል፤ ዝኒ ከማሁ

    ወዘተ… ዝኒ ከማሁ

ምን አለፋን፡፡ በኢትዮጵያ ላይ ዐውቆም ይሁን በየዋህነትና በሥልታዊ ብልጣ ብልጥነት ወይም በአክራሪነትና በለዘብተኛነት አንዳች ተንኮል የሠራ ሀገር በአብዛኛው በአሁኑ ወቅት የሥራውን እያገኘ ነው፡፡ ከቅርብ እስከ ሩቅ፣ ከክርስቲያን እስከ እስላም፣ ከ‹መናፍቅ› እስከ ኢአማኒ፣ ከዘረኛ እስከብሔርተኛ፣ ከጥቁር እስከ ነጭ፣ ከቢጫ እስከ ሶላቶ(ክልስ)፣ ከ‹ምሁር› እስከ ማይም፣… አሁንም ምን አለፋችሁ በኢትዮጵያ ላይ እጁን ያነሳ ሁሉ በአሁኑ ወቅት ያ ያነሳው እጅ እየተቆረጠ ነው፡፡ የዕዳ ክፍያው – ማለትም የእጅ ቆረጣው ደግሞ – ገና ተጀመረ እንጂ አልተሟሟቀም እንኳን፤ ምን አየንና፡፡ በባህላዊ ፉከራችንስ እንዲህ እንል የለም እንዴ? ደግሞ ለፉከራ! ‹ የማን ቤት ፈርሶ የማን ሊበጅ፤ ያውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ›፡፡ ምን አየንና፡፡ ‹የኢትዮጵያ ጠላቶች እጆች ከኢትዮጵያ ጨርሰው እስኪነሱ ድረስ ዓለም ሰላም አታገኝም› ሲባል እሰማው የነበረው ብሂል እውነት መሆኑን በማረጋገጥ ላይ እንገኛለሁ፡፡ ኢትዮጵያውያን ርስ በርስ ክፉ ቢሆኑም እንኳን ለውጮች ደግና እንግዳ አክባሪዎች ናቸው እንላለሁ – ይህ አባባል ውኃ እሚያነሣም ይመስለኛል( በነገራችን ላይ ይሄ ‘does/doesn’t hold water’ እሚሉት የፈረንጆች ፈሊጥ ከኛው ሀገር ሳይሄድ ይቀራል? ‹ውኃ ይቋጥራል/አይቋጥርም› በሚሉት ሳይሆን ‹ውኃ ያነሣል/አያነሣም› በምንለው ከሴቶቻችን የቀደመ የባልትና ሙያ ጋር በተያያዘ ማለቴ ነው)፡፡ ስለሆነም እንግዳ አክባሪን መበደል የግፍ ግፍ ነው፡፡ በየትም ሀገር የሌለ የእንግዳ አቀባበል በኢትዮጵያ ውስጥ አለ፡፡ እነዚህን ደጋግና በተለይ ለውጭ ሀገር ሰዎች እንጀራ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን መበደል ደግሞ በራስ ላይ እሳት መጫር መሆኑን እስኪያውቁ ድረስ ከዛሬ መቶ ሃምሳ ዓመታት ገደማ ወዲህ እንደመና ከሰማይ የወረደ በሚመስል የ‹ንፋስ ወለድ› ፈሳሽ ንጥረ ነገራዊ አዱኛ ልባቸው የደነደና መንፈሳቸው የሰየጤነ እኚያ ጥጋበኞች አሁንና ከአሁን በኋላ የዘሩትን የሚያጭዱበት ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረላቸው ያለ ይመስለኛል፡፡

እንዳዘነና እንደቆዘመ ዕድሜ ልኩን የሚኖር፣ ጮቤ እንደረገጠና በሰው ትከሻ ላይ ዳንኪራ እንደረገጠም እስከወዲያኛው የሚዘልቅ የለም፤ የተፈጥሮን ሕግ በገንዘቡም ሆነ በዕውቀትና በችሎታው ሊለውጥ የሚችል ሰው ሠራሽ ኃይል እስካሁን አልነበረም፤ ወደፊትም ይኖራል ተብሎ አይገመትም፡፡ … ብቸኛው አዋጪ መንገድ ወደ ጤናማ ኅሊና መመለስ ብቻ ነው፡፡ ጨካኝነት ጨካኝነትን ይወልዳል፤ ለዚህም ነው ‹አንቺም ጨካኝ ነበርሽ ጨካኝ አዘዘብ፤ እንደገና ዳቦ እሳት ነደደብሻ› ተብሎ እሚተረተው፡፡ … ኢትዮጵያንም ሆነ ሌላን ሀገር በማያገባው ገብቶ የናቀና ኅልውናን የደፈጠጠጠ ራሱን አዋረደ፤ የውስጥ መዥገርንም አሰልጥኖ በመንበረ መንግሥቱ ላይ በማስቀመጥ ሉዓላዊነትን የደፈረ ወይ ያስደፈረ በራሱ መፃኢ ሀገራዊ ኅልዉና ላይ ጥቁር የታሪክ ጠባሳ አስቀመጠ፡፡

‹ክፉም ለራስ፤ ደግም ለራስ›፡፡ የሰጠ አበደረ እንጂ አልሰጠም፡፡ ሰውን የቀማ ራሱ ተዘረፈ እንጂ አላተረፈም፤ ዕዳ ይውል ያድር ይሆናል – ነገር ግን ካለሁለትዮሽ ዕውቅና እንዲሁ በባዶ ሜዳ አይሠረዝም፡፡ ከተዋረደ ይልቅ ያዋረደ ሊታዘንለት የሚገባው ነው – ያዋራጅ የዞረ ድምራዊ ውርደት ከቀዳሚው ምሥኪን ውርደት የከፋ ይሆናልና፡፡ አውጭ አውራጅ ፈጣሪ ነው፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ብትዋረድም፣ ሕዝቧ ወደየዓለሙ ከጽንፍ እስከ አጽናፍ ቢሰደድና በገዛ ሀገሩም የበይ ተመልካች ቢሆንም፣ ይህች ታሪካዊ ሀገር አንገት በሌላቸውና በዱባ ጥጋብ በታወሩ ሞኝና ቂላቂል ጠላቶቿ ለጊዜው የዓለም መሣቂያ፣ መዘባበቺያና መሣለቂያ ብትሆንም፣ በመዝገበ ቃላት ሳይቀር ለርሀብና ለችጋር አስረጅ ምሳሌ ሆና ብትጻፍም አሁን በአግራሞት የምናስተውላቸው  ሁሉም የመጥፎ ገጽታ መገለጫዎቿ በቀደሙ ዘመናት የአሁኑን ያህል ግዘፍ ነስተው እንዳልነበሩ ሁሉ ከቅርብ ጊዜያት በኋላ አይኖሩም ብለን በሙሉ ልብ የምናምን አለን – በይፋ የመናገር ዕድሉን ለጊዜው ብንነፈግም፡፡ የአሁን ችግሮች ተረት ይሆናሉ – በፍጹም ርግጠኝነት፡፡ ግን ወዮ ለነዚያ ለችግሮቿ መንስኤዎች! ‹ለለአሃዱ በበምግባሩ!› እንዲል የጥንቱ መጽሐፍ፡፡ ፍጡር ካለ ፈጣሪ አለ፡፡ ያለ ፈጣሪ የተፈጠረ ነገር እንዳለ የሚያምኑ ማስተዋል የሚጎድላቸው ናቸው – ምናልባትም ጅላጅሎችና ሞኞች – መሆን የሚፈልጉትን ለመሆን ያላቸውን መብት ለመቃረን እንዳልተመኘሁ ይታወቅልኝና፡፡ የፈጠረን ረስቶ የተፈጠረን ፍጡር ያለ ፈጣሪ እንደተፈጠረ በመቁጠር በዕብሪትና በማንአለብኝነት በመሞላት አለፍትህና አላግባብ የሚያንገላታ ዕቡይ ፍጡር ደግሞ ከሁሉም በባሰ ወዮለት! የብልጦችና የመሠሪዎች የዕኩይ ምግባር  ምንዳ ከአስተዋዮችና ከጥበበኞች የመልካም ሥራ ደመወዝ ጋር በተቃርኖኣዊ ተመሳስሎ ተካካይ ነው፡፡

እንግዲህ ምን ቀረ? ምንም! ትንቢቱ ሁሉ ተፈጸመ፡፡ የእምቢልታው መነፋት ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ነገር ወደፍጻሜው እያመራ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ዐውድ የፍጻሜው ጦርነት በማንና በማን እንደሚሆን እንኳን መንግሥት ተቃዋሚም አያውቅም፤ በሌላ አገላለጽ እንኳን ተቃዋሚ መንግሥትም አያውቅም፡፡ ‹ዕንቆቅልህ –  ምን አውቅልህ – ሦስት ሰባት የዘበጠንን ማን ከጫንቃችን ያውርድልን?› መልስ አጠጠ፡፡ ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር!

 

*********************************************************************

አሜን በሉ እስኪ! ልቦናችንን ይግለጥልን፡፡ የውስጥ ዐይናችንን ይክፈትልን፡፡ ያለፈን ካለ፣ የአሁንን ከሚመጣ ጋር እያገናዘብን የትክክለኛ ፍርድ ባለቤቶች እንድንሆን ያድርገን፡፡ ሴከንድ ለማትሞላ ዕድሜያችን ስንል ሚሊዮን ዓመታትን እንደምንኖር  ያህል ውስጣችንን  አሳምኖ ንጹሓን ወገኖቻችንን በተለያዬ መልኩ እንድንበድል የሚገፋፋንን መጥፎ ስሜትና የሥጋ ፍላጎት ፈጣሪ በማይመረመር ጥበቡ ያስወግድልን፡፡ ሰው የመሆን ፍላጎት ያለንን ወገኖች በተለያዩ ውጫዊና ውስጣዊ አስገዳጅ ምክንያቶች የተነሣ ሰው መሆን ሳንችል ቀርተን እንዲሁ ሰው መሆን እንዳማረን እንዳንሞት ፈጣሪ ይርዳንና ሳይውል ሳያድር ሰው ያድርገን፡፡ ሞት ለማንም የማይቀር መሆኑ ግልጽ ቢሆንም ከቁም ሞትና ከዐፅም አስወቃሽ ተደጋጋሚ – ትውልድንም አሣፋሪ –  የሞት ሞት እንዲሠውረን የብርሃን አምላክ – የሰማይና የምድር ፈጣሪ ይጠብቀን፡፡ ከሁሉም ከሁሉም ከመብልና ከመጠጥ ያልተገራ መደዴ ፍላጎት እንዲሁም ገደብ ከሌለው ስድ ወሲባዊነት ይታደገን፡፡ ለሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ጸጸት ተሸክመን በሀፍረት እንዳንሸማቀቅ የሚያስችል ጤናማ ኅሊናን ይስጠን፤ አሜን፡፡

*********************************************************************

Continue reading …

በጋምቤላ ክል  በምስጢር የደኅንነት አባል ሆነው ይሠራሉ የተባሉት አቶ ጌታቸው አንኮሬ ባልታወቁ  ሰዎች  በድንገት  መገደላቸውን  ተከትሎ  ቀደም  ሲል  በክልሉ  የነበረው  ውጥረት  በከፍተኛ  ደረጃ መባባሱ  ተገለጸ።  የክልሉ  ባለሥልጣናትና  ካድሬዎችም  ስጋት ላይ  ወድቀዋል።   Read more…

Continue reading …

የኢትዮጵያም ሆነ የሌላው ዓለም ሁኔታ ሁሉ ግራ እሚያጋባ ሆነና ምን ብዬ እንደምጀምር ግራ ገባኝ፡፡

ሰዎች በባሕርያችን ተስፋ አስቆራጭ ፍጡራን ነን፡፡ በተለይ የአሁኑ ዘመን አብዛኛዎቹ ሰዎችማ ከምን ጊዜውም በበለጠ የክፉ ክፉ እዬሆንን በመምጣታችን እንዲያውም በአረመኔነቱ ከለየለት መጥፎ አውሬ እየባስን መጥተናል ማለት ይቻላል፡፡ ግን ምን ቢነካን ይሆን? ለምንድን ነው ይህን ያህል ለገንዘብና ለሥልጣን አቅላችንን ስተን ሁሉንም የኅሊናና የሃይማኖት አጥሮች ጥሰን ባለ በሌለ ኃይላችን ለሁለንተናዊ ኪሣራ በገዛ ፈቃዳችን የምንጋለጠው? ሰውነታችንን ምን ዓይነት አጋንንት ቢኮናተሩት ይሆን እስከዚህ የሞራልና የጤናማ ሰው ምልክቶችን ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ደምስሰን ለግልና ለቡድን ጥቅም የምንሸነፈው?

     እነዚህ ሥልጣንና ገንዘብ ሰውን የሚያሳውር አንዳች ምትሃታዊ ኃይል አላቸው፡፡ ሰው ገንዘብና ሥልጣን ለማግኘት የማይፈነቅለው ድንጋይ እንዳይኖረው የሆነበት ምክንያት ምንጩ ሰይጣናዊ መሆኑ የምንክደው አይመስለኝም፡፡ ሰይጣን ደግሞ አደገኛ መርዝ ነው፡፡ ሰውን ከሰው ያባላል፤ ያጨራርሳል፡፡ ከሰማይ በታች ከምድር በላይ የማይጠቀመው ዘዴ ወይም ሥልት የለም – የማፋጀት ዓላማውን ለማሣካት፡፡ ዘረኝነት፣ጎሠኝነት፣ቋንቋ፣ የመንደር ልጅነት፣ ሃይማኖት… ዋና ዋናዎቹ የማጨራረሻ መንገዶቹ መሆናቸውን ከኛዋ ምሥኪን ሀገር እውነተኛ የወቅቱ ገጠመኝ ተነስተን የምንረዳው ነው፡፡ ሰይጣን ዓላማው ይሣካለት እንጂ ባህልና ይሉኝታ ብሎ ነገር አያውቅም፡፡ ቄስና ጳጳስ፣ ዲያቆንና መዘምር፣ ነጋዴና ፖለቲከኛ ብሎ ነገርም አያውቅም፡፡ ዓላማውን ያሣኩለት እንጂ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በተለይ ቁንጮ አካባቢ ያሉት የርሱ አጫፋሪዎችና ባለሟሎቹ ናቸው፡፡ ለዚህ ሀገራችን ዋና ምሣሌ ናት፡፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት ሰይጣን እንደልቡ የማይጨፍርበት የአምልኮት ቤትና የባለሥልጣን ቢሮ በሀገራችን የትም ቦታ አይገኝም፤ ከሞላ ጎደል ሁሉም የርሱ አጋፋሪ ሆኗል፡፡ ሁላችንም በእርሱ ግዛት ሥር ወድቀናል ማለት ይቻላል፡፡ ባይሆንማ ኖሮ ቅድስት ሀገራችን በሁሉም መለኪያ የሁሉም ሀገሮች ውራ አትሆንም ነበር፡፡ …

     የሦሪያው አሠድ እሳት(ባሽር አል አሣድ) ሕዝብን በእቶን እሳት መለብለብ ከጀመረ ዓመት ሊሞላው ነው ወይም ሞልቷል፡፡  በየቀኑ እንደቅጠል የሚረግፈው የሕዝብ ሕይወት ለሥልጣኑ አንድ ቀንም ቢሆን ውሎ ማደር እስከጠቀመ ድረስ ደንታው አይደለም – ትልቅ መረገም፤ ለሕዝቡም ለራሱ ለሰውዬውም ለሀገሪቱም፤ ለዓለም ሕዝብ በጠቅላላውም የሀፍረት ምንጭ ነው፡፡ የሌሎች ዓለማት ፍጡራን (ካሉ) በሰዎች አውሬያዊ ባሕርይ እንዲሳቀቁ የሚያደርግ አንዱ ማፈሪያ ልጃችን አሣድ ነው – እርግጥ ነው ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ ፤ ይሠመርበት – ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ፡፡ እንደመለስ ጨካኝና መሠሪ በዓለም የለም፡፡ ይህን ለማረጋገጥ የኢቲቪን የላም አለኝ በሰማይ ተረት ተረት ሣይሆን እውነተኛውን የሕዝብ ኑሮ እዚህ ሀገር ውስጥ መጥቶ መመልከት ነው፡፡ በወያኔ ጨንገር የማይሸነቆጥ ከወያኔ ከራሱ በስተቀር ማንም የለም፡፡ አሁንማ ብሎ ብሎ ሕዝቡ አንዳችም የሚመካበትና ሸጦ ለውጦም የልጆቹን ጉሮሮ የሚዘጋበትን የመጨረሻ አማራጩን ቤቱን እንኳን እንዳያዝዝበት ‹ያንተ አይደለም› ብሎታል፡፡ ይህ ሕግ የአልባኒያ ይሁን የታላቋ ብሪጣንያ ገና አላወቅነውም፡፡ ወያኔ በጉብዝናው እንደቀጠለ ነው፡፡ በአባይ ሰበብም ሕዝቡን በጊንጣዊ ጅራፍ መግረፉንም እንደቀጠለ ነው፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ድሃን አልይ ብሎ የጥቂቶች ከተማ ለማድረግ ቀን ከሌት ደፋ ቀና ማለቱንም እንደቀጠለ ነው፡፡ በቃላት መግለጽ በሚከብድ የኑሮ ውድነት ጅራፍ ወያኔ ያልሆነን የሕዝብ ክፍል መቀጥቀጡንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ወያኔ ጀግናው እንደጆን ወከር – እንደ ‹ዮሐንስ ተራማጁ› በ‹still going strong› መርሁ መራመዱን እንደቀጠለ ነው፡፡ ያልተመለሰና ለመመለስ ያስቸገረን ጥያቄ ግን ‹ እስከማዕዜኑ?› – እስከመቼ – የሚለው ጥያቄ ነው – ለጊዜው፡፡

     ሰው የሚመስሉ በሰው አምሳል እንደምንም ቤተ መንግሥት ገብተው ሲያበቁ የሰውነት መገለጫ ማስመሰያ ለምዳቸውን አውልቀው የአውሬነት ባሕርያቸውን የሚላበሱና ሀፍረትና ይሉኝታን ቸብችበው ሸጠው የበሉ ሥልጣንን ሙጭጭ ብለው የቀሩ የአጋንንት ውላጆችን ብዛት የዓለም ሀገሮች አብያተ መንግሥት ይቁጠሩት፡፡ እያንዳንዳቸውን ከነጉድፋቸው እንዘርዝር ብንል ውለን እናድራለን፡፡ የሰሞኑን የሴኔጋሉን ሰውዬ እንኳን ብናይ ከማንምና ከምንም ሊማር ያልቻለ ደደብና የገልቱ ገልቱ መሆኑን እንገነዘባለን – የዚያኛውን ሰሞን የኮት ዲቯሩን የሎራን ባግቦን ቅሌት ሳንዘነጋ፡፡ ሕገ መንግሥቱ አንድ ሰው ከሁለት ዙር በላይ ለመሪነት መወዳደር አይችልም ብሎ የደነገገውን ልክ እንደቬንዝዌላው አምባገነን ሁጎ ሻቬዝ በቀጭን ትዕዛዝ በፍርድ ቤት አስለውጦ ለሦስተኛ ጊዜ እንዲወዳደር የሚያስችል አዲስ ሕግ በሕገ መንግሥቱ እንዲሰነቀር በማድረጉ አመጽ እየተቀሰቀሰ ነው፡፡ በውነት ግን ሰዎች ምን ነካን?

     የኛው ጉድ መለስም ዓለምን ለማጭበርበር እየሞከረ የቤን አሊን የሥልጣን ዕድሜ ሊደርስ የቀረው ጊዜ ጥቂት ነው፡፡ ዓለም የአጭበርባሪዎች ናት፡፡ ዓለም የሌቦች ናት፡፡ መልካም ሰዎች በዚህች ዓለም ሥፍራ የላቸውም፤ ካላቸውም ያ ጊዜ አልፏል ወይም ገና አልመጣም፡፡ የጋናው ጸሐፊ አይ ኪው አርማህ ‹ቆንጆዎቹ ገና አልተወለዱም› እንዳለው ነው ነገሩ በጅምላው ፡፡ …

     ኢትዮጵያ ውስጥ አራት ኪሎ ላይ የተገሸረው የወያኔ መንጋ በሕዝብ ላይ እንደተጸዳዳ ይሄውና ሃያ አንድ ዓመታትን ሊያስቆጥር የቀሩት በአንድ ዕጅ ጣቶች የሚቆጠሩ ጥቂት ወራት ብቻ ናቸው፡፡ ይህን የወሮበሎች የጥፋት መንጋ ከአራት ኪሎ ለማስወጣት እስካሁን ዝምቡን እሽ ያለው የለም – ‹ነጻ አውጪው› ሁሉ እርስ በርሱ ይፈሳፈስ ወይንስ የጋራ ጠላትን ለማ‘ቸ’ነፍ በኅብረት ይቁም፤ ጉድ እኮ ነው ‹በሬው ሳይገዛ ሌባው በረት ሞላ›አሉ? በርግጥ ግን ምን ነካን? ወዴትስ እያመራን ይሆን? የመማሪያ የሰውነት ክፍላችን ጭራሹን ሥራ አቆመ ይሆን? ተስፋ የቆረጠው ወገን በ‹ሀገር ሲወረር አብረህ ውረር› የቆዬ የሆዳሞች መመሪያ መሠረት ከወያኔ ጋር እየተሻረከ በፖለቲካው፣ በሃይማኖቱና በንግዱ ዘርፍ ሕዝቡንና ሀገሪቱን መቦጥቦጡን ቀጥሏል፡፡ በዚያም ሳቢያ በሀብታሙና በድሃው መካከል ያለውን ርቀት ለመሥፈር ዓለም ከደረሰችበት የልኬት መጠን ማወቂያ መሣሪያ አቅም በላይ ሆኖኣል፡፡ በአዲስ አበባ በሚሊዮን የሚገመት ድሃ በጥቂት ሺዎች ከሚቆጠሩ የናጠጡ ሀብታሞች ቤት የሚጣለውን ቆሻሻ – ከሰውነት ተራ ወርዶ –  አንዳች የሚቀመስ ፍርፋሪ ወይም የሙዝ ልጣጭ ለማግኘት በየቆሻሻ ገንዳው እንደዝንብ ሲርመሰመስ ስታዩ ኢትዮጵያዊነት ላይ የወረደው መቅሰፍት ያስለቅሳችኋል – የርህራሄ መንፈሳችሁ እንደሀብታሞቻችን ተሟጦ ካላለቀ፡፡ ሀብታሙ አእምሮውን አጥቷል፤ ድህነቱም ቅጥ አጥቷል፡፡ የምፅዓት ጊዜ የተቃረበ ይመስላል…፡፡ ለማንኛውም ግመሊቱ እየተጓዘች ነው፤ ውሾቹም እየተከተሉ ናቸው፡፡ አሁንም ‹እስከመቼ?› ለሚለው ጥያቄ መልሱን ጊዜ ባለውሉ እስኪሰጥ ድረስ መጠበቅ ብቻ ነው፡፡ አንድ እውነት ግን አለ፤ ያም እውነት ሁሉም የክፋት ስንቅ የሚያልቅ መሆኑ ነው፡፡ እናም ወያኔዎች ያማረባቸው ወቅት እንደነበረና እንዳለም ሁሉ እንደቢጤዎቻቸው እንደነጋዳፊና እንደነሂትለር መቃብሩ ተቆፍሮ እንደሚጠባበቀው እንደአሣድም ጀምበር ስትጠልቅባቸው የሚሆኑትን መሆን ዕድሜ የሰጠው የሚያየው ይሆናል፡፡ ይህን እውነት ለመናገር ነቢይነትን አይጠይቅም፡፡ የታሪክን አካሄድ ብቻ ማጤን ይበቃል፡፡ ብሂሉ ‹ከተራበ ለጠገበ አዝናለሁ› እንዲል የምናሳዝን እኛ ድሆችና ምንዱባን ሳንሆን ያደርጉትን አጥተው በገዛ ሀገራችን የተዋራጅ ተዋራጅ ያደረጉን ጥጋበኞቹ ናቸው፡፡ እኛማ …

     እሳት ላይ የተጣደን ውኃ ወይም ወተት በምናባችሁ አስቡ፡፡ በቅድሚያ ለስ ይላል፤ ሂደቱ ይቀጥላል – ይሞቃል፤ ይፍለቀለቃል፤ ይንተከተካል፤ በመጨረሻም ይገነፍላል – በዚህ ሂደት የሚተንም አለ – እሚገባበት እማይታወቅ፡፡ የገነፈለን ወተት ደግሞ ማቆም የሚቻለው አንድም ኃይል የለም፡፡ እርግጥ ነው ያቺን ወተቱ የሚፍለቀለቅባትን ወይም የሚገነፍልባትን ቅጽበት ለይቶ ማወቅ ይገባል፤ ግን እሱም ከባድ ነው – ማወቅ ያስቸግራል፡፡ ከዓለም የማኅበራዊ ሣይንስ ሊቃውንት መካከል አንዲት ምሁር ባደረጉት አንድ ቀደም ያለ ጥናት መሠረት በአንድ ሀገር ሕዝባዊ አመጽ ሊያስነሱና ያለውን መንግሥት ሊጥሉ የሚችሉ ቅድመ ሁኔታዎች በሀገራችን ከተሟሉ በጥቂቱ 30 ዓመታት አልፈዋል፡፡ ይህ ኢትዮጵያ ላይ ሲደርስ ከተጠቀሰው ጥናት ያፈነገጠ ሁኔታ አንዳንዶቻችንን ሊያስደነግጥ ሊያስበረግግም ቢችል አይገርምም፡፡ ያም ሁኔታ ለገዢዎች የልብ ልብ እየሰጠ ይበልጥ እንዲጋልቡን በር መክፈቱን ብንጠራጠር አይፈረድብንም፡፡ እውነቱ ግን በባህላዊው አገላለጽ ‹በቅሎ ገመዷን በጠሰች› ቢባል ‹ ማሠሪያዋን አሣጠረች› እንዲሉ ዓይነት ነው፡፡ የሦሪያና የሊቢያ ሕዝብ ከዐርባ ዓመታት በኋላ ከእንቅልፉ ነቅቶ ምን እንደሠራ የምንታዘብ ወገኖች ወያኔ ይዋል ይደር እንጂ በሠፈረው ቁና ዕጥፍ ድርብ እንደሚሠፈረው ቅንጣት መጠራጠር አይገባም፡፡ የገዢዎች የአገዛዝ ሥልት በጣም ተለዋዋጭና ከዓለም ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እየተገነዛበ እዬዘመነ የሚሄድም ነው፡፡ ገዢዎች በመሠረቱ የማይጠቀሙት ዘዴ የለም፤ ኮከብ ቆጣሪና መጣፍ ገላጭም ጭምር ሊጠቀሙ ይችላሉ – የፖለቲካ አሰለጦቻቸው ከሚሰጧቸው ሸር የተሞላበት የምክር አግልግሎት በተጨማሪ፡፡ ይሁንና ትብታብም በሉት አፍዝ አደንግዝ ወይም የሸረኞች ምክር የሚሠራበትና የማይሠራበት አቡሻክርና አበቅቴ አለ፡፡ ሁል ጊዜ ፋሲካ የለም፡፡ እነሱ ይህን እውነት ቢጠራጠሩ ወይም ለማመን ባይፈልጉ ሞራና ስብ አንጎላቸውን ስለደፈነው ሊሆን ይችላልና አይደንቅም፤ የሥልጣንና የገንዘብ ሱስ ዐይንን ይጋርዳል፤ የኀሊናን ጓዳ ያጨልማል፤ ማሰቢያ አካልን ከነአካቴው ከሥራ ውጪ ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ በወያኔ ብቻ የተወሰነ ሣይሆን ሊወድቅ አንድ ሐሙስ በቀረው በሦርያው የሕዳጣኑ ነገድ ተወካይ በአሣድም እያስተዋልነው ነው፡፡ ‹መብሰሉ ላይቀር ጭንቅላት ብዙ እሳት ይፈጃል› ይባላል፡፡ ሌላም አለ፤‹ ይዋል ይደር እንጂ አህያ የጅብ ናት› የሚል፡፡ ከዚህ ነባራዊ እውነታ አንድም ሰው አንድም መንግሥት አንድም ምድራዊ ተቋም ነጻ ሊሆን አይቻለውም፡፡ የሥራን ማግኘት ከፍትህ አምላክ ከፈጣሪ የሚላክ እንጂ እኔና አንተ በፈቃዳችን የምናስገኘው ሰብኣዊ ስጦታ ወይም ችሮታ አይደለም፡፡ ወያኔ አሁን ሊፈነጥዝ ይችላል፤ ለቀጣቹ ሃያና ሠላሣ ዓመታትም እንዲሁ ጮቤ እየረገጠ ሀገርንና ሕዝብን እንዳሁኑ በሲዖላዊ ጨካኝ አገዛዝ አፍኖ ሊያሰቃይ ይችላል፡፡ የማያመልጠው የታሪክና የፈጣሪ ዕዳ ግን በልጆቹም ቢሆን የማያጣው ጨካኝ ተፈጥሮው የሚያስከፍለውን ውድ ዋጋ ነው፡፡ እንዴ – የአሣድ አባት ሀፌዝ አላሣድ እኮ አሁን በመቃብሩ ውስጥ አጥንቱ እየተገላበጠ ነው – ልጁን ለማገዝ እዬፈለገ ግን በፈጣሪ ዕጅ ተይዞ ሥጋው ትቢያ ነፍሱም የጀሃነብ ምርኮኛ ሆነውበት፡፡ ይህን መሠረታዊ ዕውቀት እኮ ነው አምባገነኖች የተነጠቁት፤ ይህን ሰው በዚች ምድር የሚያብብበት፣ የሚያፈራበት፣ የሚጀግንበት፣ የሚገንበትና የሚዋረድበት ዘመን ኢምንት መሆኑን መርሳት እኮ ነው የአምባገነኖች ትልቁ ያለማስተዋል በሽታ፡፡ ለመሆኑ አንድ ሰው ሌላውን ሰው ቢያሰቃይ ምን ይጠቀማል? የደስታው እርዝማኔና ዘላቂ ውጤቱስ ምንድነው? አንድ መቶ ዓመት እንኳን በሕይወት  ሊኖር የማይቻለው ይህ ደካማ ፍጡር – ሰው – ለቅጽበታዊ መናኛ ዕድሎች እየተንበረከከ በወገኖቹ ላይ መከራና ሰቆቃ የሚያዘንበው ምን ሊጠቀም ይሆን? ሰውን ምን ነካው? እንዴት ከቀሪው የእንስሳት ዓለም ይነስ? እርግቦች በእርግብነታቸው፣ ከብቶች በከብትነታቸው፣ ድመቶች በድመትነታቸው… ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ሲቀራረቡ እኛ ሰው የመሆናችን የጋራ ተፈጥሮ ሳያንሰን እንዴት በግንባር ላይ ምልክቶችና በልሣናዊ የመግባቢያ መሣሪያ ላይ ተመርኩዘን አንዱን እናቀርባለን ሌላውን እናርቃለን? ይሁን፤ ማቅረብ ማራቁ ግዴለም፡፡ ከሰውነት ተራ በወረደ መጥፎ ጠባይ ተለክፈን ዘራችን የምንለውን ልዩ ሥልጣንና ጥቅም እንዲያገኝ ስናደርግ ሌላውንና የጥቅማችን ተቀናቃኝ ነው ብለን የፈረጅነውን ሰው ሰበብ አስባብ እዬፈለግን ከሥራውና ከኑሮው የምናፈናቅለው፣ ሰላማዊ ኑሮውን የምናዛንፈው ለእሥርና ለእንግልት ለስደትና ለሞት ለድህነትና ለባርነት ኑሮ የምናጋልጠው ለምንድነው? ለዚህ ወንጀላችንስ ሰው ዋጋችንን ባይሰጠን ለይምሰል በሰው ፊት ስሙን የምናነሳውና የውሻን ደም ሳይቀር በከንቱ የማያስቀረው ፈጣሪስ ዝም ብሎ ያልፈናል ወይ? ከየት የመጣብን ድንቁርና ነው? በእውኑ ሰዎች ምን ነካን? ክፉ ደስታ አንጎልን መደፍጠጥ አለበት ወይ? ኧረ ትንሽም ብትሆን ጊዜ ካለችን በዚህ ጉዳይ መጨነቅና ማሰብ የሚገባን ወገኖች ቆም ብለን እናስብበት፡፡ (ለምለው ነገር የኢትዮጵያን የፖለቲካና የሃይማኖት የሹመት አሰጣጥና የሀገሪቱን አጠቃላይ ወቅታዊ የሀብት ክፍፍል ልብ ብለው ያጤኗል፤ ዝርዝር ኪስ የቀዳል፡፡)

     የወያኔ ባንክን ያስጨነቀ ገንዘብ፣ የወያኔ አዲስ አበባን ያጨናነቀ የንግድና የመኖሪያ ሕንጻ፣ የወያኔ ከድሃው ሕዝብ በየምክንያቱ የተመዘበረ ሀብትና ንብረት ለወያኔ ምን ይጠቅማል? 80 ሚሊዮን ሕዝብ በማስጨነቅና መቅኖ በማሣጣት የተገኘ ሥልጣንና ሀብት እስከመቼ ይቆያል? የጋዳፊ በቢሊዮን – ከዚያም በላይ – የሚቆጠር ዶላር በመጨረሻው መጨረሻ ላይ ገና ሳይሞት በመቀመጫው ሣንጃ ሲከቱበት ምን ረዳው? መለስና ቢጤዎቹ የዓለም ደናቁርት መሪዎች ከነዚህ በነጻ ከሚገኙ ትምህርቶች – ሣንቲም ሳይከፍሉ እንዲሁ በብላሽ -  መማር እንዴት ተሣናቸው? ምናልባት የኛ ኃጢያት መብዛት? ጠርጥሩ፤ ቆሻሻ ቆሻሻን የማጽዳት የሞራል ብቃት የለውም፡፡ ‹ብዔል ዘቡል ብዔል ዘቡልን አያወጣም› እንዲል መጽሐፉ፡፡ ስለዚህ ራሳችንንም እንፈትሽ፡፡ ሰውን ስናስጠነቅቅ ከሌባ ጣታችን በመለስ ሦስቱ ጣቶች ወደኛ መዞራቸውን ልብ እንበል፡፡ የኛ የገረረ ልቦና፣ የኛ የተበከለ አስተሳሰብ፣ የኛ የተንሸዋረረ አመለካከት፣ የኛ የቆሸሸ ስብዕና፣ የኛ ፍትሀ አልባነት፣ የኛ መጥፎ ምግባር፣ የኛ ብዙ ነገር… ለወያኔ ተመቻችቶ መቀመጥ ዓይነተኛ ግብኣት ነው፡፡ እንዲያ ባይሆን ከአምሥት የማይበልጡ አጋሚዶዎች እንዲህ ባልተዘባነኑብን ነበር፡፡ ‹ትግል ከራስ› ብላለች ድምጻዊት አሥር አለቃ ውቢሻሽ በ‹ከቆራጡ መሪ…› አልበሟ- ያኔ ጥንት፡፡

     ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም፡፡ ጥቂት ነገር ልበልና ላብቃ፡፡ አዲስ አበባ እየተንተከተከች ናት፡፡ ትዕዛዝ እንደሚጠባበቅ ሠራዊት በተጠንቀቅ ላይ ትገኛለች፡፡ ትዕዛዙ ከፈጣሪ ነው፡፡ መጽሐፉ እንዲህ ይላል፤ ‹ ኢድኅን ንጉሥ በብዝኃ ሠራዊቱ›፡፡ አዎ፤ በዕጃችን የያዝናት ብርጭቆ መቼም የምትሰበር አትመስለን ይሆናል፤ በሰውነታችን የያዝነው የጤንነት ፀጋ መቼም የሚከዳን አይመስለን ይሆናል፤ ያለን የሚመስለን ጥንካሬ እስከወዲያኛው የማይለየን ሊመስለን ይችላል፤ የምናምናቸው ሰዎች – አሽከሮችና ደንገጡሮች እስከዝንተዓለሙ እንደታመኑ የሚዘልቁ ሊመስለን ይችላል፡፡ ነገር ግን ጊዜ ባለውሉ ዘመም ሲል ሁሉም የእንቧይ ካብ ይሆንና ሰማይ ምድር ይደፉብናል፡፡ ያኔ ስህተትን ለማስተካከል ፍላጎቱ ቢኖረንም እንኳ ዕድሉ ላይኖረን ይችላል፡፡ ከመነሻው ማስተዋልን የተነጠቀ ሰው ደግሞ በመጨረሻው በከንቱ ቢጮህ የሚያዝንለትም ሆነ የሚደርስለት አይኖርም፡፡ ታሪክ እሚያስተምረን ይህንን ነው፡፡

     ሌሎች ለሥልጣንና ለሀብት ያቆበቆብን አለን፡፡ ወጡ ሳይወጠወጥ የባሕርይ አባታችን ዲያቢሎስ ገና ምኑም ሳይያዝ በሰውነታችን ገብቶ እያቅነዘነዘን የምንገኝ ወገኖች በርካቶች ነን፡፡ ሕዝቡን ከአንዱ የመከራ ጫፍ ወደሌላ የመከራ ጫፍ ለመክተት ሌት ከቀን የምንፍጨረጨር በረትንም የምናምስ አለን – በዉጭም በሀገር ውስጥም፡፡ ከአበራሽ ጠባሣ ላለመማር ምለን የተገዘትን በየአጥቢያው ሞልተናል፡፡ ያ ዓይነቱ የደካሞችና የልቦናና የኅሊና ሥውራን ዕኩይ ተግባርም ነው ከኃጢያታችንና ብልሹ ምግባራችን ጋር ተዳምሮ የነጻነት ጊዜያችንን እያዘገየብን ያለው፡፡ እንጂ ወያኔ አንድም ኃይልና ሀገር የማስተዳደር ብቃትና ችሎታ ኖሮት እንዳልሆነ ልንረዳ ይገባል፡፡ የነጻነት ኃይላት በሚባሉ ወገኖች ሥውር ጠላቶችና ከፋፋዮች በማስረግ ዕድሜውን እንዲረዘም የምናደርግ የጠላት ሕቡዕና ግልጽ ተላላኪዎች ሞልተናል፡፡ ይህም ጊዜው ባለመድረሱ እንጂ የወያኔም ሆነ የቡችሎቹ ጥንካሬ ወይም ዘዴና ብልሃት አይሎ መገኘት አይደለም – በጭራሽ!…

     በአንዲት ሰሞነኛ ቀልድ ልለይ – አንዱ ነው በቀደምለት የነገረኝ – በፌስ ቡክ የተላከልኝ ብሎ፡፡ ያልሰማችሁ ፈገግ ለማለት ሞክሩ፡፡

     መለስ፣ ባለቤቱ አዜብና ልጁ ሰምሃል በአውሮፕላን ተሣፍረው እዬሄዱ ነው – ወደመቀሌ፡፡ በወሎና ሸዋ ድንበር አካባቢ ሲደርሱ መለስ ‹ የኢትዮጵያ ሕዝብ መቼም ከችግርና ከችጋር አይወጣም – አንድ መቶ ብር ቁልቄል ልወርውርና አንዱን ኢትዮጵያዊ ላስደስተው› ይላል፡፡ ሚስቱ አዜብ ቀበል ታደርግና ‹እንደሱ ካሰብክስ ለምን መቶውን ብራ ለሁለት ሰንጥቀህ አምሳ አምሳውን በመወርወር ሁለት ኢትዮጵያውያንን አታስደስትም› ትለዋለች፡፡ ልጂት ሰምሃል ደግሞ የተሻለ ነው የምትለውን ሃሳብ ‹ አባዬ፣ ያንተም የእማዬም ሃሳብ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን አንድ ወይም ሁለት ሰው ከምታስደስት ለምን መቶውን ብር በአሥር ቦታ ዘርዝረኸው አሥር አሥር ብር በመላክ አሥር ሰዎችን አታስደስትም?› ትላለች፡፡ እንዲህ ሲባባሉ በጥሞና ሲከታተል የነበረው ፓይለት ደግሞ መስኮቱን ከፈት ያደርግና ‹ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ሃሳብዎ ቆንጆ ነው፡፡ ነገር ግን አንድ ወይም ሁለት ሰው ወይም አሥር ሰዎችን ከማስደሰት እርስዎ ራስዎ ወደመሬት ተወርውረው 80 ሚሊዮኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሞላ ለምን አያስደስቱም?› በማለት የተለዬ አስታራቂ ሃሳብ ያቀርባል፡፡ ጨቅላ ማለቴ ጠቅላይ ሚንስትሩ ይወርወር አይወርወር ቲቪ ስለሌለኝ እስካሁን አላወቅሁም፡፡ ግን ልብ ይስጠው እንጂ ለምን ይወርወርብን? በየጊዜው ሰው እያጣች የመጣች ሀገራችን  ለምን የሀዘን ማቅ ትልበስ? የነአብዱል መጂድን፣ የነክፍሌ ወዳጆን፣ የነክንፈን፣ የነአሰፋ ማሞን፣ የነወይዘሮ አለማሽን፣ የነአቦይ ዜናዊን… ሀዘን በቅጡ ሳንወጣ ለምን ትልቅ የሀገር ሀብት ሊያውም ከአውሮፕላን ይፈጥፈጥብን? የምቀኛ ጆሮ ይደፈን፡፡

Continue reading …

ፖለቲካ በሁለት መሰረቶች ላይ የቆመ ሲሆን አንዱ ዶግማ ሌላኛው ደሞ ቀኖና ነው። ዶግማው ምን ጊዜም ኣይለወጥም። ዘመን ኣልፎ ዘምን ሲተካ ትውልድ ኣልፎ ትልድ ሲተካ ለሁል ጊዜም ይኖራል። የፖለቲካ ድርጅቶችም የሚሞቱለት ጉዳይ ቢኖር ይሄ ነው። ፍትሕ ዴሞክራሲ ነጻነት ለምሳሌ ዶግማዎች ናቸው።

ኣንድ ድርጅት ሲቆም ቀኖናዎችም ኣሉት። እነዚህ ቀኖናዎች የድርጅቶቻችን የትግል ስልቶች ወይም ሌሎች ግባቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ቀኖና ናቸው እና አንደ ሁኔታው ዘመን ሊለውጣቸው ይችላል። ይሁን እንጂ ኣንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች ቀኖናውንም ዶግማውንም ኣደባልቀው ዘመን ሲለወጥ ኣንለወጥም ብለው ችክ በማለታቸው ከቆሙለት ህዝብ ይፋታሉ። ደሞም ካሰቡት ለመድረስ ሳይችሉ ይቀራሉ።

ፖለቲካ የሰው ልጅን ገስጋሽ የሆነ ኣመለካከት ስራዬ ብሎ ተክትሎ የሚሄድ ጥበብ ነው።በቅርቡ ከኦነግ የወጣው መግለጫ የሚያሳየው የኦነግ መሪዎች ምን ያህል ከግል ፍላጎት እና ከግትርነት በላይ የኢትዮጵያዊያንን መከራ ለማሳጠር የቆረጡ ኣገር ወዳድ ጀግኖች መሆናቸውን ነው።

ለነነገሩ ድሮም ቢሆን የመገንጠል ጥያቄ የኦነግ ዶግማው ሳይሆን ቀኖናው ነበር። ይህ ቀኖና ደሞ ለተባለው ዋና ኣላማ ማለትም ለነጻነት ለፍትሕ ና ለዴሞክራሲ መስፈን አንደ መንገድ (means) ይሆናል ከሚል ስሜት የመጣ ነበር ። ይህ የትግል ስልት ግን ለኦሮሞ ህዝብ የሁዋላ ዴሞክራሲ ና ፍትሕ በፍጹም ዋስትና እንደሌለው ኦነግ ኣጥብቆ የተረዳ ለመሆኑ የበቀደሙ መግለጫ ያሳያል። የኦነግ መሪዎች በወሰዱት ርምጃ ሁሉን ኢትዮጵያዊ የሚያኮራ እነዚህን መሪዎችም በለቀ የሞራል እሴት ላይ የሚሰይማቸው ተግባር ነው።

የዚህ የኦነግ ሃላፊነት እና ብስለት የተመላበተ ውሳኔ በሃገራችን የነጻነት ትግል ላይ የሚከተሉት ኣዎንታዊ ተጽዕኖዎች ያሳርፋል የሚል እምነት ያሳድርብናል

፩) ሌሎች ዘውግ ተኮር የሆኑ ድርጅቶችን ያነቃል
በሃገራችን ወስጥ በነጻነት እጦት ሆድ ብሶት ለሚታገለው ኦብነግ የዚህ የኦነግ ያቁዋም ለውጥ ይነሽጠዋል የሚሉ ኢትዮጵያዊያን ኣያሌ ይሆናሉ። ኣብነግ ልክ አንደ ኦነግ ኣካሄዱን ኣይቶ ና ቀኖናውን ሽሮ ለመላው ኢትዮጵያውያን ነጻነት እኔም አንደ ኦነግ የሚልበትን የሞራል ስንቅ ከኦነግ ኣግኝቱዋል።በኣጠቃላይ የኦነግ የኣስተሳሰብ ተሃድሶ ትልቅ ትምህርትን ለመላው ኢትዮጵያዊ ኣስተላልፏል።

፪)በተራ ዜጎች መካከል መተማመንን ና ፍቅርን ያዳብራል
ፖለቲካ ከዘውግ ጋር ተጣብቆ ሲመጣ በተራ ዜጎች መካከል የስነ ልቡና ክፍተት መፍጠሩ ኣይካድም።በተለይም የፖለቲካ ድርጅቶች ጫፍ ሄደው እስከ መገንጠል ሲመኙ በዜጎች መካከል ያንድነት ስሜት እየኮሰሰ በዚያው ልክ የመለየት ስሜት እያደገ መምጣቱ ኣይቀሬ ነው። የኦሮሞ ህዝብ ከተቀበለው ግፍና በደል የተነሳ ለኔ መብት የቆመ ስቃዬ የተሰማው ብሎ ያመነው ባንጻራዊነት ኦነግን ነው ብሎ መናገር ይቻላል። ይሁን እንጂ ኦነግ የኦሮሞን ህዝብ ነጻነት ለማምጣት የሚሄድበት የነበረው የመገንጠል ጥያቄ ጉዳይ ግን የኦሮሞ ህዝብ መንገድ ነበር ማለት ኣይቻልም። የኦሮሞ ህዝብ የነፍሱ ጥያቄ የነጻነት እንጂ የኦነግ የመገንጠል ኣጀንዳ በኦሮሞው ዘንድ የከበረ ጥያቄ ኣልነበረም በመሆኑም ኦነግ ከመቸውም የበለጠ ዛሬ በኦሮሞዎች ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል። በፊት የነበረውን የህዝቡን ስጋት ሁሉ ኣውጥቶ የሚጥል፤ሃላፊነት የተሞላበት ቸርነት ያለበት ዉሳኔ በመሆኑ የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ ጋር በመተማመን ቁጭ ብሎ የሚጫወተው የሚጋራው ብስራት ነው

፫) ብሄራዊ ስሜታችንን ለመጠበቅ ለምናደርገው ትግል ኣዎንታዊ ኣስተዋጾ ኣለው
በዚህ ዘመን ኣገራችንን የገጠማት ፈተና የነጻነት ጉዳይ ብቻ ኣይደለም። ገዢው መንግስት ብሄራዊ ስሜትን እያንኳሰሰ ልዩነትን እያሰፋ በመሄድ ነው በስልጣን መቆየት የሚቻል የሚመስለው። በዚህ ላይ ላለፉት ሃያ ኣመታት ሲሰራ ነው የቆየው። ታዲያ ይህን ስሜት የምንዋጋው ዜጎች የኣንድነት ስሜታችንን በመንከባከብ ኢትዮጵያዊነትንን በመንከባከብ ነው። የዚህ የ ኦነግ ኣቋም ለብሄራዊ ስሜታችን መነሳሳት (revival) የራሱ ኣዎንታዊ ኣስተዋጻኦ ኣለው።

ደሞ ቸር ያሰማን

ገለታው ዘለቀ
geletawzeleke@gmail.com

Continue reading …
[caption id="attachment_11841" align="aligncenter" width="600" caption="OLF Meeting - Kelly Inn Saint Paul Hotel"][/caption]

 በሄኖክ አለማየሁ /zehabesha.com

ለአንድ ለሁለት ሳምንታት ጋብ ብሎ ባልተለመደ መልኩ ጠፍቶ የነበረው የሚኒሶታ በረዶ ትናንት ማምሻውን አዲስ ዓመትን እየተቀበልን ባለበት ሰዓት መስታወት የመሰለ በረዶ ጥሎ ከተማዋን ነጭ በነጭ አድርጓታል። ነጭ ደግሞ የሰላም፣ የደስታና የአንድነት መግለጫ ነው። የኦሮሞ ነጻነት ግንባርም በሚኒሶታ ከኢትዮጵያውያን ጋር ባደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ ታሪካዊ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ አዲሱን ዓመት ልክ እንደሚኒሶታ አየር ጠባይ በነጭ እንድንቀበለው አድርጓል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከሕዝብ ጋር ለመወያየት በጠራው ስብሰባ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በቪዲዮ ጄነራል ጀማል ገልቹ ነበሩ። ጄነራሉ ንግግራቸውን የጀመሩት እስካሁን በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስር ሆነው ለታገሉና ለተሰው ታጋዮች ያላቸውን አክብሮት በመግለጽ ግንባሩ እስካሁን ያደረገውን የትግል እንቅስቃሴ መርምረዋል።

ከዛም በኋላ በአሁኑ ወቅት ኦነግ ኢትዮጵያዊነቱን ተቀብሎ ለመታገል ለምን እንደወሰነ ለተሰብሳቢው አስረድተዋል። ጀነራል ከማል “እስካሁን ድረስ የኦሮሞ ሕዝብ ሲነገረው የነበረው ትክክል አልነበረም። አሁን ግን እውነቱን እየነገርነው ነው። ድሮ የኦሮሞን ሕዝብ ኢትዮጵያዊ አይደለህም እየተባለ ነበር። እውነቱ ግን የኦሮሞ ሕዝብ የኢትዮጵያ ግንድ ነው። እንዴት ነው ግንድ ከሆነበት የሚገነጠለው? “ ሲሉ ንግግራቸውን ቀጥለው “በአዲሱ የትግል አቅጣጫ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር እንታገላለን። ኦነግ አሁን ይህንን አዲስ የትግል አቅጣጫ የቀየሰው ዘመኑንና የዚህን ትውልድ አመላለከትና ተጨባጭ ሁኔታዎችን በመገንዘብ ነው” ያሉት ጄነራል ከማል ገልቹ “ትግላችን ኢትዮጵያን ለመምራት ሳይሆን የኢትዮጵያን ሲስተም በተሻለ ሲስተም መቀየር ነው” በማለት አሁን ያለውን የውሸት የወያኔ ፌደራሊዝም ወደተሻለ ፌዴራሊዝም መቀየር ነው አላማችን ብለዋል።

“ሕዝቦች እየተጨቆኑ ነው፤ ተከፋፍለን መታገል የወያኔን ዕድሜ ማራዘም ነው” ያሉት ጀነራሉ “አዲስ እውነተኛ ዲሞክራሲያዊት ሃገር ኢትዮጵያን ለመገንባትና በጋራና በእኩልነት ለመኖር የአድነት ግንባር እንፍጠር” በማለት በሃገር ቤትም ሆነ በውጭ ሃገር የሚገኙ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተባብሮ ለአንድ ኢትዮጵያ የሚታገሉበትን ጥሪ አቅርበዋል። በዚህም ወቅት አዳራሹ በጭብጨባ ናኝቷል።

በስብሰባው ላይ የተገኙ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ኢትዮጵያውያን አሁን ኦነግ በወሰደው አቋም እጅጉን መደሰታቸውን በመግለጽ “የኦሮሞ ባህላችን እና ቋንቋችን እስከተከበረ ድረስ እነዚህን መሪዎቻችንን ያመጡልንን ቅዱስ ሃሳብ ልንቀበል ይገባል” የሚሉ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። በመድረኩም በኦነግ አዲሱ የትግል አቅጣጫ ዙሪያ ጥያቄዎች ቀርበዋል። ከነዚህም መካከል በተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተመስርቶ ስለነበረው ኤኤፍ ዲ፤ ከግንቦት ሰባት ጋር አብሮ ስለመሰራት፤ እንደዚሁም ስለሌሎች በርከት ያሉ ጉዳዮችና ስለአዲሱ የኦነግ የትግል አቅጣጫ ጥያቄዎች ቀርበው መድረኩን ሲመሩ ከነበሩት የኦነግ የማ ዕከላዊ ኮሚቴ አመራር አባል አቶ ተማም ባቲ እና ከድርጅቱ ዋና ጸሃፊ አቶ አሚን ጁዲ ምላሽ ተስጥተዋል።

“የኦነግ የትግል ዓላማ መመሪያ እንጂ መተዳደሪያ አይደለም። መተዳደሪያውን የሚመርጠው ሕዝብ ነው።” ያሉት አቶ ተማም ባቲ “በኢትዮጵያ መልካም አስተዳደርን ለመፍጠር ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አብረን እንሰራለን። አሁን ያለው ስርዓት የብሄር ብሄረሰቦችን መብት እያስከበርኩ ነው ቢልም ውሸት ነው። ትክክለኛውን የሕዝቦች መብት ለማስከበር መነሳትና በአዲስ ሃሳብ አንድ ሆነን እንታገላለን” ብለዋል።

የግንባሩ ዋና ጸሃፊ አቶ አሚን ጁዲ “እስካሁን ድረስ ከማንም ጋር ግንባር አልፈጠርንም። ግን የራሳችንን ፕሮግራም ስንቀርጽ ነበር የቆየነው። ይህንን ዛሬ የወሰድነውን አቋም ማንንም ለማስደሰት ስንል አይደለም የወሰድነው። ለኢትዮጵያ መልካም አስተዳደር ያስፈልጋታል፤ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት እንደወያኔ የውሸት ሳይሆን በትክክል የሚያስከብር ስርዓት መፈጠር ስላለበት ነው ይህንን ውሳኔ የወሰንነው።” በማለት አሁን ኦነግ የወሰደውን አዲስ አቋም አስረድተዋል።

“አሁን ያለው የወያኔ ፌደራሊዝም የኦሮሞን ሕዝብም ሆነ የሌላውን ሕዝብ መብት እያስከበረ አይደለም። አሁን ያለው ሲስተም በየሁለት ዓመቱ ጁነዲን እየተባረረ፣ አባዱላ እየተተካ፤ ኩማ እየመራ እየሄደ የመለስ ዜናዊን የቤት ሥራ ይሰራል እንጂ ምንም ዓይነት የሕዝብ ውክልና የለውም” ያሉት አቶ አሚን “የኛን መብት ከሚያስከብር ና ከሚያከበር ሁሉ ጋር አብረን እንሰራለን።” ብለዋል።

አቶ አሚን ንግግራቸውን ቀጥለው “የወያኔ አንቀጽ 39 (የብሄረሰቦች መብት እስከመገንጠል የሚለው) መሸንገያ አንቀጽ እንጂ የብሄረሰቦችን መብት ያስከበረ አይደለም። ሕገመንግስቱን ስትመለከቱት ይህንን አንቀጽ የሚያፈርሱ በርካታ ነገሮችን አስቀምጧል” ያሉት አቶ አሚን “አጼ ምኒልክ እና አጼ ሃይለ ሥላሴ ለሰሩት ጥፋት የልጅ ልጆቻቸው መጠየቅ የለባቸውም። ያለፈውን ታሪክ የመጽሀፍ መደርደሪያ ላይ አስቀምጠን አሁን ይህኛው ትውልድ አዲስ ታሪክ ለመጻፍ መዘጋጀት አለበት እንጂ በአያቶቹ ጥፋት የሚከሰስ ትውልድ መኖር የለበትም። በዘር ተከፋፈሎ እንደዚህ ስንባል ነበር እየተባሉ መለያየት የሚጠቅመው አሁን ላለው የወያኔ ስር ዓት እንጂ ዲሞክራቲክ ትግሉን አይደለም። የኦሮሞ ሕዝብ አዲስ ትውልድ አመለካከቱ በጣም እያደገ ነው። ከኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ተባብሮ በአንድነት ተስማምቶ የሚኖርበትን ሁኔታ ይፈልጋል። ስለዚህ በጋራ በአንድ ኢትዮጵያዊነት ስር የሚያኖረንን ስልት መከተል አለብን” ሲሉ ተናግረዋል።

ዛሬ በሚኒያፖሊስ የተጠራው ስብሰባ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን እንዲያሳትፍ ቀድሞ የታቀደ ቢሆንም ትናንትና ከትናንት በስቲያ ዲሴምበር 30 እና 31 የድርጅቱ አመራር አባላት በዝግ ባደረጉት ስብሰባ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ጋር በአንድነት ስብሰባ ከመጠራቱ በፊት የኦሮሞን ሕዝብ በቅድሚያ ማሳመን አለብን በሚል ተወስኗል። በዚህም መሰረት በቅርብ ቀን ትልቅ የኢትዮጵያውያን ስብሰባ እንደሚጠራ ኦነግ አስታውቋል። በዛሬው እለት ኦነግ ኢትዮጵያዊነቱን አምኖና ተቀብሎ ለአዲስ የትግል ስልት መዘጋጀቱን በርከት ያሉ የስብሰባው ታዳሚዎች ካለመንም ተቃውሞ ደግፈው ለስራ ተዘጋጅተዋል። ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኋላም እንኳን ደስ ያለን እየተባባሉ እንደነበር የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ አዘጋጅ ተመልክቷል።

ስብሰባው በኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ብሄረሰብ ባህል መሰረት በአባቶች ምርቃት ነበር የተዘጋው። ትላልቅ አባቶች ባደረጉት ምርቃትም አዲሱ የትግል አቅጣጫ ከግብ እንዲደርስ ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በስብሰባው ላይ ከተሳተፉት ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ የሆነውና በሚኒሶታ የሚኖረው ፉአድ አባነሻ ለዘ-ሐበሻ በሰጠው መግለጫ “እኔ እስካሁን ድረስ ባረጀው የኦነግ ሃሳብ ላይ ነበርኩ። የቀድሞው ትግል ስልት ጥሩ አለመሆኑን ተረድቻለሁ። እስካሁን ለወያኔ ተመቻችተን ነበር የተቀመጥነው። የሚያዋጣው አንድ ሆኖ በአንድ ላይ መታገልና አብሮ መኖር ነው። በዛሬው የኦነግ አዲስ የትግል ስልት በጣም ተደስቻለሁ። በጋራ ታግለን ሃገራችንን ከወያኔ ነጻ እናወጣታለን” ብሎናል።

የኦነግን መግለጫ ለማንበብ የሚከተለውን ይጫኑ  - OLF_National_Council_Press_Release_final (1)

 

 

http://www.zehabesha.com/

Continue reading …

መግቢያ፤

[caption id="attachment_11739" align="alignleft" width="150" caption="Dr. Seid Hassen - Murray State University"][/caption]

በፍኖተ ነፃነት 2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.14 መግቢያ ላይ እንደገለጽኩት የሶሻሊስቱ (የኮሙኒስቱ) ሥርዓት ተንኮታኩቶ ሲወድቅ ከዚያ በፊት ታይቶ ያልታወቀ ግዙፍ ሙስና መከሰቱን ነበር። በዚህም የተነሳ ሙስናዎች በሁለት ፀንፎች መልክ ተመድበው እንዲታዩ የግድ ብሏል። እነዚህም (1) በመንግሥታዊ አስተዳደር ብልሹነት መስክ የሚሰባሰቡ/የሚገለፁ/የሚከሰቱ ሙስናዎች (administrative corruption) እና፤ (2) የመንግሥቱን የሥልጣን አውታር፤ አስተዳደሩን፤ ህጎቹን፤ ወ.ዘ.ተ. በመጥለፍ/በመማረክ የሚገለፁ የሙስና ጠባዮች (state capture) ናቸው። የአስተዳደሩን ብልሹነት ተጠግተው የሚከሰቱ ሙስናዎች ሕጎቹና ደንቦቹ ሳይደመሠሡ (እንደተጠበቁ ሆነው) ነገር ግን የህጎቹና የደንቦቹን አፈፃፀሞች በድብቅና ህጋዊ ባልሆነ መልክ የግለሰቦችን ጥቅሞች ማካበቻ ማድረግ  እንደሆነና  እነዚህም ከተራ ጉቦ ጀምሮ እስክ ታላላቅ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ያሳተፉ ከፍተኛ ሙስናዎች/ምዝበራዎች ሊሆኑ  እንደሚችሉ ተገልጿል። በሁለቱ ተከታታይ መጣጥፎቼም የዚሁኑ በመጀመሪያ መልክ ያሰፈርኩትን የሙስና ክስተቶች፤ጠባያትና፤ ተንቆች በመጠኑ ዘርዘር አድረጌ አቅርቤ ነበር። በዚህ ተካታይ ጽሁፍ ደግሞ የሁለተኛውን የሙስና ክስተቶች፤ጠባያትና፤ ተንቆች አቀርባለሁ። ይህም ሙስና ጠባዩና ከስተቱ፤ የመንግሥትን ሥልጣን፤ ህጎችንና የአስተዳደር ደንቦችን በመማረክ/በመጥለፍ የሚከናወን፤ እንዲሁም የአንዲት ሀገር ህጎችን፤ ደንቦችን፤ ሥርዓቶችንና ቁጥጥሮቹን፤ (laws, regulations, decrees, andother government policies) በማስቀየርና በመቀየር/በመጥለፍ ላይ የሚከሰት ሆኖ፤ የመግሥት አውታር ጠላፊዎቹም የራሳቸውን ጥቅሞች በማካበት የሕዝቡንና የሀገርን ጥቅም በመጉዳት እንደሚከሰት ነው። ጠላፊዎቹም/ማራኪዎቹም (captors) ሥልጣን ተሻሚ ግለሰቦች፤ ተመሳጣሪ ቡድኖች፤ በአምባገነናዊ መልክ ሥልጣን ላይ የወጡ ቡድኖች (oligarchy)፤ ባለጌ ባለሥልጣኖች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እንደዚህ አይነቱ ሙስናም የተከሰተው የሶሻሊዝም/ኮሙኒዝም አይዲዮሎጂ መርህን ይከተሉ በነበሩ ሀገሮች እንደነበርና እነዚህም ሀገሮች “የነፃ ገባያን” (ካፒታሊዝም) መርህ ለመከተል ሲፈልጉ አብሮ የሚከሰት ነው። የዚህ አይነቱ መስና ወደ ከፍተኛ እና የከፋ ደረጃ ሲደርስ ደግሞ ጠላፊዎቹ የመንግሥት ሥልጣኑን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልክ በእጃቸው ያስገቡና ሙስናው እጂግ የከፋ ይሆናል። ይህ ዓይነቱ ሙስና ሚዛኑ የሰፋና ውጤቱ የከፋ ከመኑም በላይ ውጤቱ የፖለቲካ ፓርቲ ሀብቶች የሆኑ ኦሊጋርኮች (oligarchs) እና ክምችት የበዛባቸው ባለሀብቶችን (Business Empires) መፍጠር ነው።

ይህ የአንዲት ሀገርን የፖለቲካ ሥልጣንና ኤኮኖሚን በመመማረክ የተከሰተው ሙስና ጠባዮች በርከት ያሉና እንደየሀገሩ ለየት ያሉ ጠባዮችና ክስተቶች ቢኖሩትም፤ በርካታ ተመሳሳይ ጠባዮችም አሉት። እነዚህ ክስተቶች ከሞላ ጎደል፤ በአልባኒያ፤ በአርሜኔያ፤ በአዘርብጃን፤ በክሮኤሽያ፤ በሰርቢያ፤ በላትቪአ፤ በሩሲያ፤ በዩክራይን፤ በቤላሩስ፤ በቱርክሜንስታን፤ በሌሎቹን እንዲሆም በአፍሪካ ውስጥ፤ በዩጋንዳና በሩዋንዳ በሰፊው የተንፀባረቁ ሲሆን፤ በከፊልም ቢሆን በሆስኒ ሙባረክ ትመራ በነበረችው ግብፅ፤ በደቡብ የመንና በከፊልም በደቡብ አፍሪካ ተንፀባርቋል። በእኔ አስተሳሰብና ምርምር ለእንደዚህ አይነቱ ሙስና በዋናነት የምትቀርበው ሀገር ኢትዮጵያ ስትሆን፤ እንዳውም በኢትዮጵያ የተከሰተውን የጠላፊ ሙስናን የከፋና “ልዩ” የሚያደርጉትም ክስተቶች በርካታ ናቸው።

“የሥልጣን ጠላፊው” ሙሳና ተግባራትና ተግባራዊ ምሰሎች (Variation in the Pattern of State Capture Corruption)

ከዚ በታች (በከፊል) የጠቀስኳቸው “የሥልጣን ጠላፊው” ሙስናዎች ከላይ በጠቀስኳቸው ሀገሮች ውስጥ የተከሰቱ ናቸው።

“የሥልጣን ጠላፊው” ሙስና፤

  1. የአንዲት ሀገርን ፖሊቲካዊና ኤኮኖሚያዊ አውታሮችን ለመቀማት ካስቻሏቸውና ከሚያስችሏቸው አንዱና ዋናው መንገድ፤ የሀገሪቱን የሕግ፤ የአስተዳደር፤ የወታደራዊ፤ የሕግ አስከባሪ ማለት የፍርድ ቤቶችንና የፖሊስ አውታሮችን (apparatus) ማላላት/ማዳከም/መበተን ወይም እንዲዳከሙ ማድረግ (weakening state institutions) ነው። እነዚህ አውታሮች ከማዳከሙ/ከመበተኑ ጋር ተያይዞ የሀገርቷን ሀብት መበዘበር በሰፌው ይካሄዳል፤ ለቀጣይ ምዝበራ አመቺ ሁኔታዎችንም መፍጠር አንዱ ተግባራቸው ነው።
  2. የሥለጣን፤ የመንግሥት አውታርና የኤኮኖሚ ጠላፊዎቹ፤ የኤኮኖሚ ለውጡን (Economic Reform) ሙሉ በሙሉ እንዳይሳካ ከማድረገቻውም በላይ፤ ለውጡ እንዲቀለበስም ያደርጋሉ። የኤኮኖሚ ለውጥ ሂደቱን ተጠቅመውም የራሳቸውን ሀብት ያካብታሉ። ከሚጠቀሙምባቸውም መንገዶች መካከል፤ በመግሥት ሥር የነበሩትን ኩባንያዎችና የኤኮኖሚ አውታሮች ወደግል ባለሀብትነት ለመለወጥ የሀራጅ ሂደት በረከሽ ዋጋ ለራሳቸውና ለጥቅም ተጋሪዎቻቸው እንዲዛወሩ በማድረግ ነው።
  3. በሥልጣን ላይ በመባለግና ኤኮኖሚውን ወደ-ግል ባለሀብትነት ለመለወጥ በሚደረገው ሂደት ላይ ጣልቃ በመግባታቸው የተነሳ የሀገሪቱን ኤኮኖሚ ሙሉ በሙሉ ወደ-ግል ሀብትነት እንዳይሸጋገር መሰናክል ይሆናሉ። በዚህም የተነሳ የሀገሪቱን ኤኮንሚ ለማሻሻል የሚደረገው ጥረት እንዲጨናገፍ ስልጣንን ተጠቅመw ጋሬጣ ይሆናሉ። ይህ አይነቱ ክስተት የተጠናወታቸው ሀገሮችም፤ ወይ ሶሻሊስት፤ ወይ የገባያውን የኤኮኖሚ መስመር ሳይከተሉ የቀሩና የኮኖሚው መሻሻልም (privatization and reform) ተጨናግፎ ይቀራል።
  4. “የኤኮኖሚውን ሥርዓት መለወጥ/ማሻሻል” -(privatization and reform) የሚለውን በዓለም ባንክና በዓለም የገንዘብ ድርጅት የሚገፋውን መርህ ተጠቅመው የተቀናበረ ዝርፊያ ያደርጉና ባንኮችን፤ በመንግሥት ሥር ያሉና የነበሩ ድርጅቶችንና ኩባንያዎችን፤ የአስመጭና ላኪ የንግድ ዘርፎችን፤ የአከፋፋይና የተራ ነግድ ዘርፎችን፤ የከተማ መሬትንና በተለይም የመገናኛ ዘዴዎችን (media) ሆን ብለው/ትኩረት ሰጥተው በቁጥጥራቸው ሥር ያሰገቡና የራሳቸውን የላቀና ከፍ ያለ በተለይም ከፖለቲካው ጋር የተዛመደ ኤኮኖሚንም (empires and oligarchs ) ይመሰርታሉ። ይህ ተግባር በአብዛኞቹ ድህረ-ኮሙኒስት (Post-communist) ሀገሮችም ወደ የሞኖፖሊ ያዘነበለ/ያዘመመ የኤኮኖሚ ሥርዓትና አያያዝ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል።
  5. የጠላፊዎቹ ቁጥጥርና ጣልቃ ገብነቱ በበዛባቸው ሀገሮች፤ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ፓርቲያቸው በሕግ አስከባሪና አስፈፃሚ ውስጥም ገብተው ለመቆጣጠር ችለዋል። ፍርድ ቤቶችንና የሕግ አስከባሪ አውታሮችን በመቆጣጠርና ከነሱም ጋር በመተባበርም፤ የሀገርን ሀብት ዘርፈዋል። ዜጎችን ያለ-ምክንያት እስር-ቤቶች ከተዋል። ድራሻቸውንም አጥፍተዋል።
  6. የጠለፉትን ሥልጣን ተጠቅመው ለገበብቧቸው/ለመሰርቷቸው የራሳቸው የኤኮኖሚ አውታሮች (their own empires and oligarchs) በሕገ-ወጥነት ከወለድ ነፃ የሆነ “ብድር” እንዲገፋላቸው ያደርጋሉ። የሥራ ፈቃድን “ለወገኖቻቸው” ብቻ ያድላሉ፤ ያለ-ጨረታ ኮንትራት ይሰጣሉ፤ ከግምሩክና ከታክስ ክፍያ ነፃ ያስደርጋሉ። አንዳንድ ጊዜም “ብድሩ” ተብሎ የተሰጠው ሳይከፈል ይቀራል።
  7. ከውጭ በእርዳታ የተገኙ ብድሮችንም ሆነ ጭሮታዎችን እንዲሆም መዋዕለ-ንዋይ ለራሳቸውና “የእኛ” ለሚሏቸው አድሎ በማድረገ ይሰጣሉ።
  8. ያቋቋሟቸውን “ኩባንያዎች ለመጥቅም፤ የውሽት (በማር የተቀባ እሬታዊ ሕጎችን- phony  regulations) አውጥተው ይጠቀማሉ።
  9. በዝርፊያ beመሠርቷቸው ታላላቅ አውታሮች (Economic Empires and Oligarchs) እራሳቸውንና በተወሰነ ደረጃም የሚያምኗቸውን ሰውች የቦርድ አባልና መሪ በማድረግ ይሾማሉ። ይህ ተግባር የኤኮኖሚውን ዋና ዋና አውታሮች ለመቆጣጠር ከማስቻሉም በላይ፤ የገቢ ምንጮቻቸውን ያበዛላቸውዋል።
  10. በአስመሳይነት የፈጠሯቸውን “ኩብናያዎች” (shell companies and oligarchs) ተጠቅመው የዘረፉትን ሀብት ወደ-ውጭ ሀገር ያሸሻሉ።
  11. በጠለፋ ሙስና የተዘፈቁት ቡድኖች፤ የተወሰኑ ዖሊጋርኪ ተቋማትን በመገንባት ብቻ ሳይወሰኑ በየቦታው፤ በየከፍለ-ሀገሩ፤ በውጭ ሀገርም ጭምር የተለያዩ የኤኮኖሚ ዘርፉን ለመቆጣጠር በርካታ የንግድ ዘርፎችን ያቋቁማሉ (create constellation of businesses, crony capitalism and predatory activities)።
  12. የማፊያ አይነት፤ አድሎ የበዛበት፤ ዘረኝነትም የሰፈረበት የኤኮኖሚ አውጣር እንደ-ሸረሪት ድር ዘርግተው “የእኛ ወገን አይደለም” የሚሉትን የግል ባለሀብት ያገለለ የኤኮኖሚ ሥርዓትን ይመሰረታሉ። የማፊያ ጠባይ ስላላቸውም የግል ድርጅቶችና ግለሰቦች የበለጠ ሲቀናቸውና እነሱን ሲበለጧቸው፤ ይቀኑና ግለሰቦቹንና ድርጅቶቹን አስፈራርተው ወይም ቀምተው (Blackmailing private firms) ያባራሉ።

  1. ሙስናው ተስፋፋቱ ሲመጣ፤ ከሕዝቡም ሆነ ከለጋሽ ሀገሮችና ድርጅቶች ቅሬታ ይነሳል። ሕዝቡንና ለጋሾቻን ለመሸንገል፤ የፀረ-ሙስናው ተቋምን ያቋቁሙና (phony anti-corruption regulations) ከእጃቸው እንዳይወጣ አድረገው ይመሠርቱትና በሙሳና ላይ የሚደረገውን ጦርነት እንዲኮላሽ ያደረጋሉ። በግልም ሆነ በሌሎች ድርጅቶች የተቋቋሙትን የፀረ-ሙሳና እንቅስቃሴዎችን ይጠልፉና በቁጥጥራቸው ያስገባሉ። የፀረ-ሙስናው ትግልም ተኮላሽቶ ይቀራል። ሕዝቡም በመግሥትና በፀረ-ሙሳና ተቋሙ ላይ ተስፋውን ያጣል።
  2. የ”ሥልጣን ጠላፊ ሙስና” በተስፋፋባቸው ሀገሮች በመንግሥትና በፖለቲካ ፓርቲዎች፤ እንዲሁም በመንግሥታዊ ድርጅቶችና በፖለቲካ ድርጆቶች መካከል መኖር የመገባው ልዩነት የደበዘዘ ነው። ይህም የደበዘዘ ግንኙንት (ልዩነት)ም የሙስና መስፋፋት ምክንያትና አንዱ ጠባዩም ነው።
  3. በጠላፊ ሙስና የተመሰረቱት “ኩባንያዎች” ሀብት የፖለቲካ ፓርቲን ለመገንባት ሕገ-ወጥ በሆነ መልክ ይውላል።
  4. ባጠቃላይ፤ የሀገሪቱን ዋና ዋና የደም-ሥር ሀብቶች በቁጥጥር ውስጥ በማስገባትና የሞኖፖሊ ሥር ዓትን በማስፈር አጠቃላይ የሀገሪቱን የኤኮኖሚ እቅድ ለመግታት እንዲያስችላቸው (cornering ) ካማድረግ አይቆጠቡም።

 

ማሳሰቢያዎች

ሀ)      አንባቢ መርሳት የለለበት ነገር ቢኖር ምንም እንኳ በአስተዳደር ብልሹነትና ህጎችንና ደንቦችን በመማረክ/በመጥለፍ የሚከሰቱት ሙስናዎች በሥነ-ልቦናና በተግባር ልንለያቸው ብንችልም፤ አብዛኛውን ጊዜ አንዱን ከሌላው መነጠል ያስቸግራል። በተለይም ህጎችንና ደንቦችን በመማረክ/በመጥለፍ የሚከሰተው ሙስና (state capture) የከፋ ስለሆነ በአስተዳደር ብልሹነት (administrative corruption) የሚከሰቱት ሙስናዎችንም ይጨምራል።

 

ለ)      አንዳንድ መልስ የሚሹ ጥያቄዎች፤

አንባቢያን ከዚህ በታች የጠቀስኳቸውን ጥያቆች በአንክሮ ተመልከተው መልስ እንዲሰጡ (ቢያንስም እንዲያሰላስሏቸው) እጋብዛለሁ።

  1. በ”ሥልጣን ጠላፊ ሙስና” መልክ በኢትዮጵያ የተደረገው የኤኮኖሚ ዝርፊያ ምን ይመስላል? በሌሎች ሀገሮች ከተከሰቱት ዝርፊዎች እንዴት ይለያል? የባሰ ነው፤ ወይስ የቀለለ? ለምን? እንዴት?
  2. አንዳንድ ሰዎች በኤትዮጵያ የተከሰተውና እየተከሰተ ያለው ሙስና ከማፊያና ከተቀናጀ ሕገ-ወጥ ድርጊት (organized crime) ጋር ያመሳስሉታል። ይህ ማመሳሰል ትክክል ነው? ከሆነስ (ካልሆነስ) ለምን? እንዴት?
  3. በየኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው የጠላፊ ሙሳናን ጠላፊዎቹ በተጣደፈ መልክ እንዲፈጽሙት (ተግባራዊ እንዲያደርጉት) ያስቻሏቸው ነገሮች ምንድር ናቸው? የጠላፊዎችን ጠባያት የሌሎች ሀገሮችን ሥልጣንና ንብረት ከጠለፉት ጋር የሚለዩአቸው ጠባዮች ምን ይመስላሉ?
  4. የጥልፊያ ሙስናውን የምናቃልልበት፤ የሕዝብን ሀብት የምናስመልስባቸው መንገዶች እንዴት መሆን አለባቸው?
    1. በኤኮኖሚና የፖለቲካን ጠለፋ መሠረት ያደረገ ሙሳና የአሸበሪነት ጠባይ አለው። በዚህም የተነሳ ቋሚ አይደለም፤ ይባላል ( Oligarchic corruption is unstable by its nature and violent as well!) ታዲያ በኢትዮያ ላይ የተከሰተው የጠላፊ ሙስና ለምን ይህን ያህል ጊዜ ቆየ? ሲበተንስ የሚያስከተላቸው በሀገርና በሕዝብ ላይ የሚደርሱ ክስተቶች ምን ይመስላሉ? ይህ የጠላፊ ሙስና በሀገር ኤኮኖሚ፤ ፖሊቲካና ሕብረተሰዊ ግንኙነት ላይ የሚያደረሰው የክፋት ውጤት (አፀፋ) ምንድር ነው (ምን ሊሆን ይችላል)? ለነዚህስ የከፉ ከስተቶች ተዘጋጅተናል?

በሌላ ጊዜና በሌላ ጽሁፍ እስከምንገኝ ድረስ አላህ ቸሩን ይበለን።

Continue reading …

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዛሬ እሁድ ታህሳስ 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባዔዉን አጠናቀቀ። ለሚቀጥሉት አመታት ድርጅቱን በሊቀመንበርነት የሚመሩትን እንዲሁም የድርጅቱ የላእላይ ምክር ቤት አባላትን ጠቅላላ ጉባዔዉ የመረጠ ሲሆን ስብሰባዉ በተሳሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና ያመለክታል።

የድርጅቱ ሊቀመንበር ለመሆን ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የአዲስ አበባ የአንድነት ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶር ንጋት አስፋዉ እንዲሁም ከአንድነት ፓርቲ ጋር የተዋሃደዉ የብርሃን ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ፣ ለእጩነት ቀርበዉ እንደነበረ መዘገባችን ይታወሳል።

ከስብሰባዉ በፊት ዶር ንጋት እራሳቸዉን ከእጩነት በማንሳታቸዉ፣ ፉክክሩ በዶር ነጋሶና በኢንጂነር ዘለቀ መካከል ብቻ እንደነበረ የደረሰን ዘገባ አክሎ ያትታል።

ከጠለቀ ዉይይትና ዲሞክራሲያው ክርክሮች በኋላ የጠቅላላ ጉባዔዉ አባላት፣ ዶር ነጋሶ፣ አሁን የያዙትን ሃላፊነት እንዲቀጥሉና የፓርቲዉ ሊቀመንበር ሆነዉ እንዲቀጥሉ በአብላጫ ድምጽ ወሰኗል። የብዙ አባላትን ድምጽና ድጋፍ ያገኙት ኢንጂነር ዘለቀም፣ ያሸነፉት ዶር ነጋሶ ሳይሆኑ ያሸነፈዉ ዲሞክራሲ እንደሆነ በመግለጽ ፣ የጠቅላላ ጉባዔዉን ዉሳኔ በጸጋ እንደሚቀበሉ፣ ከዶር ነጋሶም ጋር ተያይዘዉ በመስራት፣ ፓርቲዉ የቆሞለትን አላማ ከግቡ ለማድረስ የድርሻቸዉን እንደሚወጡ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።

ጠቅላላ ጉባኤዉ የድርጅቱን ሊቀመንበር ከመምረጥ ባሻገር፣ የላእላይ ምክር ቤት አባላትን የመረጠ ሲሆን የድርጅቱ ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ በላይ፣ የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ ዳዊት አስራደ፣ የፓርላማ አባል አቶ ግርማ ሰይፉን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች የምክር ቤቱ አባላት እንደሆኑም ለማወቅ ችለናል።

ለሊቀመንበርነት እጩ ተወዳደሪ ሆነዉ ቀርበዉ የነበሩት ዶር ንጋትንና ኢንጂነር ዘለቀን እንዲሁም በእሥር የሚገኙት አቶ አንዱዋለም አራጌንና አቶ ናትናዔል መኮንንን በሌሉበት፣ እንዲሁም ከአሜሪካ አገር ሆነዉ በስካፕይፒ ስብሰባዉ የተካፈሉትን የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስቴር አቶ ስዬ አብርሃን የምክር ቤቱ አባላት እንዲሆኑ ጉባዔዉ መርጧቸዋል።

ከቀድሞ የአመራር አባላት መካከል ዶር ኃይሉ አራያ ፣ አቶ አስራት ጣሴ በድጋሚ የምክር ቤቱ አባል እንዲሆኑ የተመረጡ ሲሆን፣ የድርጅቱ አንጋፋ መሪ የነበሩት ኢንጂነር ግዛቸዉ የምክር ቤቱ አባል እንዳልሆኑም ለማወቅ ችለናል። ኢንጂነር ግዛቸዉ፣ ወጣቶች ወደ ድርጅቱ አመራርነት መምጣት አለባቸው በሚል እነ አቶ አንድዋለም አራጌን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች ወደ አማራር እንዲመጡ ያደረጉ ሲሆን፣ ከብርሃን ፓርቲ ጋር ዉህደት እንዲመሰረት፣ ኢትዮጵያዉያን በዘር ሳይከፋፈሉ ለአንዲት ኢትዮጵያ በጋራ መስራት ይቻል ዘንድ የአንድነት ፓርቲ በመድረክ ዉስጥ እንዲሰራ ቁልፍ ሚና ተጫዉተዋል።

ዛሬ በተደረገዉ ጉባዔ የታሰሩ የአንድነት አመራር አባላት ቤተሰቦች፣ የመድረክ አባል ድርጅቶች አመራር አባላት ፣ ዲፕሎማቶች እንደተገኙም ለማወቅ ችለናል። የመድረክ አመራር አባላት በተለይም የአንድነት ፓርቲን የብርሃን ፓርቲ መዋሃዳቸዉን እንደ ትልቅ ስኬት በመግልጽ መድረክም ከግንባርነት ወደ ዉህደት መገስገስ እንዳለበት ገልጸዋል።

የድርጅቱ ሊቀመንበር እንዲሆኑ የተመረጡት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ ካቢኔያቸዉን (የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን) የሚሰየሙ ሲሆን፣ የተሰየሙት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በአብላጫ ድምጽ የምክር ቤቱን ድጋፍ ካላገኙ ተቀባይነት እንደማይኖራቸዉ የድርጅቱ ሕገ ደንብ ይገጻል።የምክር ቤት አባላት ያልሆኑ የድርጅቱ አባላት፣ በሊቀመንበሩ ከተሰየሙና በምክር ቤቱ ተቀባይነት ካገኙ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሊሆኑ እንደሚችሉም የድርጅት ሕገ ደንብ ይገልጻል።

ለተሰብሳቢዉ በሳካይፒ ንግግር ያደረጉት የሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶ ሊቀመንበር አቶ አሎግ ልመንህ ፣ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአገር ቤት የሚደረገዉ ትግል ለመደገፍ ቆርጠው መነሳታቸውን በመግልጽ፣ በተለይም በድርጅቱ ሊቀመንበር የሚመረጠዉና በምክር ቤቱ የሚጸድቀዉ የስራ አፈጻሚ ኮሚቴ በርካታ ወጣቶችን ያቀፈ እንዲሚሆን ያላቸዉን ተስፋ ገልጸዋል።

Continue reading …
ጠያቂው- መምህር የኔ ሰው ራስህን መስዋእት ለማድረግ ዝግጅትህን ባጠናቀክበት በዚህች የመጨረሻ ሰአት  ቃለ ምልልስ ለምድረግ ስለፈቀድክልኝ ከልብ አመሰግናለሁ።
የኔሰው፤- እኔም አመሰግናለሁ እድሉን ስላገኘሁ።
ጠያቀው፡- የኔሰው በአሁኑ ሰኣት ራስህን መስዋእት ለማደርግ ቆርጠህ ወደዚያው ስታመራ ነው ያገኘሁህ እስቲ ልብህ ምን ይላል?
የኔሰው፦-  ይህንን ከባድ ወሳኔ ስወስን ዝም ብዬ አይደለም። አርቄ ያየሁት ነገር ስላለ ነው።ከሁሉም በላይ ለነጻነት እና ለፍትህ ለሚደረገው ህዝባዊ አመጽ እንደ ቀንዲል በመሆኔ በውነት እልሃለሁ ልቤ ሃሴት ተሞልቱዋል።
ጠያቂው፤- እንግዲህ የኔ ሰው በኛ ሃገር የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አሁን አንተ ልታደርገው በተዘጋጀህበት ራስን በማቃጠል የተደረገ መስዋእትነት የለም። ለምን ይህን መንገድ መረጥክ?
የኔሰው፤- በሃገራችን ታሪክ ወስጥ ፍትህና ዴሞክራሲን ለማስፈን ሲሉ ብዙ መስዋእትምነት የከፈሉ እየከፈሉም ያሉ እንዳሉ አይዘነጋም። ብዙ ወጣቶች ህይወታቸውን አካላቸውን አጥተዋል። እነሱን ሁልጊዜም አደንቃለሁ። የእኔን እንዳልከው ለየት የሚያደርገው ባለተለመደ ሁኔታ አካሌን አቃጥዬ ለማለፍ መወሰኔ ነው። ለዚህ ከባድ መስዋእትነት ያነሳሱኝን መክንያቶች ልግለጽልህ።
1ኛ አካሌ ሲነድ ተምሳሊትነት አለው።
ዛሬ በፍትህ እና በዴሞክራሲ እጦት የሚቃጠለውን በኑሮ ውድነት እና በድህነት የሚነደውን የህዝብ ኑሮ ለመላው አለም ለማሳየት ሲሆን እኔ ራሴን ሳቃጥል በቁሙ የሚቃጠለውን ህዝብ በተምሳሊትነት ለማሳየት ነው። ይህን ሳደርግ ምን ያህል ግፍና መከራ እንደበዛብን አለም የበለጠ ይረዳል።
2ኛ ለመቀስቀስ
በቱኒዚያ ውስጥ አንድ የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ስራ አጥነትን ና ፍትህ እጦትን ተቃውሞ ራሱን በማቃጠሉ ታላቅ ህዝባዊ ቁጣ ተቀስቅሶ እንደምታየው በለውጥ ጎዳና ላይ ናቸው። ካገሩ አልፎም የአረብ አገሮችን እና ሰሜን አፍሪካን ሁሉ ሊያንቀሳቅስ የቻለ መስዋእትነት ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ያ ወጣት የጫረው የነጻነት እሳት እስካሁን ይነዳል። በመሆኑም እኔ  ይህንን መስዋእትነት ስመርጥ ከሁዋላየ የሚነሳውን ታላቅ ህዝባዊ አመጽ እና ፍሬውን እያየሁ ነው።
3ኛ ጥሪዬ ክብደት ይኖረዋል ብዬ ነው
ራሴን ለመስዋእትነት ሳዘጋጅ በአንድ ጥይት ባደርገው ስቃዩ ይቀንስልኝ ነበር። ታንቄ ወይም መርዝ ጠጥቼ ብሞት ይቀለኝ ነበር ነገር ግን እነዚህ የሞት መንገዶች ሁሉ የፈለኩትን ያህል የነጻነት እና የፍትህ ጩኽቴን ሊያስተጋቡልኝ አይችሉም። በመሆኑም ይህንን የከፋውን መራራ ጽዋ ጠጥቼ ማለፍን መረጥኩ። ስቃጠል ፍትህ…ፍትህ…ፍትህ…ፍትህ….እያልኩ ነው። ይህ መስዋእትነቴም ይህንን ጥሪ እንደ ነጋሪት ያስተጋባልኛል ህዝቡንም ሆ ብሎ እንዲነሳ ሃይል ይሆነዋል በሚል ነው።
4ኛ እኛም እንደነ ቱኒዚያና ሌሎች ሃገሮች ጀግና እንዳላን ለአለም ለማሳየትም ነው።
ጠያቂው፤- እንዳልከው በቱኒዚያ ያ ወጣት መስዋእት ከሆነ በሁዋላ ህዝቡ ሆ ብሎ ወጥቶ ለውጥ ማምጣት ችልዋል ካንተ መስዋእትነት በሁዋላ የምትፈልገው ህዝባዊ አመጽ የመነሳቱን ነገር በተመለከተ የእምነትህ ደረጃ የት ይደርሳል?
የኔሰው፡- የእምነት ደረጃዬ እና መተማመኔ ከፍተኛ በመሆኑ ነው ይህን ከባድ መንገድ እንድመርጥ ያደረገኝ። ከኔ መስዋእትነት በሁዋላ ወጣቶች አዛውንቶች ሴቶች ወንዶች ሁሉ ፍትህ..ፍትህ..ፍትህ…እያሉ ሲጮሁ በህሊናዬ ይታየኛል። ይህ ብቻም ሳይሆን የቱኒዚያው ወጣት ከሃገሩ አልፎ ለሌሎች አብሪ እንደሆነ ሁሉ የእኔ መስዋእትነት በፍትህ እጦት በአለም የመጨረሻ ደረጃ ላይ ለሚገኘው የምስራቅ አፍሪካ ህዝብ ንቅናቄ ቀንዲል ይሆናል ብዬ ህሉ አምኛለሁ።
ጠያቂው፦እንግዲህ አንተ መስዋእት ስትሆን ሁለት አይነት ዜናዎች መሰማታቸው አይቀርም። በተለይ በኢትዮጵያ መንግስት ዘንድ ምን ሊነገር የሚችል ይመስልሃል?
የኔ ሰው አንገቱን ወደቀኝ ወረወረና ፈገግ አለ……… ወዲያውም
የኔስወ፦  ምን ይሄ እኮ የታወቀ ነው። መቼ የነሱ አሳብ ይሳታል። አብዶ ነው የሚሉት።
እንደገና የኔሰው ፈገገ አለ…….
ጠያቂው፦ በመጨረሻ የምታስተላልፈው ነገር ካለ እድሉን ልስጥህማ
የኔሰው፡- እኔ እንግዲህ በቃ! የሚለውን መፎክር ከቃል ወደ ተግባር ለመቀየር ራሴን ቀዳሚ አድጊያለሁ። በዚህም ኩራት ይሰማኛል። ለሌሎች ወገኖቼ የምለው በቃ ብለው በአንድነት እንዲነሱ ነው። እኔ ይህንን መስዋእትነት ስመርጥ መኖር ስላልፈለኩ አይደለም። ገና ወጣት ነኝ ይሁን እንጂ ፍርሃትን ለማስወገድ ከባዱን መስዋእትነት እኔ ወስጄላችሑዋለሁና ሆ በሉ ወጡ በአንደነት ነው የምለው። የቱኒዚያን፤ የግብጽን፤ የሶርያን ህዝብ ተመልከቱ
ህዝብ ከተነሳ የሚመልሰው ነገር እንደሌለ ከነሱ ተማሩ እላለሁ። በተረፈ እንደማታሳፍሩኝ ተማምኜባችሁ እስከወዲያኛው ሄጃለሁ ።ቻው።
ጠያቂው፦ በመጨረሻም ስለቤተሰቦችህ የምትለን አለ?
የኔሰው በምናብ እንደገና ነጎደ……….አንገቱን ደፋና ጥቂት አሰበ። አይኖቹ የእንባ ዛላ አዘሉ…..
የነሰው፦- እነሱን እንግዲህ ለኢትዮጵያዊያን ትቼአቸው እሄዳለሁ።
ተቃቀፍን…… ሌሎች ቃለመጠይቁን ሳደርግ የነበሩ ሁሉ አቅፈውት አለቀሱ። በቁጭትም ከንፈራቸውን እየነከሱ የትግሉን ችቦ እንድሚያነሱ ቃል ገቡለት።
ጠያቂው፦ ራእይህ ግቡን እንደሚመታ እኔም አምናለሁ። አምላክ በገነት ያኑርህ ወንድምየ።
የኔሰው፦ አሜን። ቻው።
ወዲያውም የኔሰው ፍትህ….ፍትህ….የፍትህ ያለህ….ያለፍትህ ከመኖር ሞት ይሻለል…ፍትህ…ፍትህ……እያለ እየጮኸ ወደ መስዋእቱ ሜዳ አመራ።
ያዘጋጀውን የፍትህ  ጥያቄ ቀንዲል እሳት  በላዩ ላይ አነደደው። ለብዙ ደቂቃዎች ፍትህን…. እየጠራ የኔሰው የዚህኛውን አለም እስከወዲያኛው ተሰናበተው።
እኔም ጠያቂው  በምናብ የኔሰውን አግኝቼው ያደረኩትን ቃለምልልስ በዚሁ ቁዋጨሁ።
        ገለታው ዘለቀ
  geletawzeleke@gmail.com

Continue reading …

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

 

የሕገ-መንግሥት ጥሰቱና ገደብ የለሽ አምባገነንነቱ

እየጨመረና እየባሰበት ነው!!

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሠጠ መግለጫ 

            በመርህ ደረጃ የምናውቀውና በትምህርት ቤት የተማርነው ሰዎች ከታሪክ ይማራሉ በዚህም ስህተቶች እየታረሙ ይሄዳሉ፣ አይደገሙም የሚል ነው፡፡  ነገር ግን የሕይወት እንቆቅልሽና  በተግባር ስናየው ታሪክ፣ የሚያስተምረን፣ ሰዎች ከታሪክ የማይማሩ መሆናቸውን  መሆኑ  የሚያስገርም  ነው፡፡ ይበልጥ አስገራሚው ደግሞ  ሰዎች እንኳን ከአለፈ  ከታሪክና በፊት ለፊት  ከሚያዩት፣ ከሚሰሙትና ከሚያውቁት እውነታም እንደማይማሩ ነው፡፡ በተለይም አምባገነኖች፤ ጥቂቱንና የቅርቡን ለመጥቀስ፤ የግብፁ ሙባረክ ከቱኒዚያው በንዓሊ አልተማሩም፡፡ የሊቢያው ጋዳፊ ከግብጹ ሙባረክ አልተማሩም፡፡ የየመኑ ዓሊ አብደላ ሳሊሕና  የሶሪያው በሸር አልአሳድ ከጋዳፊ የተማሩ አይመስሉም፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለ አንዱ ከሌላው የማይማር መሆኑ የቀጠለና የማያቋርጥ ክስተት እየሆነ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ከምንም በላይ ግልጽ ሆኖ የመጣው ጉዳይ ከአለፈ ታሪክ፣ እንዲሁም ከፊት ለፊት ከሚያዩትና ከሚሰሙት አለመማር የአምባገኖች አንዱ ዓይነተኛ ባህሪ መሆኑ ነው፡፡

           ከላይ በመንደርደሪያ የጠቀስናቸው አስተያየቶች ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ በአገራችን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥትና የገዢው ፓርቲ እያደር እየታረመ፣ እየተማረ፤ እየሰከነና ልብ እየገዛ ይመጣ ይሆናል  እያልን ስለ አገር፣ ስለ ሕዝብና ስለ ራሱም ብሎ የሕግ የበላይነት እንዲያስከብር ደጋግመን ሳንሰለች ስንጎተጉተው ብንከርምም ሰሚ ጆሮ አልተገኘም፡፡ እንዲያውም ይባስ ብሎ አምባገነኑ መንግሥት ሲፈልግ በየጊዜው በሚያወጣቸው አሳሪና አስፈሪ አዋጆች ከፈለገም ያለምንም አዋጅ በጠራራ ፀሐይ ሕገ-መንግሥቱን በጉልበት እየጣሰ ነው፡፡ ዜጎችን አክብሮ  መከበር ለመንግሥት  ባዕድ ነገር  ሆኗል፡፡  መንግሥት በዜጎች ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት ተጠያቂነት የለበትም፡፡ ‹‹ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ ክብሩና መልካም ስሙ የመከበር መብት አለው›› የሚለው የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 24 ተ.ቁ 1 የወረቀት ላይ ጌጥ ሆኖ ነው የቀረው፡፡ በመሆኑም  መንግሥት ያለምንም ጥንቃቄና ማስተዋል ከጳጉሜ 2ዐዐ3 ዓም ጀምሮ የሠላማዊና ሕጋዊ ፖለቲካ አራማጆችንና ነፃ ጋዜጠኞችን በሽብርተኝነት ከሶ ወደ ወህኒ ቤት አውርዷቸዋል፡፡ ታሳሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ በአንድ በኩል በታክስ ከፋዩ ሕዝብ ገንዘብ የሚንቀሳቀሱት  ቴሌቪዥኖች ሬዲዮኖችና ጋዜጦች በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 2ዐ ተ.ቁ 3 የተከሰሱ ሰዎች ‹‹በፍርድ ሄደት ባሉበት ጊዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደ ጥፋተኛ ያለመቆጠር . . . መብት አላቸው›› የሚለውን በመጣስ አሸባሪነታቸው የተረጋገጠ እንደሆነ በአደባባይ ሲገልጽ ከርሟል፡፡ አሁንም እየገለጽ ነው፡፡

             ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ሕገ-መንግሥቱን የማሰከበርና የማስጠበቅ ኃላፊነትን በቃለ-መሀላ የተቀበሉት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጥቅምት 9 ቀን 2ዐዐ4 ዓም ፓርላማ  ተገኝተው በአደረጉት ንግግር በሽብር ተጠርጥረው ከተያዙት ተከሳሻች መካከል አንድም ሰው ማስረጃ ያልቀረበበት የለም ብለዋል፡፡ አልፈው ተርፈውም ሁሉም ተከሳሾች በበቂና በአሳማኝ ሁኔታ ወንጅለኛ ሆነው ስለተገኙ ነው በቁጥጥር ሥር የዋሉት በማለት  በሕግ   በሚያሰጠይቃቸው መልኩና በተለመደው ማንአለብኝነት  የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ   ጥሰውታል፡፡ የሚገርመው ጉዳዩ ግን እንዲህ ዓይነቱ ማረጋገጫ ከተሰጠባቸውና  አለአግባብ ከተንገላቱት ሰዎች  መካከል አራት ሰዎች በቅርቡ  መፈታታቸው  ነው፡፡ የተነገረውና እውነታው ሰማይና ምድር ያህል የተለያየ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የሌሎቹም ተከሳሾች ጉዳይ ከዚህ የተለዬ አይደለም  የሚል እምነት አለ፡፡  ተከሳሾቹን እኛ የምናውቃቸውና የምንመሰክርላቸው በሠላማዊ ትግል ተምሳሌትነታቸው ነው፡፡  ዛሬም ድምፃችንን  ከፍ አድርገን እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡

            ህዳር 9 ቀን 2ዐዐ4 ዓም በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች (ቃሊቲ) የተፈፀመው የአምባገነኖች የሕገ-መንግሥት ጥሰት  ደግሞ አንድ ሌላ   ተጨማሪ ማስረጃ ነው፡፡ በእለቱ የማረሚያ ቤቱን ሕግ መሠረት በማድረግ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበርና ሁለት ም/ሊቀመናብርት፣ የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚና የብሔራዊ ም/ቤት አባላት  በቃሊቲ በመገኘት በሽብርተኝነት ተጠርጥረው የታሰሩትን የፓርቲውን አባላት፣ የመድረክ አባል ፓርቲ አባላትና ጋዜጠኞችን ለመጠየቅ 6፡ዐዐ ሰዓት ላይ በቃሊቲ በመገኘት   ከሕዝብ ጋር ተራ ይዘው  ወደ  ግቢው  ቢገቡም በእስር ቤቱ ኃላፊዎች  የተለመደ የማንአለብኝነትና የአምባገነንነት መንፈስ የሕገ-መንግሥቱን አንቀጽ 21 በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች መብት በሚለው ስር ተ.ቁ 2 ‹‹ ከትዳር ጓደኞቻቸው፣ ከቅርብ ዘመዶቻቸው ከጓደኞቻቸው (ስርዝ የተጨመረ) . . . ጋር ለመገናኘትና እንዲጎበኛቸውም እድል የማግኘት መብት አላቸው›› የሚለው ተጥሶ ጥየቃውን ተከልክለዋል፡፡   ይህ ዓይነቱ ጥሰት ተገቢ  አይደለም በማለት ከኃላፊዎቹ ጋር የተሞከረው ውይይት ሊሳካ አልቻለም፡፡ ምናልባትም  የዓይናችሁ  ቀለም ስለአላማረን ነው  የማትገቡት የሚለው አባባል እዚህም ሊጠቀስ ይችል ይሆናል፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ የሕገ-መንግሥት ጥሰት አዲስ አይደለም፡፡  ከዚህ የባሱ የሕገ-መንግሥት ጥሰቶች በከፋና በሚጎዳ ሁኔታ እየተፈፀሙ ነው፡፡  መንግሥት በሕዝብ ስም  በአደራ የያዘውን ሥልጣን ለሕዝብ ማጥቂያ እየተጠቀመበት ነው፡፡ በሕግ ሽፋን ሕዝብን የማጥቃት ዘመቻ እያካሄደ ነው፡፡

            የዚህ መግለጫ ዋና ዓላማ ምንም ቢዘገይ የመንግሥትን ሥልጣን የያዘው ገዢው ፓርቲ ቆም ብሎ በሰከነ አዕምሮ  ስለአገርና ስለ ሕዝብ፤ ስለ ሕገ-መንግሥታዊነት እንዲያስብበት ለማሳሰብ ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊን እንደ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ ጉልበተኝነትንና ጥቃትን አምርረን እንጠላለን፡፡  እንታገለዋለንም፡፡ ትግላችንም ጥቃትንና ጉልበተኝነትን ከአገራችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ነው፡፡  ኢህአዴግአዊያን ግን ጉልበተኝነትን፣ አምባገነንነትን፣ ጥቃትን፣ እንቃወማለን ሲሉ ‹‹ብሶት የወለደን ነን ሲሉ›› ጉልበተኝነትን፣ አምባገነንነትን፣ ጥቃትን ከአገር ለማትፋት ሳይሆን እራሳቸውን አዲስ አጥቂዎች፣ አምባገነኖች፣ ጉልበተኞች ለማድረግና ሌሎችን ለመበደልና ለማጥቃት ነው፡፡ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ብሶት የወለዳቸው መሆናቸው ቀርቶ ብሶት የወለደው ሕዝብ እየፈጠሩ ነው፡፡   በእኛ በኩል ኢህአዴግ ከታሪክ ባይማርም ከራሱ ታሪክ በመነሳት ብሶት የወለደው ሕዝብ አምባገነኖችን እንደሚያስወግድ እንገነዘባለን፡፡

          ትግላችን ለእኩልነት፣ ለነፃነት ለእድገትና ብልጽግና ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ለሕጋዊነትና ለሕገ-መንግሥታዊነት ነው፡፡ የነፃነቶችና መብቶች መከበር ለእድገትና ብልጽግና ቁልፍ ናቸው፡፡ የነፃነት በርን ጥርቅሞ ዘግቶ ሕገ-መንግሥትን እየደፈጠጡ ስለ ልማት መለፈፍ ትርጉም የለውም፡፡ ሂውማን ደቨሎፕሜንት ኢንዲክስ እንደሚያሳየው ከሆነ በ2ዐ11 ኢትዮጵያ ከ185 አገሮች መካከል በእድገት 174ኛ ደረጃ ላይ ነች፡፡ በዓለም ላይ በእድገት የምትበልጠው 11 አገሮችን ብቻ ነው፡፡› በብልጽግና ደረጃም ቢሆን ኢትዮጵያ ለግምገማ ከቀረቡ 11ዐ አገሮች መካከል 1ዐ4ኛ ነች፡፡ ከዓለም በብልጽግና የምትበልጣቸው 6 አገሮች ብቻ ናቸው፡፡ በዴሞክራሲ ደረጃም የለየላት በአምባገነን ሥርዓት ሥር ያለች አገር መሆኗን ጥናቱ ያሳያል፡፡ ወደድንም ጠላንም እውነታው ይህው ነው፡፡ አውቀን እንታረም፡፡ ይህ በተሳሳተ የታሪክ ጎዳና መጓዝ  ለአገርም፣ ለሕዝብም ለኢህአዴግም ከባድ ዋጋ የሚያስከፍል እንዳይሆን እንጠንቀቅ እያልን ባንደማመጥ ደግመን ደጋግመን እንናገራለን፡፡

 

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

ህዳር 14 ቀን 2ዐዐ3 ዓም

አዲስ አበባ

Continue reading …

   ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Continue reading …
[caption id="attachment_10769" align="alignnone" width="320" caption="የኔሰው ገብሬ"][/caption]

አንተም እንደ የሱስ
የኔሰው ገብሬ

አንተ ያገሬ ልጅ
እስኪ ልጠይቅህ
የነጻነት ትርጉም
እንደምን አስተዋልህ
በመለሰ ዘመን
ለጥብሥ ያበቃህ
እኔ በሚገባኝ
የሱስ ብቻ ነበር
ባልሰራበት ሐጢት
ራሱን የሰዋ
ያውም ለዓመጹበት
እጅጉን ይገርማል
አንተም መሰዋትህ
በኢትዮጵያዊነት
ሞትማ ይመጣል
ሁሉን አስተካካይ
አንተ ያገሬ ልጅ
እስኪ ልጠይቅህ
የነጻነት ትርጉም
እንደምን አስተዋልህ
በመለሰ ዘመን
ለጥብሥ ያበቃህ
ዋጋ ከፍሎዋል አሉ
ብዙ ኢትዮጵያዊ
ለፍትህ ለነጻነት
ያንተ ረቀቀ እንጅ
ለነጻነት ስትል
እንደ ወርቅ ማዕድን
በእሳት ውስጥ መንጠርህ::

©ለምለም ጸጋው፣ ለ የኔሰው ገብሬ መታሰቢያ የተጻፈ፣ህዲር 7 ቀን 2004 ዓ/ምህር

“ፍትህና ዱሞክራሲ ሌለበት አገር አልኖርም በሚል ምክንያት ራሱን በእሳት አቃጥሎ የገደለው መምህር የኔሰው
ገብሬ የቀብር ስነስርአት ተፈጸመ፣ ህዲር 5 ቀን 2004 ዓ/ም” (http://www.ethiopatriots.com/images/be%20esat%20meqatel%20111115.pdf)

Continue reading …

ከሁሉም በፊት በወያኔው ኢሰብኣዊ አገዛዝ ተንገሽግሾ ሰውነቱ ላይ ቤንዚን በማርከፍከፍ ይህችን የደም ምድር ኢትዮጵያ በገዛ ፈቃዱ የተሰናበተውን ወንድማችንና ልጃችንን መምህር የኔሰው ገብሬን የከፈለውን መስዋዕት ፈጣሪ እንደአቤል መስዋዕት ቆጥሮ መንግሥተ ሰማይን ያውርስልን ማለት እፈልጋለሁ፡፡ ካህናት እንዳይታዘቡኝ አንድ ሁለት ቃላትን ልናገር፡፡

[caption id="attachment_10769" align="alignleft" width="320" caption="የኔሰው ገብሬ"][/caption]

     ‹የኔሰው ራሱን አጠፋ› ብዬ ለማመን ይከብደኛል፤ አልችልምም፡፡ እርግጥ ነው ራሱን አጥፍቷል፡፡ ግን ለምን? ይህ ወጣት አስተሳሰቡን እንደብዙ ወጣቶች ለሆዱና ለጠባብ ሥጋዊ ፍላጎቶቹ ለውጦ ኢትዮጵያን ቢክድ በአፍታ ሚሊዮነር ሊሆን በቻለ ነበር – ልማታዊ ነጋዴ፣ ልማታዊ ኢንቬስተር፣ ልማታዊ የሥራ ሂደት ባለቤት፣ ልማታዊ የኢሕአዴግ የወጣት ሊግ፣ ልማታዊ የአነስተኛና ጥቃቅን ኢንዱስትሪ ባለቤት… ቢሆን ኖሮ ቢጠሩት የማይሰማ ዲታ በሆነ ነበር – እንኳን ቀረበት፡፡ የተሻለውን መረጠ፡፡ ከዚህ ሁሉ ግን የኅሊናው ታዛዥ ሆነና በደልንና ኢፍትሓዊነትን በሰላማዊ መንገድ ለመዋጋት ቆርጦ ተነሳ፤ ባዶ ዕጁን በፍቅር ሰባኪ አንደበቱ ብቻ ተዋጋቸው፡፡ ብዙ ጮኸ፡፡ ፍትህና ነጻነት እንዲኖር ታገለ፡፡ ለዜጎች መብት ተከራከረ፡፡ ነገር ግን የጠበቀው ሳይሆን ያልጠበቀው እየተከናወነ ከሥራም ከነጻነትም ከዲሞክራሲያዊ መብትም ሳይሆን ሰሚ አጥቶ ሜዳ ላይ ቀረ፡፡ እናም ለሀገሩና ለወገኖቹ አንድ አቅሙ የሚችለውን ነገር ማድረግ እንደሚኖርበት አመነ፡፡ በዚያም እምነቱ  ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ምሥረታ አንዲት ጡብ – ከፕሮፌሰር አሥራት፣ ከአሰፋ ማሩ፣ ከፋንታሁን ወርቁና ከሌሎች ጥቂቶች በስተቀር እስካሁን ማንም በፈቃዳቸው ሊሰጧት ያልሞከሯትን አንዲት ጡብ በፅኑ መሠረት ላይ አኑሮ፣ የጀመረው የመብት ተሟጋችነትና የነጻነት ትግል ግን እንዳይቋረጥ ተማፅኖ ላይመለስ አልፏል፤ በኔ በኩል እንደኃጢያት እንዳይያዝበት ይልቁንም በየማነ አብ እንደተቀመጠው በክርስቶስ ደም የጸደቀ ፈያታይ አሁኑኑ በእግዚአብሔር ቀኝ እንዲቀመጥ እጸልያለሁ፡፡ እናም ይህ ወጣት አርአያ ሊሆነን ተነሳስቶ በወሰደው እርምጃ ራስን የማጥፋት ወንጀል እንደፈፀመ ቆጥሬ ልቃወመው የሚያስችለኝ የሞራል ድፍረት የለኝም፡፡ ስንፈራው የነበረው ነገር ድኾ ድኾ መምጣቱን ግን ልብ ይሏል፡፡ እንደቺንዋ አቼቤ የመጽሐፍ ርዕስ ”No Longer at Ease” ማለት ከአሁን ወዲህ ነው፡፡ ወያኔ ከእንግዲህ ባጭር ሊታጠቅ ይገባዋል፡፡ የዘራውን ለማጨድ፣ በሠፈረው ቁና ለመሠፈር ዐውድማውን ይለቅልቅ እንጂ የሀገር ሀብትና ንብረት ለፖለቲካ ሎቢስቶች(አሻሻጭ ደላሎች) እና ቢቢሲን ለመሳሰሉ ቅሌታም የዜና ማዕከላት በገፍ እየረጨ የበሬ ወለደ ነጭ ውሸቱን ቢነዛ ከአሁን በኋላ ፋይዳ የለውም፡፡ በሞተ ሰዓት ኢትዮጵያ  በብርሃን ፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ አራት የዓለም ሀገሮች ውስጥ  አንዷ ሆናለች ብሎ መናገርና ማስነገር ቀርቶ ወያኔ ዛሬም ይሁን ነገ ሥነ ሕይወታዊ ቀመሩን በድንገት ለውጦ ከእባብነት ወደርግብነት ተቀይሮ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማርና ወተት ከሰማይ ቢያዘንብ የሚያምነውም ሆነ የሚቀበለው የለም፡፡ የወያኔን ነጭ ውሸት ለለመድነው የዛሬው ውሸት ምንም ላይመስለን ይችላል፡፡  ነገር ግን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸውን እንደቢቢሲ ያሉ የዜና ተቋማትን ተንተርሶ እንዲህ እንደዛሬው ያለ ወራዳ ዜና ሲነገር በውነቱ ያሳዝናል፤ ሰው ሆኖ መፈጠርንም ያስጠላል፡፡ ሕግ የለም እንጂ ቢኖር ኖሮ ቢቢሲን ዘ ሄግ ፍርድ ቤት ወስዶ መገተር ነበር – ለነገሩ እሱስ የማን መሣሪያ ሆነና፡፡ የመጥረቢያ ልጅ መዘለፊያ አይደል ተረቱስ? አንደኛው አንባቢ አንደኛው ተርጓሚ!

እውነቱን ለመናገር ከማስታውሰው የቅርብ ጊዜ የፕሮፓጋንዳ ታሪክ እንደዛሬ ያዘንኩበት ጊዜ የለም፡፡ ቢቢሲን ያህል እንደመርግ የሚከብድ ታላቅ የዜና አውታር እንዲህ የመሰለ ውርደት ውስጥ ይገባል ብዬ በህልሜም ሆነ በዉኔ አስቤው አላውቅም፡፡ እርግጥ ነው በነጭና በጥቁር፣ ባደጉና ባላደጉ ሀገሮች መካከል አድልዖ እንደሚያደርግ ብዙ ጊዜ ታዝቤያለሁ፡፡ የምዕራባውያን ጥቅምና ፍላጎት ሲነካ ቀኑን ሙሉ ብቻ ሳይሆን ሣምንቱንና ወሩን በሞላ በዚያ ዜና ላይ ሲያላዝኑበት ይከርማሉ፡፡ በኢትዮጵያ የሚያልቅ የመቶ ሺህ ሰው ሕይወት በስዊድን በመኪና አደጋ ከሚሞት የአንድ አሟሟቱ ካልሆነ ሞቱ በፈጣሪ ዘንድ ብዙም ሀዘኔታን የማያስከትል ውሻ ሕይወት ይበልጥባቸዋል፡፡ ግነት አይደለም፡፡ ምንም እንኳን እንደዘይና በዳዊ ያሉ ታዋቂ ጥቁር ጋዜጠኞች በእስታፍነት አብረው ቢኖሩም – ቢቢሲዎች ጥቁር ሰው፣ ሰው መስሎ የሚታያቸው አይመስሉኝም ባጠቃላይ፡፡ በኢትዮጵያ የ97 ምርጫ ለምሳሌ ያ ሁሉ ሕዝብ ሲረግፍና የ85 ሚሊዮን ሕዝብ የዲሞክራሲ ሽል ሲጨነግፍ ከሴከንዶች ያለፈ ሽፋን አልጡትም፡፡ በወቅቱ አዝኛለሁ፤ ከአሁኑ ባይብስም፡፡ ሰዎቹ በሽተኞች ናቸው፡፡ በዘረኝነትም ይለከፉ በጥቅምና ፍላጎት ዋናው ባለጌና ደደቦች ናቸው – ልክ የሌለው ደደብነት፡፡ እነዚህ ሰዎች ሠልጥነናል የሚሉ ከሆነ፣ ሃይማኖት አለን የሚሉም ከሆነ በጣሙን ተሳስተዋል፡፡ የሠለጠነና ሃይማት ያለው ሰው፣ ሰው በጠቆረና በቀላ ወይም በኢኮኖሚ ባደገና ባላደገ ብሎ የዜና ሽፋን ቅድሚያና ትኩረት አይሰጥም፡፡ ስለዚህ መንገዱ ያላችሁ ንገሩዋቸው – ፈጣሪንም ኅሊናቸውንም እያሳዘኑ ነው፡፡ የኛስ ግዴለም፡፡ ነጻ በወጣን ጊዜ ነጻ እንወጣለን፡፡ ያኔም የነሱን እውነተኛ ማንነት እንነግራቸዋለን፤ የሚሰሙበት ጆሮ ካላቸው፡፡

የውሸቱ ንጉሥ ኢቲቪ ቢቢሲን ጠቅሶ ከደቂቃዎች በፊት እንደዘገበው፣‹ኢትዮጵያ፣ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ አራት የዓለም ሀገራት አንደኛዋ ናት፡፡ ይህ ዓይነት ዕድገት የዛሬ ሃያ ዓመት ቻይና ያስመዘገበችው ዓይነት ዕድገት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በምታሳየው ፈጣን ዕድገት ሥራ አጥነት እየጠፋ፣ ሕዝብ ከርሀብና ችግር እየተላቀቀ፣ሀገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ በዕድገት እየተመነደገች፣ የትራንስፎርሜሽኑ ዕቅድ በታሰበው መንገድ እየገሠገሠ … ሊገኝ የቻለው መንግሥት ባመቻቸው የኢንቬስትመንት ዕድል› ነው፡፡  በአግራሞትና በድንጋጤ ተውጬ ነው በትግስት የተከታተልኩት፡፡ ሰው ውሸታም መሆን ከፈለገና ኀሊናውን ለጥቅም ከሸጠ ለካንስ የማይዋሽ የውሸት ዓይነት የለም? እንዲህ ተዋሽቶ የሚበላ እንጀራ ገደል ይግባ፡፡ የፈረንጅ ሙሰኛ ደግሞ በጣም ያስቀይማል፡፡ የታዳጊ ሀገር ጋዜጠኛ ቢሆን እናዝንለት ይሆናል – ደመወዙ ስለማይበቃው ሊሆን ይችላል ብለን፡፡ ቢቢሲ ግን መቼም በሀገሪቱ የኑሮ ደረጃ የሚበቃቸውን ያህል ሳይከፍሏቸው አይቀሩም – ሰዎች ስንባል በደምሳሳው እምብርት ባይኖረንም፡፡ ታዲያ ወደዚህ ቅሌት ውስጥ ምን አስገባቸው? የተነገራቸውን በጥሬው ምናልባትም ‹ተሞኝተው› አመኑ ብንልስ ከገለልተኛ ወገን ለማጣራት እንዴት አልሞከሩም? ስንት ቢከፈላቸውስ ይሆን ይህን ያህል አንዲት ድሃና በዴሞክራሲ ዕጦት ምክንያት በስደተኞች ብዛት ከመጀመሪያዎቹ አምስት ሀገራት ውስጥ ያለች ሀገር በዓለም በዕድገት ከአራቱ አንዷ ናት ብለው የመሠከሩት? አሁን እኔ ቢቢሲን ለመክሰስ አቅምም ሆነ ችሎታ የለኝም፤ መቼም የሚኖረኝም አይመስለኝም፡፡ ባለችኝ ብቸኛ የጸሎት መሣሪያ ግን ልታገላቸው መብትም ምክንያትና ፍላጎትም አለኝ፡፡ የአቡነ ዘበሰማያት ቶር ደግሞ ለተናቁ ዋና ፍላጻ ነው – ሲወረወር አይታይኝም ሲወጋ እንጂ – ይላሉ አባቶች፡፡ በቅንነት ለምንለምነው ፈጣሪ ይስማንና እንደፈቃዱ ያድርግልን፡፡ ዱሮውንም ችግራችን እንዴትና ምን እንደምንጠይቀው በውል አለመረዳታችን እንጂ ‹የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትን የማይረሳ› አምላከ ኢትዮጵያ አያሳፍረንም ነበር፡፡ አሁን ግን ግዴላችሁም በየቻልነው መንገድ በቡድንም በተናጠልም እንበርታና ይህችን የጨለማ ዘመን ተባብረን እናንጋት፡፡ የኔን አቅም ከተናገርኩ ዘንድ በውጭ ሀገር ያላችሁና ለሀገሬ እቆረቆራለሁ የምትሉ ወገኖች ይህን መርዘኛ የውሸት ዜና ቢያንስ ለታወቁ ዓለም አቀፍ ተቋማት በያላችሁበትና በተቻላችሁ መጠን አጋልጡ፡፡ ‹ተደጋግሞ የተነገ ውሸት እንደእውነት ይቆጠራል› ‹አንድ ወሬኛ ያባረረውን ሺህ ፈረሰኛ ጦር አይመልሰውም› መባሉ የወሬን አደገኛነት ለማስገንዘብ ነው፡፡ ለጊዜው በወያኔ ተገዝግዛ በጣር በምትገኘው በእምዬ ኢትዮጵያ ፃዕረ-ሞት ይዣችኋለሁ፡፡ እንዴ? ልጆች የሏትም እንዳታስበሏት አደራችሁን፡፡ ውሸት ገደብ ሊኖረው ይገባል፡፡ ለውሸታቸው ለከት እንዲያበጁለት ንገሯቸው፡፡

እንዲህ በሉልኝ፡- የሰብኣዊ መብት ተሟጋቹ የኔሰው ገብሬ ብሶቱን ለዓለም ሕዝብ ለማሰማት የገዛ ሕይወቱን ቤንዚን አርከፍክፎ በማቃጠል የተሰዋው፣ ጋዜጠኛ እስክንድንር ነጋና ሌሎች በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ የተቃውሞ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ ተጠርጣሪ የፖለቲካና የኅሊና እሥረኞች በየዘብጥያው የታጎሩትና እየተሰቃዩ ያሉት ይሄን ዕድገት ተቃውመው ይሆን? በሉልኝ፡፡ እነዚያ የቢቢሲ ልማታዊ ‹ጋዜጠኞች› በኢሚግሬሽን ቢሮ አላለፉ ይሆን? በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ኢምግሬሽንን ያጥለቀለቁት ለቱሪስትነት ወደዱባይና ወደአካፑልኮ ቤይ ወደ ሆኖሉሉ ሊሄዱ ይሆን? በእግራቸውና በታንኳ፣ በበረሃና በባሕር ከመሞት መሰንበት ብለው ላያልፍላቸውና የዱር አውሬና የባሕር እንስሳት ቀለብ የሚሆኑት በየቀኑ ከኢትዮጵያ የሚሰደዱት ወገኖቻችን ይህን ‹ፈጣን ዕድገት› ጠልተው ይሆን? በሕዝብ የሚቀልድ ዋጋ ይከፍላል በሉልኝ፡፡ በእርግጠኝነትም ይከፍላሉ፡፡ ‹ቀበጥ አማት ሲሦ ብትር አላት› የሚለውን ብሂላችንን አስረዱልኝ፡፡

እነዚያን ሌቦች የቢቢሲ ጋዜጠኞች እንዲህም በሏቸው፡- ሕንጻ የዕድገት መለኪያ አይደለም፤ ሕንጻ አይበላም፡፡ መንገድም አይበላም – በዕድገት ፍጥነት ከአራቶች ውስጥ የሚያስገባ በቂ መንገድም የለንም፡፡ ፋብሪካ የዕድገት መለኪያ አይደለም፡፡ አንድ ፋብሪካ ባለቤቱ ቢያንስ አንድ ነው፡፡ ቀጥሮ የሚያሠራቸው ግን ብዙ ድሆች ናቸው፡፡ ያ ቀጣሪ በአብዛኛው ሌባ ነው፡፡ የገዛ ሆዱን እየሞላና በየሣምንቱ አውሮፓና አሜሪካ እየተንሸራሸረ ሠራተኞቹ ግን የራስ ምታት አስፕሪን መግዣ እንኳን እያጡ ጭንቅላታቸውን በእራፊ ጨርቅ ጠምጥመው ነው የርሱን የማይሞላ ከርስ ለመሙላት በላብ እየተጠመቁ በሥራ ሲፈጉ የሚውሉት፡፡ እነዚህ ዘመናዊ ባሪያ ፈንጋዮች የሚሰጡት የእማኝነት ቃል ደግሞ ባብዛኛው ‹የዐይጥ ምሥክር ድንቢጥ› እንዲሉ ዓይነት ነው፡፡  ‹ቦሃ ላይ ቆረቆር፡፡› የዘንድሮው ኢትዮጵያዊ ላይ ሀብታም ኢንቬስተርነት ተደምሮ፡፡ የቀን ጉዳይ ነው እንጂ ሁሉንም እናውቀዋለን፡፡ ወያኔን ማን ቀጥ አድርጎ እንደያዘው ይታወቃል፡፡ ገንዘብ ብቻውን የማያድንበት ጊዜ ደግሞ እየመጣ ነው፡፡ ግን ግን ሁሉም ዋጋውን ያገኛል፡፡ ዛቻ እንዳይመስላችሁ፡፡ ቀኑ ቀርቧል፡፡ እንዲህ የምንጮህ ወገኖች ደግሞ እንደዮሐንስ መጥምቁ የጽድቅ የክብር አክሊል ለማግኘት አልመን ወይ ተመኝተን አይደለም፤ በጭራሽ!  ጨለምተኞች ሆነን የማስበርገግ ዓላማ ኖሮንም አይደለም – አንዳንዶቻችን እንዲያውም ራሳችን በርጋጎች ነን – በየስርጓጉጡ ተደብቀን እንደዕንቁራት የምንጮህ፡፡ እንደምንም እንጩህ ጩኸታችን ግን ትክክለኛ ጩኸት ነው፡፡ ደግሞም ይህን ዕወቁልን – የምንጮኸው  የሚታየን ነገር በሉ በሉ እያለ ዕረፍት ስለሚያሳጣን ነው፡፡ አንዳንዶች በሟርተኝነት እስኪፈርጁን ድረስ  እንዲህ ተጨንቀን የምናስጨንቃችሁ ለ‹በጎ› እንደሆነ ቁጠሩልን፡፡  አለዚያማ ነገር ዓለሙን ትቶ መተኛትን ማን ይጠላል? … እናም አትዘኑብን፡፡

 ‹ኢ(ይ)ድኅን ንጉሥ በብዝኃ ሠራዊቱ›፡፡ ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፡፡ ቀድሞ የተነገረ ወንጌላዊ ቃለ ግሣጼ ነው፡፡ በሠራዊት ብዛትና በሀብት ክምችት መዳን ቢቻል ኖሮ ሌሎቹ ሁሉ ቀርተው ‹የዓለምን የገንዘብ ልውውጥ በወርቅ ሣንቲም አድርጌ አውሮፓንና አሜሪካንን በእንትናቸው ቁጭ አደርጋቸዋለሁ!› ብሎ ከመዛቱ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ዋጋውን ያገኘው ሙኣማር ጋዳፊ እስከወዲያኛው በሊቢያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ እንደሸና በኖረ ነበር – እውነቴን ነው ፤ ከሌሎች ቃላት ይህኛው ይቀላል ከሚል ነው እንጂ የርሱ ነገር ከዚያም በላይ ነው፡፡ ጠንቁ ለኛም ደርሶ እንዲያውም ሲያስመልሰው ይደርና ዕድሜ ለመለስ የኛ ወገኖችም በፈላ ውኃ እስከመቀቀል የደረሱበት ዘግናኝ አገዛዝ መሥርቶ ነበር፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው የክፉ መጨረሻ ያው ክፉና ክፉ ብቻ ነውና ብድር በምድሩን በውርደት አገኛት – ሲያንሰው ነው፡፡ ብዙዎቻችን ማገናዘብ እየተሳነን እንጂ የዚህች ዓለም እውነት አትለወጥም፡፡ በሠይፍ የገደለ በሠይፍ ይገደላል፡፡ ያሰቃዬ ይሰቃያል፡፡ የገፈፈና የቀማ ይገፈፋል ይቀማልም፡፡ ግና የዱባ ጥጋብ ካለስንቅ እንደሚያዘምት ሁሉ ለጥቂት ዓመታት በምናገኛት ‹ዕድል› ተጠቅመን ጥሩ ታሪክ መተው ስንችል ያችን አለመላው አበለሻሽተን እንዲያውም ዳፋችን ለብዙዎች ይተርፍና አይሆኑ ሆነን እንቀራለን፡፡ የመለስና የመሰሎቹ መጪው ዕድልም ከባሕርይ አባቶቻቸው ከነሣዳምና ከነጋዳፊ የሚዘል አይደለም፡፡ የቀንን ፍርድ የሚያውቅ አደብ ይገዛል፡፡

ለነዚያ የቢቢሲ ጋዜጠኞች ግን አደራ ይህችን ደብዳቤ አድርሱልኝ፡፡ እንርገማቸው፡፡ ዘራቸው ብኑን ይሁን፡፡ ከኔ ደም ተንቅሮ የተሠጣቸውን የመዋሻ ገንዘብ ሳይበሉት ይቅሩ፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ ብድራታቸውን አሁኑኑ ይክፈላቸው፡፡ ጥቁር ውሻ ይውለዱ – እንደነወያኔዎቻችን( እነወያኔዎች ወልደዋልና!እመለስበታለሁ)፡፡

የኢሜል ሣጥኔ ለስድብ ቦታ የለውም – ለገምቢ አስተያየት ግን እነሆ አድራሻየ፡ yiheyisaemro@gmail.co

Continue reading …

አጭር መልእክት መጻፍ አሰኘኝ – ደካክሞኝ ልተኛ ስል፡፡ ከበፊትም የነሱና የኛ ታሪኮች መመሳሰል በጣሙን ያስደንቀኝ ነበር፡፡ የነሱና የኛ ችግር ተቀራራቢ እንደሆነ በተለይ ካለፉት ስምንትና ዘጠኝ ወራት ወዲህ እነሱ እየደረሰባቸው በሚገኘው የጭፍጨፋና የግድያ የሰቆቃ ኑሮ  መገንዘብ ችያለሁ – የሁለታችንም አሳዳሪ ጌቶች ክፉኛ ጨካኞች ናቸው – ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው፡፡ እነሱ እንደሕዝብ በጣም ጠንካሮች ናቸው፡፡ እኛ ግን የነሱን የብቃት ደረጃ ለማግኘት ገና በውል ያልተገለጠልኝ  የጊዜ ርዝማኔ የሚያስፈልገን ይመስለኛል፡፡ እነሱ የማይቀርላቸውን የታሪክ ዕዳ እየተወጡ ናቸው፡፡ እኛ ግን ቋቱ አልሞላ ብሎ የተቸገርን ይመስል ሞልቶ መፍሰስ ከጀመረ ከሃያ ዓመታት ለበለጠው የመከራና የግፍ ዘመን ተመቻችተን እንደተቀመጥን አለን፡፡ ይሁን – ካመጣው ምን ይደረጋል? አንዳንዱ ቋት እንደሽንቁር በርሚል ሞላ ሲሉት እየጎደለ ለተወሰነ ጊዜ ማስቸገሩ ጥንትም ነበር፡፡ እንደተቀደደ ሳይበጅ ወይም ሳይጠገን የሚቀር የግፍ ቋት ግን ኖሮ አያውቅም፡፡ በሰባ ዓመትም፣ በዐርባ ዓመትም፣ በሠላሳ ዓመትም፣ በሃያ ዓመትም፣ እንደየሁኔታው ከነዚህ ከጠቀስናቸው የጊዜ አጥቆች በላይም ሆነ በታች ለሚረዝምና ለሚያጥር ጊዜ ብዙ ሕዝቦች የመከራ ገፈት ሲጋቱ ቆይተው በመጨረሻው ግን ነጻ መውጣታቸውን ታሪክ በተለያዩ አጋጣሚዎች አረጋግጦልናል – ከሥቃይ ፋብሪካ ማፈሪያ የዓለም ዜጎች መካከል ሂትለር፣ ሙሶሊኖ፣ቻውቼስኮ፣ሣዳም፣ ጋዳፊ… ጥቂቶቹ ግን ከዋናዎቹ ውስጥ የሚመደቡ ናቸው፡፡ ይህ ሲባል ግን እንደተኛን እንክረም፣ የኛን ሥራ በኮንትራት ወይም በ‹ፓርታይም› ለውጪ ሠራተኞች እናሠራው(out source)  ለማለት እንዳልሆነ ልብ ይሏል፡፡ ‘አብናቶቼና ወንድምቶቼ’ ሆይ! – ባለቤት ካልጮኸ ጎረቤት አይረዳም፡፡ የጮኹ ተጠቀሙ – ያልጮኹ ወይም በቅጡና ሥርዓት ባለው አዋጭ መንገድ ያልጮኹ  በገዛ መንግሥቶቻቸው እንደእባብ ራስ ራሳቸውን ተቀጠቀጡ፡፡ ልዩ የታሪክ አንጓ! የመንን እንመልከት፤ ባሕሬንን እንመልከት፤ ሱዳንን እንመልከት፤ ኢራንን እንመልከት፤ ጆርዳንን እንመልከት፤ኢራቅን፣አፍጋኒስታንን፣ፓኪስታንን፣በተለይ ግሪክንና ጣሊያንንና መላው አውሮጳን፣አሜሪካንን፣ናይጄሪያን፣ኢትዮጵያን … በእውኑ በአሁኑ ወቅት የመከራ ጥንስስ የማይንተከተክበት፣ የዕልቂት ድግስ ብፌ ያልተዘረጋበት የዓለም ሀገር አለን? እነመምሩ ‹ያድኅነነ እመዓቱ፣ ይሠውረነ በምሕረቱ በእንተ ማርያም ወላዲቱ…› የሚሏትን ጥዑመ ዜማ ማመልጠን አሁን ነበር፡፡ ክፉ ጊዜ እየመጣ ነው – በተለይ ለኢትዮጵያና በኢትዮጵያ!!!! (ብዙ ሰው ተስፋ ከመቁረጡ የተነሳ በተለይ አሁን አሁን ብቻውን እያወራ መሄድ ጀምሯል ብቻ ሳይሆን ብቻውን የማያወራ እንደበሽተኛ የሚቆጠርበት ጊዜ ላይ ሳንደርስ አልቀረንም፤ ያልተነካ ግልግል ያውቃል ነውና እንዳይፈረድባችሁ ውሸቱን ነው ብላችሁ አደራችሁን በኔ እንዳትፈርዱ፡፡ የማን ዓለመኛ ነው ሰው ሁሉ በኑሮና በፍትህ ዕጦት ዐብዶ እሱ ሳያብድ የሚቀር? ከእግዚአብሔር በስተቀር ሁሉም ስለሰላም የሚሰብክ በሀገርም ይሁን በውጭ ያለ ዜጋ አሸባሪ ከሆነ ከእንግዲህ ምን ቀረን? ኦባንግ ኦ. ሜቶ ሳይቀር አሸባሪ ሲሆን? ምን አለፋችሁ ለአቅመ-አሸባሪነት ካልደረሱ የጋንዲ ማዋለጃ ሆስፒታል ሕጻናት በስተቀር ቆሞ የሄደው ሁሉ አሸባሪ ሆኗል – አሁንስ መለስ እያሳዘነኝ ነው፡፡ በጤናው ነው ብላችሁ ነው? የቅንፉ ሃሳብ አባሪ እንጂ መነሻየ አይደለም፡፡)

አዎ! ‹ባለቤት  ካልጮኸ ጎረቤት አይረዳም፡፡› ሦርያውን መጮኽ (መሞትም) ከጀመሩ ዓመት ሊጠጋቸው ነው፡፡ በይፋዊ ግምት እስካሁን ከ3600 በላይ ዜጎች በሥልጣን አልጠግብ ባዩ የአሲድ ማለቴ የአሳድ ጨፍጫፊ መንግሥት ተገድለዋል፤ ከሰባ ሺህ በላይ ዜጎች በዬእሥር ቤቶች ታጉረው ለሞትና ለእንግልት እንደተዳረጉ ይነገራል፡፡ ሰላማዊ ኑሮና ሥራ ብቻ ሳይሆኑ የዜጎች ሕይወትና የሀገር ኅልውናም አደጋ ላይ ወድቀዋል፡፡ በሠፈነው የአድልዖ አገዛዝ ምክንያት በእህህ የመከራና የቁጭት ሕይወት ሲገፉ የነበሩ የአንዲት ሀገር ዜጎች ወደባሰ የመቃቃር ሁኔታ እየገቡ ይመስላሉ፡፡ የሀገሪቱ የጦር ሠራዊት ከነበጀቱ የተሰለፈው የውጭ ጠላትን በታንክና በጀት ለመውጋት ሳይሆን የዴሞክራሲ መብቱን በሰላማዊ ሰልፍ  ሊጠይቅ አደባባይ የወጣን 88 ከመቶ የሚሆነውን የሀገሪቱን ሕዝብ ለማንበርከክ ነው እየተባለ ነው፡፡ የአፍሪካ ወያኔ በአፍሪካ ቀንድ – በኢትዮጵያ – የመካከለኛው ምሥራቅ ወያኔ ደግሞ በሦርያ፡፡ የሚገርም አጋጣሚ፡፡ የሠመረ የታሪክ መመሳሰል ይሏል ይህንን ነው፡፡ እርግጥ ነው የኛ ድህነትና መለኪያ በሌለው ሁኔታ መጠኑን ያለፈ ሀገራዊ ጉስቁልና ለዚህ ዓይነቱ ውድድር እንኳን አላበቃንም፡፡  በቁንጅና ውድድር መሸነፍ አንድ ነገር ነው፡፡ በፉንጋነት ውድድር መሸነፍ ደግሞ ሌላና የሚቆጭም ነገር ነው፡፡ የሦርያ ሕዝብ እኮ ቢያንስ እንደኛ ሀገር አልባ ሆኖ አይደለም በአውሬው ሃፊዝ አላሳድ ልጅ በለግላጋው አውሬ በባሽር አላሳድ እየተመተረ ያለው፡፡ ተጨማሪ ነጻነት ለማግኘት መብቱን ጠየቀ – ልክ እንደኛው የጥይት መልስ ተሰጠው፡፡ በየቀኑ እያለቀ አንዳች ተስፋ ሳይቆርጥ የነጻነት ትግሉን ቀጠለ፡፡ አሁን ሰሚ እያገኘ ነው፡፡ የዐረብ ሊግ ወንድ ሊወጣው ነው – ሴትም ጭምር፡፡ ይሄ የ‹ጄንደር› ነገር ምን ይሻላል!

     የዐራብ ሊግ ከሦርያ ሕዝብ ጎን መቆሙን በዛሬ ውሎ አስቸኳይ ስብሰባው ገልጾለታል፡፡ ደስ ይላል፡፡ ይህ ጅማሮ ፍሬ እንዲይዝ በበኩሌ ፈጣሪን ተማጥኛለሁ፡፡ የተጀመረ የማያልቅ፣ በርትቶ የታገለ የማያሸንፍ የለምና ይሄውና ‹የመጨረሻው መጀመሪያ› የነጻነት አብሪ ጥይት ዛሬ በካይሮ ተተኮሰች፡፡ …

     በዚህ ስብሰባ ማጠናቀቂያ ከአንዲት ሴት የፖለቲካ ተንታኝ ትሁን ዜና ዘጋቢ ያዳመጥኩትና በፊትም የማውቀው ጉዳይ ግን ከነከነኝ – የሴቷን ማንነት አሁን ረስቼው ነው ይቅርታ፡፡ የችግራችን መመሳሰልም ፍንትው ብሎ የተገለጠልኝ ያኔ ነው – ለመጻፍም ያነሳሳኝ፡፡

     የሦሪያ መንግሥት ተቃዋሚ ወገኖች  ኮከባቸውና ክፍላቸው እንደኛዎቹ ተቃዋሚዎች የአንዳቸው ካንዳቸው አይገጥምም አሉ፡፡ ይህ ዓይነቱ የተቃዋሚዎች መረገም ደግሞ ለጨቋኞች ሠርግና ምላሽ ነው፡፡ ከጮማና ውስኪ በበለጠ የሚያጣጥሙት ምናባዊ የሥጋ ማድለቢያ ምግብ ቢኖር የተቃዋሚዎቻቸው መለያየት ነው፡፡ በተቀናቃኞቻቸው መካከል ሽብልቅ በመቀርቀብ ለመፈረካከስና እስከተቻለም ድምጥማጣቸውን ለማጥፋት የማያደርጉት ጥረት የለም፡፡ ይሄ ጉዳይ የአደባባይ ምሥጢር ነው፤ ተቃዋሚዎች ግን ለዚህ ዓይነቱ ሤራ በራቸውን የሚዘጉና የሚጠነቀቁ አይመስሉም፡፡ ሞኝነት ወይስ ፖለቲካዊ መርገምት? ምን ይሻላቸው ይሆን?

      በመቶዎች የተቧደኑት የሦርያ ተቃዋሚዎች የአሳድን መንግሥት ከሚጠሉና ከሚፈሩ ይልቅ በበለጠ እርስ በርስ ይፈራራሉ፤ ይጠላላሉ፤ ይጠላለፋሉም ይባላል፡፡ በዓለም የፖለቲካ መድረክ ከበሬታን የሚያስነፍጋቸው ትልቁ የኪሣራቸው ምንጭ ይሄ ወጡ ሳይወጠወጥ ቂጢጥ የሚያደርጉት የሥልጣን ሽሚያ ወስከምቢያ ጉዳይ ነው እየተባሉ ክፉኛ ይተቻሉ፡፡ ለዝንጀሮዋ ተረት ቁብ ያላቸው አይመስሉም – ‹ቀድሞ የመቀመጫየን› ያለችውን፡፡ ሦርያን ለጨፍጫፊው አሳድ አሳልፎ ሰጥቶ፣ ራስን በግዞት ካይሮና በመላው የዐረብ ምድር በትኖ ገና ለገና – ዛር ወርዶ ተንቀጥቅጦ – ዘንቦ ተባርቆ – ለሚገኝ የሥልጣን ፍርፋሪ ከዋናው ጠላት በመረረ ሁኔታ የገዛ የትግል አጋርን መጥመድ የጤነኝነት ሳይሆን የወፈፌነት ምልክት መሆን አለበት ብቻ ሳይሆን በእርግጠኝነት ነው፡፡ ይህ ደዌ ሦርያን ብቻ ሳይሆን የኛዋን ኢትዮጵያን ጨምሮ የብዙ ሀገሮችም የታወቀ ግን መድሓኒቱ የጠፋለት የበሽታዎች ሁሉ ንጉሥ ኃያል ወረርሽኝ ነው፡፡  በጠበል አይድን፤ በክኒን አይድን፤ በመርፌ አይድን፤ በመታሻ ቅባት አይድን፤ ዋገምት አይነቅለው፤ ወጌሻ አያገኘው፤መጣፍ ገላጭና ድቤ መች አያውቁት… እንዲሁ በአሰለጦች የታወረ ልቦና ውስጥ ተሸጉጦ ሀገርና ሕዝብን ያምሳል፤ በ‹ላም አለኝ በሰማይ› የሕልም እንጀራ የአንዲት እናት ልጆችን እርስ በርስ ያባላል፡፡ እንዲያ ባይሆንማ ኖሮ አሁን ማ ይሙት የባሽር አላሳድ ማለትም የመለስ ዜናዊ ቅልብ የቁርጥ ቀን ጦር ሕዝብን ያለ አንዳች ርህራሄ ለመጨፍለቅ አነጥንጦ በሚገኝበት ሁኔታ የሥጋ ቅርጫ መደብ ወይም የዕድርና የሰንበቴ ማኅበር ይመስል በመቶና ከዚያ በላይ በሚቆጠር የተቃውሞ ጎራ ተሰልፎ መወራከብ እንደአዋጭ የትግል ሥልት መያዝ ነበረበት? በእውነቱ በየሀገሩ የሚታየው ይህን መሰሉ የጅልነት ሥራ በእጅጉ ይገርማል፡፡ ከዚህ ዓይነቱ የሞኞች አባዜ የሀገራችን የተቃውሞ ኃይላት ትልቅ ትምህርት እንደሚቀስሙ አምናለሁ፡፡ ዝንጀሮዋ ምን አለች? ‹ቀድሞ የመቀመጫየን›፡፡

 ማበጠሪያ የሚያስፈልገው ፀጉር ያለው ነው፤ መተኛት የሚችል ሃሳብ የሌለው ነው፤ ማንቀላፋት የሚችል እንቅልፉ የመጣ ነው፤ ማሰብ የሚችል አእምሮ ያለው ነው፤ ትናንትን ከነገ የሚያመዛዝን ትናንት ወዲያን ከነገ ወዲያ ማገናዘብ የሚችል አስተዋይ ነው፡፡ የሰውን ደምና ሕይወት በሥውርና በግልጽ እየገበሩ በሸርና በተንኮል የሚገኝ ሀብትና ሥልጣን ነገና ከነገ ወዲያ የገዛ ትውልድን አንገት እያስደፋና ዐፅምን  እያስወቀሰ ክፉ ስምን ከመቃብር በላይ የሚያኖር አደገኛ መርዝ ነው፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ‹ነገም ሌላ ቀን ነው›፤ እንደትናንቱ ሁሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሰማይ ያረገዘውን በገደምዳሜ የተናገርሁ ይመስለኛልና ‹ሰንበትን እሑድ› ማለት እንደማያስፈልገኝ ለሚመለከተው ወገን ጠቁሜ ሃሳቤን ልቋጭ፤ ቋጨሁ፡፡

መሰነባበቻ፡-

እዚያ ማዶ ሆኖ ክፉ ሰው ተጣራ፤

እዚህ ማዶ ሆኖ ክፉ ሰው ‹ወይ› አለው፤

ጎበዝ ተጠራጠር ይህ ነገር ለኛ ነው፡፡

                    ይሉ ነበር አባቶች፡፡

(ውይ፣ ሞት ይርሳኝ፤ በበቀደሙ ጦማሬ አንዲት መናኛ ስህተት ሠርቻለሁ፡፡ ያቺውም በሠንጠረዡ ውስጥ የሽቦ(እስታፋ እሚሉት) ዋጋ አሁን 30ብር ከ10 ዓመት በፊት 3 ብር ማለት ሲገባኝ ሁለቱንም 30 ማለቴ ነበር፡፡ ለማንኛውም አሁን ከይቅርታ ጋር አረምኩት፡፡)

Continue reading …
  •  ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ ጋዜጠኛ ዐብይ ተክለማሪያም፣ ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ፣ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም በክሱ ውስጥ ይገኙበታል
  •  እስረኞች ቶርቸር እንደተፈፀመባቸው ገልጸዋል

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ /አንድነት/ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት አላፊ አቶ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 24 ሰዎች በዛሬው ቀን ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ በዛሬው ዕለት ከሰዓት በኋላ የተሰየመው የፌድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛው ወንጀል ችሎት 8 ተከሳሾች ቀርበው የክስ ቻርጅ የተቀበሉ ሲሆን ከተራ ቁጥር 9-24 ያሉት ተከሳሾች በሌሉበት ክሳቸው ተመስርቶአል፡፡

በቁጥር የፍ/ሚ/ፌ/ማ/መ/ቁ 00180/04 ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ.ም. በቀረበው የክሰ ቻርጅ ላይ አቶ አንዱዓለም አራጌ ዋለ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን ገ/ኪዳን፣ አቶ ዮሃንስ ተረፈ ከበደ፣ አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ በረደድ፣ አቶ ምትኩ ዳምጠው ውርቁ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፈንታ፣ አቶ አንዱዓለም አያሌው ገላው በአካል ፍርድ ቤት ተገኝተው የክስ ቻርጅን የተቀበሉ ሲሆን የቀሩት በሌሉበት ክሱ ቀርቧል፡፡ በአካል ያልቀረቡ ተከሳሾች በጋዜጣ እንዲጠሩ ዐቃቢ ህግ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

በጋዜጣ እንዲጠሩ የተከሰሱት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንገር፣ ውቤ ሮቤ፣ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ፣ አቶ መስፍን አማን፣ አቶ ዘለሌ ፀጋ ስላሴ፣ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም፣ አቶ አበበ በለው፣ አቶ አበበ ገላው፣ አቶ ንአምን ዘለቀ፣ አቶ ኤልያስ ሞላ፣ አቶ ደሳለኝ አራጌ ዋለ፣ ኮ/ሌ አለበል አማረ፣ አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽና ጋዜጠኛ ዐብይ ተ/ማሪያም ናቸው፡፡

በችሎቱ ላይ አቤቱታ ያቀረቡት ሁለተኛ ተከሳሽ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል መምህር ናትናኤል መኮንን እንዳሉት “በማዕከላዊ እስር ቤት ግፍ ተፈጽሞብኛል፡፡ ከወንጀል ምርመራ ኋላፊ እስከ ታችኛው ወንጀል መርማሪ ሠራተኛ አንድ ላይ ሆነው ልብሴን ሙሉ በሙሉ አስወልቀው ውሃ እየደፉብኝ ለ23 ቀን ሙሉ አሰቃይተውኛል፡፡ እነሱ የሚፈልጉትን እንድናገር ጠይቀውኝ አልናገርም በማለቴ 7 ቀን ምግብ እንዳልበላ፣ እነሱ የሚሉኝን የማልናገር ከሆነ አትቀመጥም አትተኛም ብለው በቁም እንድሰቃይ አድርገውኛል፡፡ እጄን ወደ ኋላ አስረው አሰቃይተውኛል፡፡ የፌድራል ሰባአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር እኔ በስቃይ ላይ ባለሁበት ወቅት ሌሎች ክፍሎች ጎብኝተው እኔን በመዝለል በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በበርካታ ዜጎች ላይ የሚፈፀመውን ግፍ እንዳልተፈፀም ለመሸፈን በመሞከር ትብብር አድርገዋል፡፡ በጊዜ ቀጠሮ በምቀርብበት ፍርድ ቤት አመልክቼ በዛሬው ዕለት የምርመራ ኋላፊው ቀርበው እንዲያስረዱ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ሲሆን፣ ቀርበው ከማስረዳት ይልቅ በሌላ በኩል እኔን እዚህ ፍርድ ቤት አቅርበውኛል” በማለት ያመለከቱ ሲሆን ፍርድ ቤቱ “ወደ ፊት በክርክሩ ወቅት እንሰማዋለን” በማለት አልፈውታል፡፡

ተከሳሾች ጠበቃ ማቆም የሚችሉና የማይችሉ መሆኑን ጠይቀው አንችልም ላሉት መንግስት እንዲያቆምላቸው አዟል፡፡ ተከሳሾቹ ከጠበቃቸው ጋር ተመካክረው ለህዳር 5 ቀን 2004 ዓ.ም. እንዲቀርብ ቀነ ቀጠሮ በመያዝ የዕለቱ ችሎት ተጠናቋል፡፡

በተያያዘ ዜና በትላንትናው ዕለት የተሰየመው ፌድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛው ወንጀል ችሎት “በአሸባሪነት” ክስ የተመሰረተባቸው በእኔ ኤልያስ ክፍሌ ክስ የተከሰሱት የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዘሪሁን ገ/እግዚሐብሔር፣ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ ጋዜጠኛ ርዕዩት ዓለሙ እና ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ የዐቃቢ ህግ ምስክሮች ተሰምቷል፡፡ በዚህ የክስ መዝገብ ከ1-6 የቀረቡት ምስክሮች ሰራተኛ፣ ሊስትሮ የሚሠሩና ዕቃ በማዞር በመሸጥ የሚተዳደሩ መሆናቸውን አድራሻቸውን ሲገልፁ ተደምጠዋል፡፡ አንዱ ምስክር መምህር ሲሆን ሦስቱም ምስክሮች ጋዜጠኛ ውብሸትና ርዕዮት ዓለሙ ከኮንፒተር ጹሑፍ አውጥተው ለፖሊስ ሲሰጡ በታዛቢነት ማየታቸውን፣ ወረቀቶቹን በእንግሊዘኛና በአማርኛ የተፃፉ መሆናቸውን እንጂ ይዘታቸውን እንደማያውቁ ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስተር መለስ ዜናዊ በቅርቡ ባደረጉት ንግግር የማያወላዳ ማስራጃ በያንዳንዱ ተከሳሽ ላይ ይቀርባል ተብሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ እስካሁን ባለው የፍርድ ድራማ ሂደት እንደምንረዳው የፍትሕ ተቋማት ተቃዋሚን የማጥቂያ መሳሪያ ከመሆን ያለፈ ጉዳይ አለመሆኑን ነው፡፡

ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች በፖለቲካ ልዩነት ተቻችለው የሚኖሩበት ሃገርና ተባብረው ችጋርና ድህነትን ለማስወገድ የሚሠሩበት ሃገር ለመፍጠር ትግሉ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ለዴሞክራሲና ለነፃነት ለሚደረገው ትግል በሞራል፣ በሃሳብና በገንዘብ ይርዱ፡፡ የያንዳንዳችን ጥርት ለትግሩ የራሱ ድርሻ አለው፡፡

ጊዜው የተግባር ነው!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የሕዝብ

(የአቃቤ ህጉን የክስ ቻርጅ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

 

Continue reading …

ሪፖርተር

[caption id="attachment_10582" align="alignleft" width="300" caption="ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ  ና  አቶ ገብሩ አስራት"][/caption]

ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ1993 ዓ.ም. ባካሄደው ጥናት በአገሪቱ ውስጥ ከሚታዩ ዋና ዋና ችግሮች መካከል ሙስና አንዱ መሆኑ ተጠቅሶ ነበር፡፡

ሙስና የአገሪቱ ችግር ነው የሚለው ይህ የኅብረተሰቡ አስተሳሰብ ከአሥር ዓመት በኋላም የተቀየረ አይመስልም፡፡ በ1993 ዓ.ም. የተቋቋመው የፀረ ሙስና ኮሚሽንም ሙስናን በመዋጋት ረገድ ከፍተኛ እምነት ተጥሎበት የነበረ ቢሆንም፣ በአገሪቱ የሚታየው ሙስና በዓይነትና በመጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መምጣቱን ታዛቢዎች ይገልጻሉ፡፡

እንደ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የመሳሰሉት ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚያወጧቸው ሪፖርቶችም ሙስና በአገሪቱ እየጨመረ መምጣቱን የሚያመላክቱ ናቸው፡፡ አገሪቱን የሚያስተዳድሩት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጭምር በሙስና ተዘፍቀዋል የሚለው ጉዳይ በኅብረተሰቡ ዘንድ መወያያ አጀንዳ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ ‹‹ይህ ሕንፃ እገሌ የሚባለው ባለሥልጣን ንብረት ነው፤ ይህ ቪላ እንትና የሚባለው ሚኒስትር ነው፤›› የሚል መረጃ ከአንዳንድ ውስጥ አዋቂዎች መሰማት የተለመደ ነው፡፡ ባለሥልጣናት በሙስና ተዘፍቀዋል የሚለው የሕዝቡ እሮሮ ግን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከመንግሥት በኩል በቂ ምላሽ ያገኘ አይመስልም፡፡

ኢሕአዴግ በሥልጣን ላይ በቆየባቸው ባለፉት 20 ዓመታት በሙስና ተጠርጥረው የተከሰሱ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል የቀድሞ ጠቅላይ ማኒስትር ታምራት ላይኔ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸው ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ በሙስና ጉዳይ ላይ ቁርጠኛ አቋም እንዳለው የሚያሳይ ነው በማለት አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በወቅቱ ገልጸው ነበር፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይ መንግሥት ዕርምጃ መውሰዱ በሙስና ወንጀል አንደማይደራደር አመላካች ውሳኔ መሆኑን ያመኑት ጥቂቶች አልነበሩም፡፡ ይህ የኅብረተሰቡ አመለካከት ግን በሂደት እየተሸረሸረ ሳይመጣ አልቀረም፡፡ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት በሙስና ወንጀል የተዘፈቁ አንዳንድ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ተከታትሎ ለፍርድ የማቅረብ ጉዳይ ትኩረት የተነፈገው ይመስላል፡፡ ባለሥልጣናቱ የፖለቲካ ልዩነት እስካልፈጠሩ ድረስ ያሻቸውን እንዲያደርጉ፣ የፖለቲካ ልዩነት ከፈጠሩ ግን በሙስና ተጠርጥረው የሚታሰሩበት ዕድል ሰፊ መሆኑን የሚናገሩት እነኚሁ ታዛቢዎች፣ ይህንን ሐሳባቸውን ለማጠናከር ከሕወሓት ክፍፍል በኋላ የአቶ ስዬ አብርሃን በሙስና ተጠርጥሮ መታሰር በምሳሌነት ይጠቅሳሉ፡፡

በአገሪቱ እየተስፋፋ የመጣውን የሙስና ወንጀል ለማስቆም መንግሥት ምን እየሠራ ነው? የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ የሚቀርብላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሙስናን መቀነስ የሚቻለው ኅብረተሰቡን በማስተማር እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ሰሞኑን ፓርላማ ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራርያ በሰጡበት ወቅትም ይህንኑ ደግመውታል፡፡ መንግሥት የሙስና ወንጀል ስለመፈጸሙ በቂ ማስረጃ ካለው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ወንጀለኞችን ተጠያቂ የማያደርግበት ምክንያት እንደሌለ የገለጹት ጠቅላይ ማኒስትሩ፣ ሙስናን በመቀነስ ረገድ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ከተፈለገ ግን ኅብረተሰቡን ማስተማር ግድ እንደሚል ያስረዳሉ፡፡

የዓረና ትግራይ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት ግን ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ሙስናን በመዋጋት ረገድ ቁርጠኝነት የጐደለው መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

ሙስና በአገሪቱ ውስጥ ስለመስፋፋቱ ራሱ መንግሥትም የሚያምነው ጉዳይ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ገብሩ፣ መንግሥት ችግር መኖሩን ቢያምንም በተጠርጣሪዎች ላይ ዕርምጃ የመውሰድ አቅምም ሆነ ፍላጐት የሌለው መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

እርሳቸው እንደሚሉት በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ የሚታየው ሙስና በከፍተኛ ባለሥልጣናት ጭምር የሚፈጸም ቢሆንም፣ አልፎ አልፎ ‹‹እገሌን አባርሬያለሁ›› የሚል መግለጫ ከመስጠት በስተቀር በግልጽ ሙስና ስለመፈጸማቸው በሚታወቁ ባለሥልጣናት ላይ ዕርምጃ መውሰድ አልቻለም፡፡

‹‹ባለሥልጣናቱ ከመንግሥት ጋር እስከተስማሙ ድረስ ሙስና ቢፈጽሙም ሃይ የሚላቸው ኃይልም ተቋምም የለም፤›› በማለት የፖለቲካ ልዩነት ያላቸው ሰዎች ብቻ ሙስና ፈጽመዋል ተብለው ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ይናገራሉ፡፡

‹‹በሙስና የተዘፈቀ ኃይል ራሱን መልሶ መቅጣት የሚችል አይመስለኝም፤ በሙስና የተዘፈቀውን እዋጋለሁ ቢል የሚጀምረው ከራሱ ነው፤›› በማለት መንግሥት በሙሰኞች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ የተቸገረበትን ምክንያት አቶ ገብሩ ይጠቅሳሉ፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት የመንግሥት ቀኝ እጆችና የሥልጣን መሠረት የሆኑትን እነዚህን ባለሥልጣናት መቅጣት በሥልጣኑ ላይ ስጋት ስለሚፈጥርበት ሊሆን ይችላል መንግሥት ዕርምጃ ከመውሰድ የሚቆጠበው፡፡ ‹‹ነፃነት በሌለበት፣ ዲሞክራሲያዊ መብቶች ባልተጠበቁበት፣ የሕግ የበላይነት በሌለበት ሁኔታ ሙስናን መቅረፍ ያስቸግራል፤›› በማለት ሙስና ከፖለቲካ ጋር ተያያዥነት ያለው ጉዳይ መሆኑን አቶ ገብሩ ይገልጻሉ፡፡

አቶ ስየ አብርሃ በሙስና ተጠርጥረው ከታሰሩ በኋላ ሙስና የፖለቲካ ጉዳይ ተደርጐ መወሰዱን የሚናገሩት አቶ ገብሩ፣ በአቶ ስየ ላይ የተወሰደው ዕርምጃ ‹‹ሙስናን እየፈጸምክ ሥርዓቱን ካልተቀናቀንክ እንደፈለግክ መኖር ትችላለህ፡፡ የእኔን ሥርዓት ከተቃወምክ ግን ሙስና እንኳን ባትፈጽም በሙስና ከስሼ አሳስርሃለሁ፤›› የሚል መልዕክት ያዘለ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

በእርሳቸው እምነት የስየ ‹‹ሕግ›› ተብሎ በአንዳንዶች የሚጠራው ሕግ በችኮላ በፓርላማ ፀድቆ ለፖለቲካ መሣርያነት መዋል ከጀመረ በኋላ፣ ሙስና የመፈክር ጉዳይ ሆኖ ቀርቷል፡፡ ሙሰኞችም የሚበረታቱበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

በአንዳንድ አገሮች ፀረ ሙስና ተቋም የሚቋቋመው ሙስናን ለመዋጋት ቁርጠኝነት አሳይተዋል የሚል እሳቤን ለመፍጠር እንጂ ሙስናን ለመታገል ታስቦ አለመሆኑን የሚናገሩት አቶ ገብሩ፣ ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ከልቡ ሙስናን ለመዋጋት ከፈለገ ሙስናን ለመታገል የሚያስችሉ መብቶችን ሊያከብር እንደሚገባ ያስገነዝባሉ፡፡ ከመብትና ከነፃነት ጋር በተያያዘ በአገሪቱ ያለውን ችግር ሲገልጹም የአንዳንድ አገሮች ሕዝቦች ‹‹ባለሥልጣናቱ የአገሪቱን ሀብት እየመዘበሩ ነው፤›› በማለት፣ ሰላማዊ ሠልፍ ወጥተው ዕርምጃ እንዲወስድባቸው የሚጠይቁ መሆኑን ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ሰላማዊ ሠልፍ መውጣት መንግሥትን ለማፍረስ እንደመሻት ተደርጐ ስለሚታሰብ፣ ይህንን መብት ተጠቅሞ ለውጥ ለማምጣት አለመቻሉን ይገልጻሉ፡፡

ከሕወሓት ክፍፍል በኋላ ሙስናን እንዋጋ የሚለው መፈክር ጐልቶ መውጣቱን የሚያስታውሱት አቶ ገብሩ፣ ሕዝቡ የመንግሥትን ፕሮፓጋንዳ አምኖ ሥር ነቀል ዕርምጃ ይወሰዳል ብሎ የሰነቀው ተስፋ ከተስፋ በላይ አለመዝለሉን፣ እንዲያውም በከፋ መልኩ ሙስና አእየተስፋፋ መምጣቱን ይናገራሉ፡፡

‹‹አንድ ሙስና የፈጸመ ሰው የመንግሥት ደጋፊ ነኝ እስካለ ድረስ ከአንድ መሥርያ ቤት ወደ ሌላ መሥርያ ቤት እንዲዛወር ይደረጋል፡፡ ወይም ከማዕከላዊ ኮሚቴ ገለል ብሎ ይቆይና ከጊዜ በኋላ ደግሞ ሌላ ሥልጣን ይሰጠዋል፡፡ በኢሕአዴግ ጊዜ ሙስኛ ሳይሆን ሙስናን የሚያጋልጠው ነው የሚፈራው፤›› በማለት በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በአዲስ አበባና በሌሎችም ክልሎች በሙስና ተባርረዋል የተባሉ ሰዎች ሹመት አግኝተው ሲንቀሳቀሱ እንደሚታዩ ይናገራሉ፡፡

የአንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳም በአቶ ገብሩ ሐሳብ ይስማማሉ፡፡ እርሳቸው ፕሬዚዳንት በነበሩበት በ1989 ዓ.ም. የቀድሞ ድርጅታቸው ኦህዴድ ባደረገው ግምገማ በርካታ የድርጅቱ አባላት፣ ካድሬዎችና የፓርላማ ተመራጮች በሕገወጥ መንገድ ሀብት ማካበታቸው ስለታወቀ ‹‹ከየት አመጣችሁት?›› ተብለው ሲጠየቁ ምንም መልስ መስጠት አለመቻላቸውን የስታወሱት ዶ/ር ነጋሶ፣ ግምገማውን ተከትሎ በሙስና ተዘፍቀው የተገኙ ከአሥር ሺሕ በላይ ካድሬዎች እንዲባረሩና የተወሰኑትም እንዲታሰሩ ቢወሰንም፣ ከአራት ዓመት በኋላ በ1993 ዓ.ም. እነዚያ የተባረሩና የታሰሩ ሰዎች ተፈትተው ወደ ድርጅቱ እንዲመለሱ መደረጉን ይናገራሉ፡፡

ሰኔ 15 ቀን 1993 ዓ.ም. ሥልጣን ከመልቀቃቸው በፊት በነበሩት ቀናት በተካሄዱ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባዎች ላይ በሙስና በተገኘ ገንዘብ ቪላዎችን እንደሠሩ የሚወራባቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት ጉዳይ እንዲታይ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱንም ዶ/ር ነጋሶ ያስታውሳሉ፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ በሙስና ላይ ቁርጠኛ አቋም የሌለው መሆኑንም በግንቦት 1993 የኦህዴድ ስብሰባ ተገንዝበዋል፡፡ በዚሁ የኦህዴድ ስብሰባ ላይ ስብሰባውን ሲመሩት ከነበሩት ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር በሻይ የዕረፍት ሰዓት ላይ በተገናኙበት ወቅት በሙስና የተዘፈቁ ባለሥልጣናት ጉዳይ እንዲታይ ላቀረቡላቸው ጥያቄ፣ ‹‹እያንዳንዱን እየተከታተልን መረጃ የምናገኝበት ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ ይህንን [የሙስና] ጉዳይ በሰዎች ላይ ማንሳት ይከብዳል ለውጥ ማምጣት የሚቻለው ኅብረተሰቡን በማስተማር ነው፤›› የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ያስታውሳሉ፡፡ አያይዘውም ‹‹የእኔ አቋም ዕርምጃዎችን ካልወሰድን ሌላውን ኅብረተሰብ የማስተማር ሞራል ሊኖረን አይችልም የሚል ነበር፡፡ ይህ ባለመሆኑም ሙስና ተንሰራፍቷል፤›› በማለት በሙስና ወንጀል የተዘፈቁ ሰዎች ላይ ዕርምጃ አለመወሰዱ ምን ያህል በአገሪቱ ላይ ችግር እንደፈጠረ ዶ/ር ነጋሶ ያስረዳሉ፡፡

የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የሥነ ምግባር፣ ትምህርትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አሰፋ በበኩላቸው፣ ሙስና በባህሪው ሚስጥራዊነቱ ተጠብቆ ሥልጣኑና ሀብቱ ባላቸው ታስቦበት የሚፈጸም ድርጊት በመሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት ሙስና ያለበትን ደረጃ በተጨባጭ ለማወቅ እንደሚያስቸግር ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ብዙውን ጊዜ በሙስና ላይ ጥናት የሚያደርጉ ድርጅቶች በሰዎች አስተሳሰብ ላይ ተመሥርተው መረጃ እንደሚሰበስቡ የሚናገሩት አቶ ብርሃኑ፣ የሰዎች አስተሳሰብ ቦታ የለውም ባይባልም የእነዚህን ሰዎች አስተሳሰብ ተመርኩዞ በእርግጠኝነት ‹‹ሙስና ጨምሯል ወይም ቀንሷል›› ማለት እንደሚከብድ ያስረዳሉ፡፡

እርሳቸው እንደሚሉት ፀረ ሙስና ኮሚሸን ከተቋቋመ በኋላ ሙስናን በሚመለከት በአገሪቱ የታየውን ለውጥ በጥናት ማወቅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ በዓለም ባንክ ድጋፍ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኪሊማንጃሮ ኢንተርናሽናል ከተባለ ድርጅት ጋር በመሆን ጥናት እያካሄደ ነው፡፡ ‹‹[አጥኚዎቹ] የሰበሰቡትን መረጃ የመተንተን ሥራ ውስጥ ነው ያሉት፡፡ ጥናቱ ሙስና ጨምሯል ወይስ ቀንሷል የሚለውን የኅብረተሰቡ አስተሳሰብ ሊያሳየን ይችላል፤›› ይላሉ፡፡

የአገሪቱ ኢኮኖሚ በሚንቀሳቀስበትና ብዙ ገንዘብ ወጥቶ በርካታ የልማት ሥራዎች በሚከናወኑበት ጊዜ የሙስና አጋጣሚዎች እየሰፉ ሊሄዱ እንደሚችሉ የሚጠበቅ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ብርሃኑ፣ ችግሩን ለመቅረፍ ጥናቱን አይቶ መወሰን እንደሚጠይቅ ይናገራሉ፡፡

አቶ ብርሃኑ እንደሚሉት ኮሚሽኑ በተቋቋመ በአሥር ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙስናን በመከላከልና ሕግ በማስከበር ረገድ መልካም ውጤቶችን ያስመዘገበ ቢሆንም፣ ኅብረተሰቡ በሚጠብቀውና ኮሚሽኑ በሚያስመዘግበው ውጤት መካከል ክፍተት ስላለ ጠንክሮ መሥራት ይጠበቅበታል፡፡

ፀረ ሙስና ኮሚሽን በሙስና ወንጀል የተዘፈቁ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ከሶ ወደ ፍርድ የማቅረብ አቅም የለውም ተብሎ በአንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች የሚሰነዘሩት ትችቶችም መሠረተ ቢስ ውንጀላ መሆናቸውን አቶ ብርሃኑ ይገልጻሉ፡፡

‹‹አንድ ሰው ባለሥልጣን ስለሆነ የግድ መክሰስ ያለብን አይመስለኝም፡፡ ጉዳዩ የሚያስጠይቀው ከሆነ ማንም ሰው ይጠየቃል፡፡ ከዚህ ቀደምም ሆነ በቅርቡ የጠየቅናቸው ባለሥልጣናት አሉ፡፡ ባለሥልጣን ለመክሰስ ብቻ ብለን ግን የምንሠራው ሥራ የለም፤›› በማለት ኮሚሽኑ ሰዎችን የሚከሰው በሙስና ወንጀል ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ ሲያስብና መረጃ ሲኖረው ብቻ መሆኑን ያብራራሉ፡፡

Continue reading …

 ለማንበብ እዚህ ይጫኑ   

 

Continue reading …

አንድ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤት የሚማር ተማሪ ለአባቱ ‹አባዬ፣ በት/ቤታችን ነገ የሚቀርበውን የምትሃት ትርዒት ለማየት ሦስት ብር ክፈሉ ተብለናልና ስጠኝ› ይለዋል፡፡ አባትም ‹አዬ ልጅነት፣ እኔ አባትህ በአምስት መቶ ብር ደመወዝ ይህን ሁሉ ቤተሰብ ወር እስከ ወር ቀጥ አድርጌ መያዜ ራሱ ምትሃት አይደለም? ታዲያን እዚሁ እቤትህ እኔ አባትህ ምትሃት እያሳየሁህ የምን ገንዘብ ከፍሎ ማየት ነው?› ይለውና ለምትሃት ቀርቶ ለዳቦም የሚሆን ሣንቲም ለማግኘት መቸገሩን ያረዳዋል ፤ ማስረዳት ጥንት ያኔ በደጉ ዘመን በመቅረቱ፡፡ ዛሬ ዛሬ ማርዳት እንጂ ማስረዳት የለም፡፡

የሀገራችን ኑሮ ጦፏል፡፡ ከቃላት የመግለጽ አቅም በላይ ተቃጥሏል፡፡ በዚያም ምክንያት ብዙው ዜጋ የሚያደርው ጠፍቶት እንዲሁ ፈዝዟል፡፡ ይህን ያህል ምን እንዳነሆለለን አይገባኝም፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ በምትሃት የሚተዳደረው ሰው እጅግ ብዙ ነው፡፡ የደመወዙን መጠን የምናውቀው ሰው – ከሦስት ቀናት ያልበለጠ ሊያኖረው እንደማይችል የምንረዳው ብዙ ደመወዝተኛ – በማይገባን ምሥጢር በየቀኑ መጠጥ አፉ ላይ ለግጦ እናየዋለን፤ የ120 ብር ኪሎ ሥጋ ከባልንጀሮቹ ጋር ሲቀረጥፍም  እናስተውላለን፡፡ የተሻለ ደመወዝ አለን የምንል ደግሞ ከቤታችን ሥጋና ቅቤ ከጠፉ ዓመታት ተቆጠሩ – በተለይ ከ97 ምርጫ በኋላ፡፡ ውጪ ማምሸትም ከብርቅነት ተቆጠረ – የቤት ሽሮ ሳይሟላ እንዴት ተደርጎ ውጪ ይመሻል? የወጉን ለማድረስና የሃሳብን ትርምስምስ ከወዳጅና ጓደኛ ጋር ተካፍሎ አእምሮን ፈታ ለማድረግ ከውስኪና ቢራ የሚወርዱ የወራጅ ቀጣና አባላት በየሀበሻ አረቂ ቤቱ ሲያውካኩ ያመሻሉ – እናመሻለን፤ ሌላ ምን ምርጫ አለን? አለበለዚያ በሃሳብና ጭንቀት ድርና ማግ ተተብትበን መውጫ በማጣት ልናብድ እንችላለን፡፡ የዚህ ዓይነቱ የተመሰቃቀለ ሕይወት መነሻው ምሥጢር ሆኖብናል፡፡

አዲስ አበባ ውስጥ ሕይወት ፈርጀ ብዙ ናት – እንደማንኛውም ከተማ ሁሉ፡፡ የኑሮ ልዩነቱ ግን ከየትኛውም ሀገር የሚብስ እንጂ የሚስተካከል እንኳን አይደለም፡፡ አንድ ሰው በአንድ ቀን አዳር እንዴት አንቱ የተባለ ቱጃር ወይም ሙልጭ የወጣ ድሃ እንደሚሆን ዕንቆቅልሽ ነው – የማይገባ፡፡ ከተማዋ ውላ የምታድረው በፈጣሪ ጥበብና ጥበቃ እንጂ አስተዳዳሪ ያላት አትመስልም፡፡ ጉልበተኛ ከሆንክ ሁሉም ነገር አለህ፡፡ ፈሪሃ እግዚአብሔርና ጤናማ ኅሊና ካለህ ከእግዚአብሔርና ከጤናማ ኅሊና በስተቀር ምንም የለህም፡፡ እነዚህ ደግሞ በንጹሕ ኅሊና እንድትደሰት ያደርጉህ ይሆናል እንጂ ለቁሣዊ ሕይወትህ ደንታ ያላቸው አይመስሉም፡፡ እናም ነፍስህ በንጽሕናዋ ልትደሰት ብትችልም በተወሰነ መልኩ ሥጋህ ሊከፋብህና በፈተናም ልትከበብ ትችላለህ፡፡ ያኔ ፈጣሪና ንጹሕ ኅሊና ሊከዱህ ዳር ዳር ይላሉ፡፡ በሠፊው መንገድ ልታመራ ከቆረጥህ ሰው የመሆንህን አንጡራ ሀብት ትቀማና የሁሉም ቁሣዊ ሀብቶች ባለቤት የምትሆንበትን ዘዴና ብልኃት ከቢጤዎችህ ትማራለህ፡፡ ከዚያ አዲስ አበባን በቀንና በሌሊት በሽንጣም ዘመናዊ አውቶሞቢል እየተሸከረከርህ መምነሽነሽ ነው፡፡ ነገ ለራሱ ይጨነቅበታል – አንተ ለምንም መጨነቅ ሣይኖርብህ በሚሊዮኖች ወገኖችህ ደምና ወዝ መደሰት ብቻ ነው የሚጠበቅብህ፡፡ ነጋዴም ሁን፣ ፖለቲከኛም ሁን፤ ተቀጣሪ ሠራተኛም ሁን፣ ዋናው ኀሊናህን እቤትህ አስቀምጠህ ሆድህ ያዘዘህን መፈጸም ነው፡፡ ለዚያ ደግሞ እንደግብኣት ዘውገኝነትና ጠባብ ብሔርተኝነት ዋስ ጠበቃ እንደሚሆኑህ ዐውቀህ እስከጥግ ልትጠቀምባቸው ይገባሃል፡፡ በሌላ በኩል ሰፋ ያለ የኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ እንዳይኖርህ መጠንቀቅ አለብህ – ይሄ ዓይነቱ አስተሳሰብ ለዕድገትህ ፀር ነው፡፡ በሀብት ሽቅብ ለመስፈንጠር የኢትዮጵያን ስም በፍቅርና በቅንነት ካነሳህ ወዮልህ! ‹በማን ላይ ቆመሽ ወያኔን ታሚያለሽ› የሚለውን አዲስ ተረትና ምሣሌ ማጤን ይጠበቅብሃል፡፡ የምትከብረው በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ወጪና ኪሣራ መሆኑን ካልተረዳህ ሁሉንም የምትቀማበት ዘመን እንደሚመጣ ዕወቅ – በኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ የምትከብረው ከአስብቶ አራጆች ጋር ተስማምተህና ተሞዳሙደህ እስከቀጠልህ እንጂ ጉዳይህ ሲሞላ ሸርተት የምትል ከሆንክ ተዘጋጅተው ከሚጠብቁህ የማጥቂያ ካርዶች ባንደኛው ዘብጥያ ትወርዳለህ፤ የቁሣዊ ዕድገትህ ምንጭ የወያኔ ችሮታ የታከለበት ያንተው ኅሊናቢስነት  እንጂ የብቃት ደረጃህ ከፍተኛነት እንዳልሆነ ካልተረዳህ ተጎጂ ነህ፡፡ በብፅዕና መክበር የለም – በዚህ ዘመን የሚከበረው ራስን ከድቶ ኅሊናን ለባዕድ አስተሳሰብ ካስገዙ ብቻ ነው፡፡ ይህ ውርደታዊ ዕድገት ጥንትም ነበር፤ አሁንም አለ፡፡

ትናንት አለቤሾው ላይ አዘጋጁ አለባቸው ተካ በፕሮግራም መግቢያነት ይጠቀምባት የነበረችውን  ኩሽና እምትመስል ጢስ የጠገበች ደሳሳ ጎጆ ውስጥ በኪራይ ሲኖር የነበረ ሰው ዛሬ የመዋኛ ገንዳና ጃኩዚን የተባሉ የቅንጦተኛ ኑሮ መገለጫዎች የተሟሉለት የተንጣለለ አውሮፓዊ ግቢ ውስጥ አኗኗሩን እንኳን በቅጡ ሳያውቅበት  ትናንትናና ከትናንት በስቲያ ድሃ ከነበረ ቤተሰቡ ጋር ሲኖር ብታይ መቅናት የለብህም፡፡ አንተም እርሱን የመሆንና ያለመሆን መብት ስላለህ በምንም ነገር ልትቀና አይገባህም፡፡ ኑሮ በአዲስ አበባ ዕንቆቅልሽ መሆኑን ተገንዝበህ ነፍስህን አውለህ ለማሳደር መታገል ወይም ‹ጅብ ከሚበልህ በልተኽው ተቀደስ › በሚለው የሆድ አደር መመርያ መሠረት የነበረህን ዓላማ – ከነበረህ-  ቀይረህ ወደሀብቱ ተራራ መጓዝ ነው፡፡ አትጠራጠር – ይሳካልሃል፡፡ ግን ጸሎትህንና እምነትህን ካልለወጥህ አይሆንልህም፡፡ በነጻ እሚገኝ ነገር የለም፡፡…

ጸሎትህ ባጭሩ ይህን ይምሰል፡- ‹ አቤቱ ወያኔ ሆይ በጠበንጃ ጫፍ የምትኖር ደደቢታዊ መንፈስህ ትባርከኝ፡፡ ስምህ በዲያቢሎስ መንግሥት ገናና እንደሆነ ሁሉ በእኔም ቤት እንደዚያው እንዲሆን ፈቃድህ ይሁንልኝ፡፡ ከሀብት ማግኛ ጠላቶቼ ከመድረክና ቅንጅት ብሔራዊ መናፍስት እንዲሁም እነሱ ከሚያቀነቅኑት የኢትዮጵያዊነት አባዜ  በኪነ ልደትህ ወሞሼህ ጠብቀኝ፡፡  ዐይኔ ያየውን መኪና ሳልነዳ፣ የልጆቼን እናት አሮጊት ሚስቴን ፈትቼ ቀልቤ ያረፈባትን ውብ ኮረዳ ሳላገባ፣ ልቤ በተመኘው ምግብና መጠጥ ሁሉ ሳልደሰት፣ ለትውልድ የሚተርፍ ገንዘብ በባንክ ሳላከማች… በጅምር እንዳልሰናከል የዐድዋና የአክሱም ወያኔያዊ አበጋሮች ተለምነውኝ ጸሎቴ በወያኔ/ኢሕአዴግ መንበረ ሣጥናኤል ውኩፈ ለይኩን ይሁንልኝ፡፡ አሜን፡፡ › ጸሎትህ አጠር ይበል – ሲንዛዛ ደግ አይደለም – ያስጠረጥርሃል፤ ያስመነጥርሃልም፡፡

አዲስ አበባ ላይ ኑሮ በዘመናዊ የምፀት አገላለጽ ‹አሸወይና› እንደሆነች አየን፡፡ የኑሮ ዕንቆቅልሹ ከአእምሮ በላይ እንደሆነም በጣም ባጭሩ ተመለከትን፡፡ የዛሬ ሕይወቱን ለነገ ለማሳደር አቅሉን ስቶ የሚራወጥባት አዲስ አበባ በዚያው ልክ ሳይሠራና ሳይለፋ ሕይወት ቀኝ በቀኝ የሆነችለት ዘራፊና ሌባም ብዙ ነው፡፡ ቀን ቀን በከተማዋ የሚርመሰመሱትን መኪኖችና ካለአንዳች ሥራ በሥራ ሰዓቶች በየአደባባዩና በየሥፍራው የሚንቀሳቀሰውን የሰው ብዛት ስታዩ ‹ይህ ሕዝብ ሥራ የሚሠራው መቼ ነው? ሌሊት ሌሊት ይሆን እንዴ?› ብላችሁ ልትጨነቁና ይህ ሁሉ ዜጋ ሥራ የሌለው ይሆን ይሆናል ብላችሁ የምትገምቱ ከሆነ ደግሞ ‹ታዲያ ማንስ ነው ሠርቶ የሚያኖረው?›  ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ አስጨናቂ ሀገራዊ ምስል ተደቅኖብናል፡፡ እንዴት ይወገዳል? ወደፊት የምናየው ይሆናል፡፡ ነገሩ ግን የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር የኑሮ ውድነቱ ብቻ አንድ ቀን የሚፈነዳና ሀገሪቱን ለከፋ ምስቅልቅል የሚዳርግ ስለመሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱ ከቀን ቀን እየናረ ባለበት ሁኔታ ገንዘብ የሚያጋብሱት ዜጎች ደግሞ ከአጠቃላዩ ሕዝብ ሲነጻጸሩ እጅግ ኢምንት የመሆናቸው ነገር ተደማምሮ ቀውሱን እንደሚያፋጥኑት የታመነ ነው፡፡ የሚገርም ወቅታዊ ሁኔታ!!

የመኪናውን ነገር ስናነሳ መርሳት የሌለብን ነገር አለ፡፡ በቻይና ዋና ከተማ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ መኪኖች ሲርመሰመሱ በአዲስ አበባ ከሁለት መቶ ሺህ የሚያንሱ እንደሆነ እንሰማለን፡፡ ያበዛቸው ታዲያ ምኑ ነው? ብለን ስንጠይቅ መልሱ የመኪና መንገዱ ጥበት እንደሆነ እንረዳለን፡፡ አንድ ሺህ ለሚደርሱ መኪኖች የተሠሩ መንገዶች ለዚህ ከሌሎች ሀገሮች ጋር ሲወዳደር ኢምንት ለሆነ የመኪና ቁጥር ሊበቁ አልቻሉም፡፡ በዳዴ በምትሄድ ሀገር መቶ ሺና ሁለት መቶ ሺ መኪኖች ብዙ ናቸው፡፡ አሁን አሁን ሰውና መኪና እየተጋፋ መሄድ ጀምሯል፡፡ ያደጉ አገሮች አራትና አምስት ንብርብር መንጎዶች ሲሠሩና ዕድገታቸውን ጠብቀው ሲተሙ ከአፍ እስከ አፍንጫቸው አርቀው የማያስቡት የኛ መንግሥታት እንደኤሊ በሚጎተት የዕድገት ትልማቸው ሰውና መኪናን የሚለይ መንገድ ሊሠሩ አልቻሉም፤ ሠራን ቢሉም የተሠራውና የሚሠራው ከዕድገቱ ጋር ሊመጣጠን አልቻለም – በየቀኑ በብዙ መቶዎች ምናልባትም በሺዎች ለሚገባ መኪና የሚሠራው መንገድ ግን በተለይ አሁን አሁን የተቦረቦረን አስፋልት ከመለጠፍና የመንገድ ደሤቶችን ከማስዋብ የዘለለ አይደለም፡፡ በዚሁ ያልተመጣጠነ ሙከራቸው ሲኮፈሱና ሲመጻደቁ ማየት ደግሞ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ሠርቶ ችግርን ካስወገዱ በኋላ መኩራራት የተገባ ነበር፡፡ ግን ለአፍዝ አደንግዝ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲባል በሚዲያ ጆሮን እየደጋገሙ መጠለዝ አግባብ አይደለም፡፡ አሥራ አምስት ደቂቃ ለማይፈጅ መንገድ ከአንድ ሰዓት በላይ እየፈጀን ሥራ የሚረፍድብንና ከአለቆቻችን የቃል ግሣጼና የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የሚደርስብን ዜጎች ይህ የመንገዶች መስፋፋት ዜና ለኛ ቀልድ ነው፡፡ አልተሠራም ማለት ግን አይደለም – ችግሩን ሊቀርፍ በሚችል ሁኔታ አልተሠራም ነው የምንለው፡፡ በየቦታው ማነቆ ነው፡፡ ማስተንፈሻዎች በበቂ አልተሠሩም፡፡ ከአሁን በኋላም ወደላይና ወደታች ካልሆነ በስተቀር የጎንዮሽ የመንገድ ሥራ አያዛልቅም፤ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናልና፡፡ ትርፉ ቤት ማፍረስ ብቻ ነው፡፡ እስከመቼስ እያፈረሱ መቀጠል ይቻላል? ብሎ ብሎ ሁሉም እኮ ሊፈርስ ነው፡፡

የመንገዱ ጉዳይ እዬዬም ሲዳላ ዓይነት ነው፡፡ አሁን ማንቁርታችንን ይዞን ያለው የኑሮ ውድነቱ ነው፡፡ በነጋሪት ጋዜጣ ወይም በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ በግልጽ ባልታወጀ ጦርነት እያለቅን ነን፡፡ እየኖሩ ያሉት ጥቂቶች ናቸው፡፡ ብዙዎቻችን ሞትን በሚያስመኝ ሁኔታ በኑሮው እያለቀስን እንገኛለን፡፡ ብዙ የምግብ ዓይነቶች ከመወደዳቸው የተነሣ ከብዙዎቻችን የቀድሞ ደህና ኗሪዎች የምግብ ዝርዝር ተሠርዘዋል፡፡ ለምሣሌ ቅቤና ሥጋ ጥርዥ ብርዥ ሲሉ ቆይተው ለይቶላቸው ከኔ ቤት ከተሰናበቱ ሦስት ወራት ተቆጠሩ – ብርቱካንንም፣ ወተትንም፣ ሙዝንና ሌሎቹንም ጠቃሚ የምግብ ይዘቶች አስከትለው፡፡ ይህ የኔ ችግር የቅንጦት ነው፡፡ በሌሎች ቤቶች ደግሞ ኪሎው ከአሥራ አምስት ብር በላይ የሚሸጠው ሽምብራ ጠፍቶ ለከፋ ርሀብ የተጋለጡ እንዳሉ ዐውቃለሁ፡፡ ርሀብ ደግሞ ጊዜ አይሰጥም፡፡ መሪያችን በሀገራችን ርሀብ የለም ይበሉ እንጂ ሁላችንም ርሀብተኞች ነን፡፡ ርሀብ ደግሞ ፍቺው እንደዬሀገሩ ይለያያል፡፡ ነፍስ ውሎ ስላደረ ብቻ አንድ ሰው አልተራበም አይባልም፡፡ እኔ ራሴ የርሀብ ተጠቂ መሆኔን ማስረዳት እችላለሁ፡፡ አንድ በሠለጠነው ዓለም የሚገኝ የማይራብ ዜጋ በቀን የሚያገኘውን የምግብ ራሽን አገኛለሁ ወይ? ብዬ ራሴን ስጠይቅ የማገኘው መልስ ‹ተሼ፣ ለምን ትቀልዳለህ? የምን መቀናጣት ነው? በብረት የከበረ የጥቁር ጤፍ እንጀራ ከዶኬ ወጥህ ጋር ካገኘህ የምን ፕሪሞ ሴኮንዶና ቴርዞ፣ የምን ሥጋ፣ወተት፣ዕንቁላል፣ዓሣ፣ፓስታሹታ፣ቪልኮተሌት፣ስካሎፕ፣አኜሎዲቢቴሎ፣ፓይ፣ቤከን፣ቋሊማ፣ ስቴክ፣ ሙዝ፣ቴላቴሊ፣ሞርታዴላ፣ላዛኛ፣ሩዝ፣ብርቱካን፣ማንጎ፣ፓፓያ፣ሙዝ፣ፖም፣ለውዝ፣ዙኪኒ፣ሾርባ፣…(የስንቱን ወስፋት አላውሼው ይሆን – ይቅርታ፤ ብቻ የምግብ ሰዓት አይሁን) … ጌታው ተው እንጂ…› የሚል ነው፡፡ አዎ፣ ከዚህ አንጻር ከተመለከትነው የርሀብተኛውን ቁጥር፣ ቁጥር አይገልጸውም፡፡ 99 በመቶ የምንሆነው ዜጎች የኗሪ አኗኗሪ ስለመሆናችን የሚነገርልን እንግዲህ ከዚህ መሠረታዊ ጭብጥ በመነሳት ነው፡፡ እናስ የኔ ርሀብተኝነት ተገለጠላችሁ ይሆን አሁን? እንጂ መኖር ከተባለማ ዐይናቸው ሳያይ ዕጃቸው የገባላቸውን የገዳም አካባቢ ቅጠል እየሸመጠጡ በቀን አንዴ የሚቀምሱት የበቁ አባቶችስ ይኖሩ የለምን? የነሱ በምርጫ – የኛ መንግሥታችንና መንግሥታዊ ዕጣችን በጣሉብን ግዴታ መሆኑ ነው ልዩነቱ፡፡ እናም በአሸር ባሸር ምግብ ሆድን ቆዝሮ ዐይጥ የዋጠ እባብ መስሎ መንቀሳቀስ በቅጡ መኖርን እንደማያመለክት መገንዘብ ያሻል፡፡ ለነገሩ ይሄም ከጠፋ ሰነባበትን፡፡ የአሁኑ ብሶ ቁጭ አለ፡፡

የኑሮ ውድነት ከተነሣ ዘንድ የሚከተሉትን የግንባታ ዕቃዎች የወቅቱን ዋጋ ከአሥር ዓመት በፊት ከነበራቸው ዋጋ ጋር እያነጻጸርኩ ልግለጽላችሁ፤ በዚያውም በአሁኑ ወቅት የደረስንበትን የብር የመግዛት አቅም ግሽበትና ቤት የሚሠራው ማን ሊሆን እንደሚችል ትረዳላችሁ፡፡ በልተውት አንጀት ጠብ የማይል አንድ ተራ የፍስግ ምሣ በአማካይ ብር 35 በሆነበት ዘመን፣ የተሸቀበ አንድ ኪሎ ጥብስ ወይ ጥሬ ሥጋ በአማካይ 100 ብር በሆነበት ዘመን፣ ጭብጥ ባቄላ ገዝቶ አፍን ለመሻር ከበቆልት አዟሪዎች ከአምስት ብር በላይ መክፈል በሚያስፈልግበት ዘመን፣ ሻይና ቡና ጠጥተህ በደጉ ዘመን ለቁርጥና ለውስኪ ከምታወጣው ገንዘብ የበለጠ በምትጠየቅበት ወቅት፣ ሥጋ መግዛት ይቅርና በሉካንዳ በር ካለፍክ ሥጋን ለማየት ገንዘብ የምትከፍልበት ጠማማ ዘመን በግምባር እየመጣ ባለበት አስቸጋሪ ወቅት፣… ላይ እንገኛለን፡፡ ይህን ጉድ ዘመን ለልጆቻችን እናወርሳለን ወይንስ የተሻለ አማራጭ ይኖረናል? እናስብበት፡፡

ተ.ቁ

የዕቃው ስም

መለኪያ

የአሁን ዋጋ(በችርቻሮ)

በ90ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ

1

ስሚንቶ

ኩንታል

350 ብር

50 ብር

2

አሸዋ

ባለ16ሜ.ኩ

6000 ብር

1500 ብር

3

ጠጠር

  ››

5600 ብር

1400 ብር

4

ሽቦ

በኪሎ

30 ብር

30 ብር

5

ባለ8 ፌሮ

ቤርጋ

123 ብር

18 ብር

6

ባለ10 ››

   ››

195 ብር

28 ብር

7

ባለ 12 ››

   ››

275 ብር

31 ብር

8

ባለ14   ››

    ››

368 ብር

41 ብር

9

ባለ16

   ››

478

 50 ብር

10

ምሥማር

ኪሎ

30 ብር

 8 ብር

11

የቆርቆሮ ምሥማር

ኪሎ

45

10 ብር

11

አናፂ/ግምበኛ

የ ቀን ውሎ

ከ120 ብር በላይ

(ለማጁን) ከ15 ብር እስከ 30 ብር

12

ረዳት ወዛደር

  ››

ከ50 ብር በላይ

ከ5 ጀምሮ እስከ 15

13

ቆርቆሮ

32ጌጅ

ከ160ብር በላይ

38ብር

14

የውኃ ቀለም

ጋሎን

140 ብር

50 ብር

ልዩ ማስታወሻ፡- በኢትዮጵያ ከመኖር በለየለት ሲዖል ውስጥ መኖር ይሻላል፡፡ ይህን ወረቀት ጽፌ ከጨረስኩ በኋላ ለመላክ ስሞክር    ኢንተርኔት አይሠራም፤ ደጋግሜ ሞከርኩ አሁንም አይሠራም፡፡ መስመሩ ይገባል ነገር ግን ግንኙነት እንዳይኖር በቅጥረኞች    ድረገፅ   አምካኞቹ የቻይና ‹ዐይጦች› ታግዶኣል፡፡ በዚህች እንኳን እንዳንተነፍስ ያለብንን እመቃ ተመልከቱ፡፡ እንዲህ የሚሆነው ደግሞ       ዛሬ     ብቻ ሣይሆን ሁልጊዜ ነው፡፡ ከሌላው ሁሉ ይሄኛው ድርጊታቸው ይበልጥ ያሣርራል፡፡ ሳይሞቱ መከፈንን የመሰለ መጥፎ ነገር   የለም፡፡ ርሃብን በሆነ ነገር ማስታገስ ይቻል ይሆናል፤ ይህ ዓይነቱ የኅሊና ነጻነት ርሃብ ግን እጅግ ሲበዛ መሪር ነው፡፡ ሞትን       ያስመርጣል፡፡

Continue reading …

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Continue reading …