አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
በአሁኑ ጊዜ አቶ አንዱዓለም አራጌ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ ይገኛል፡፡ ከአስተማማኝ ምንጮች በተገኘ መረጃ መሠረት የካቲት 7 ቀን 2ዐዐ4 ዓም ከቀኑ 8፡ዐዐ ሰዓት ገደማ ለህይወቱ የሚያሰጋ ከባድ ድብደባ ተፈጽሞበታል፡፡ ድብደባውን የፈፀመው አቶ አንዱዓለም በታሰረበት ክፍል ውስጥ የሚገኝ ኢባስ አስፋው የሚባል ፍርደኛ ነው፡፡ ይህ ሰው [...]
የቻይናው ደራጎን (dragon can be translated to “zendo” like St. George killing zendo on his horse with a spear; also the image of zendo suggests that one day he will face the spear of Ethiopian people) (ጭራቅ) ከአፍሪካውያን ጅቦች ጋር አሸሸ ገዳሜ ጭፈረውን እያስነካው ነው፡፡ለዚህ (zendo) ደራጎን አፍሪካ በምንም መልኩ ተስማሚ ሁኔታ አትፈጥርለትም፡፡ታሪክ እንደሚያስረዳው በአንድ [...]
Continue reading …በሽብርተኝነት ስም በእስር ላይ ሚገኘው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አንዱአለም አራጌ ቃሊቲ በሚገኘው እስር ቤት ውስጥ በተቀመጠበት በታህሳስ 7 ቀን 2004ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ለጠያቂዎች ገለፁ፡፡ ፊታቸው ላይም ጠባሳው የሚታይ ሲሆን ጭንቅላታቸው አካባቢም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
አቶ አንዱአለም ለወንድሙ አቶ አብርሀም አራጌ በብስጭት እንደነገሩት በማረሚያ ቤቱ የተቀነባበረና የታቀደ ጥቃት እየተፈፀመባቸው እንደሆነ [...]
PDF- የአፍሪካ ሕብረት ህንጻ ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ሃገሬ
ይቅርታ አድርጉልኝ፡፡ በሰው ስቃይ የመደሰት ባሕርይ አለኝ ብዬ አላምንም፡፡ ግን ሰው ነኝና በኔ ግንዛቤ መሠረት ክፉ ሠሩ የምላቸው ሰዎች ወይም ሕይወት ያላቸው ሌሎች ፍጡራን የሥራቸውን ሲያገኙ ይከፋኛል ብል ራሴን ማሞኘት ይሆንብኛል፡፡ አለበለዚያ ሰው መሆኔ ይቀርና ሌላ ‹ነገር› ነኝ ማለት ነው – በምድር ላይ እንደሰው እዬተንቀሳቀስኩ ሌላ ነገር ልሆን በፍጹም ላይቻለኝ፡፡ ይህ አባባሌ ከግለሰባዊ አንድምታ ወጥቶ [...]
Continue reading …በጋምቤላ ክል በምስጢር የደኅንነት አባል ሆነው ይሠራሉ የተባሉት አቶ ጌታቸው አንኮሬ ባልታወቁ ሰዎች በድንገት መገደላቸውን ተከትሎ ቀደም ሲል በክልሉ የነበረው ውጥረት በከፍተኛ ደረጃ መባባሱ ተገለጸ። የክልሉ ባለሥልጣናትና ካድሬዎችም ስጋት ላይ ወድቀዋል። Read more…
Continue reading …የኢትዮጵያም ሆነ የሌላው ዓለም ሁኔታ ሁሉ ግራ እሚያጋባ ሆነና ምን ብዬ እንደምጀምር ግራ ገባኝ፡፡
ሰዎች በባሕርያችን ተስፋ አስቆራጭ ፍጡራን ነን፡፡ በተለይ የአሁኑ ዘመን አብዛኛዎቹ ሰዎችማ ከምን ጊዜውም በበለጠ የክፉ ክፉ እዬሆንን በመምጣታችን እንዲያውም በአረመኔነቱ ከለየለት መጥፎ አውሬ እየባስን መጥተናል ማለት ይቻላል፡፡ ግን ምን ቢነካን ይሆን? ለምንድን ነው ይህን ያህል ለገንዘብና ለሥልጣን አቅላችንን ስተን ሁሉንም የኅሊናና የሃይማኖት [...]
ፖለቲካ በሁለት መሰረቶች ላይ የቆመ ሲሆን አንዱ ዶግማ ሌላኛው ደሞ ቀኖና ነው። ዶግማው ምን ጊዜም ኣይለወጥም። ዘመን ኣልፎ ዘምን ሲተካ ትውልድ ኣልፎ ትልድ ሲተካ ለሁል ጊዜም ይኖራል። የፖለቲካ ድርጅቶችም የሚሞቱለት ጉዳይ ቢኖር ይሄ ነው። ፍትሕ ዴሞክራሲ ነጻነት ለምሳሌ ዶግማዎች ናቸው።
ኣንድ ድርጅት ሲቆም ቀኖናዎችም ኣሉት። እነዚህ ቀኖናዎች የድርጅቶቻችን የትግል ስልቶች ወይም ሌሎች ግባቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ቀኖና [...]
በሄኖክ አለማየሁ /zehabesha.com
ለአንድ ለሁለት ሳምንታት ጋብ ብሎ ባልተለመደ መልኩ ጠፍቶ የነበረው የሚኒሶታ በረዶ ትናንት ማምሻውን አዲስ ዓመትን እየተቀበልን ባለበት ሰዓት መስታወት የመሰለ በረዶ ጥሎ ከተማዋን ነጭ በነጭ አድርጓታል። ነጭ ደግሞ የሰላም፣ የደስታና የአንድነት መግለጫ ነው። የኦሮሞ ነጻነት ግንባርም በሚኒሶታ ከኢትዮጵያውያን ጋር ባደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ ታሪካዊ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ አዲሱን ዓመት ልክ እንደሚኒሶታ አየር ጠባይ በነጭ እንድንቀበለው [...]
መግቢያ፤
በፍኖተ ነፃነት 2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.14 መግቢያ ላይ እንደገለጽኩት የሶሻሊስቱ (የኮሙኒስቱ) ሥርዓት ተንኮታኩቶ ሲወድቅ ከዚያ በፊት ታይቶ ያልታወቀ ግዙፍ ሙስና መከሰቱን ነበር። በዚህም የተነሳ ሙስናዎች በሁለት ፀንፎች መልክ ተመድበው እንዲታዩ የግድ ብሏል። እነዚህም (1) በመንግሥታዊ አስተዳደር ብልሹነት መስክ የሚሰባሰቡ/የሚገለፁ/የሚከሰቱ ሙስናዎች (administrative corruption) እና፤ (2) የመንግሥቱን የሥልጣን አውታር፤ አስተዳደሩን፤ ህጎቹን፤ ወ.ዘ.ተ. በመጥለፍ/በመማረክ የሚገለፁ የሙስና ጠባዮች (state [...]
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዛሬ እሁድ ታህሳስ 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባዔዉን አጠናቀቀ። ለሚቀጥሉት አመታት ድርጅቱን በሊቀመንበርነት የሚመሩትን እንዲሁም የድርጅቱ የላእላይ ምክር ቤት አባላትን ጠቅላላ ጉባዔዉ የመረጠ ሲሆን ስብሰባዉ በተሳሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና ያመለክታል።
የድርጅቱ ሊቀመንበር ለመሆን ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የአዲስ አበባ የአንድነት ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶር ንጋት አስፋዉ እንዲሁም ከአንድነት ፓርቲ [...]
ጠያቂው- መምህር የኔ ሰው ራስህን መስዋእት ለማድረግ ዝግጅትህን ባጠናቀክበት በዚህች የመጨረሻ ሰአት ቃለ ምልልስ ለምድረግ ስለፈቀድክልኝ ከልብ አመሰግናለሁ።
የኔሰው፤- እኔም አመሰግናለሁ እድሉን ስላገኘሁ።
ጠያቀው፡- የኔሰው በአሁኑ ሰኣት ራስህን መስዋእት ለማደርግ ቆርጠህ ወደዚያው ስታመራ ነው ያገኘሁህ እስቲ ልብህ ምን ይላል?
የኔሰው፦- ይህንን ከባድ ወሳኔ ስወስን ዝም ብዬ አይደለም። አርቄ ያየሁት ነገር ስላለ ነው።ከሁሉም በላይ ለነጻነት እና ለፍትህ ለሚደረገው ህዝባዊ [...]
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
የሕገ-መንግሥት ጥሰቱና ገደብ የለሽ አምባገነንነቱ
እየጨመረና እየባሰበት ነው!!
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሠጠ መግለጫ
በመርህ ደረጃ የምናውቀውና በትምህርት ቤት የተማርነው ሰዎች ከታሪክ ይማራሉ በዚህም ስህተቶች እየታረሙ ይሄዳሉ፣ አይደገሙም የሚል ነው፡፡ ነገር ግን የሕይወት እንቆቅልሽና በተግባር ስናየው ታሪክ፣ የሚያስተምረን፣ ሰዎች ከታሪክ የማይማሩ መሆናቸውን መሆኑ የሚያስገርም ነው፡፡ [...]
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
Continue reading …አንተም እንደ የሱስ
የኔሰው ገብሬ
አንተ ያገሬ ልጅ
እስኪ ልጠይቅህ
የነጻነት ትርጉም
እንደምን አስተዋልህ
በመለሰ ዘመን
ለጥብሥ ያበቃህ
እኔ በሚገባኝ
የሱስ ብቻ ነበር
ባልሰራበት ሐጢት
ራሱን የሰዋ
ያውም ለዓመጹበት
እጅጉን ይገርማል
አንተም መሰዋትህ
በኢትዮጵያዊነት
ሞትማ ይመጣል
ሁሉን አስተካካይ
አንተ ያገሬ ልጅ
እስኪ ልጠይቅህ
የነጻነት ትርጉም
እንደምን አስተዋልህ
በመለሰ ዘመን
ለጥብሥ ያበቃህ
ዋጋ ከፍሎዋል አሉ
ብዙ ኢትዮጵያዊ
[...]
ከሁሉም በፊት በወያኔው ኢሰብኣዊ አገዛዝ ተንገሽግሾ ሰውነቱ ላይ ቤንዚን በማርከፍከፍ ይህችን የደም ምድር ኢትዮጵያ በገዛ ፈቃዱ የተሰናበተውን ወንድማችንና ልጃችንን መምህር የኔሰው ገብሬን የከፈለውን መስዋዕት ፈጣሪ እንደአቤል መስዋዕት ቆጥሮ መንግሥተ ሰማይን ያውርስልን ማለት እፈልጋለሁ፡፡ ካህናት እንዳይታዘቡኝ አንድ ሁለት ቃላትን ልናገር፡፡
‹የኔሰው ራሱን አጠፋ› ብዬ ለማመን ይከብደኛል፤ አልችልምም፡፡ እርግጥ ነው ራሱን አጥፍቷል፡፡ ግን ለምን? ይህ ወጣት አስተሳሰቡን [...]
አጭር መልእክት መጻፍ አሰኘኝ – ደካክሞኝ ልተኛ ስል፡፡ ከበፊትም የነሱና የኛ ታሪኮች መመሳሰል በጣሙን ያስደንቀኝ ነበር፡፡ የነሱና የኛ ችግር ተቀራራቢ እንደሆነ በተለይ ካለፉት ስምንትና ዘጠኝ ወራት ወዲህ እነሱ እየደረሰባቸው በሚገኘው የጭፍጨፋና የግድያ የሰቆቃ ኑሮ መገንዘብ ችያለሁ – የሁለታችንም አሳዳሪ ጌቶች ክፉኛ ጨካኞች ናቸው – ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው፡፡ እነሱ እንደሕዝብ በጣም ጠንካሮች ናቸው፡፡ እኛ ግን የነሱን የብቃት [...]
Continue reading … ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ ጋዜጠኛ ዐብይ ተክለማሪያም፣ ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ፣ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም በክሱ ውስጥ ይገኙበታል
እስረኞች ቶርቸር እንደተፈፀመባቸው ገልጸዋል
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ /አንድነት/ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት አላፊ አቶ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 24 ሰዎች በዛሬው ቀን ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ በዛሬው ዕለት ከሰዓት በኋላ የተሰየመው የፌድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛው ወንጀል ችሎት 8 ተከሳሾች ቀርበው [...]
Continue reading …ሪፖርተር
ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ1993 ዓ.ም. ባካሄደው ጥናት በአገሪቱ ውስጥ ከሚታዩ ዋና ዋና ችግሮች መካከል ሙስና አንዱ መሆኑ ተጠቅሶ ነበር፡፡
ሙስና የአገሪቱ ችግር ነው የሚለው ይህ የኅብረተሰቡ አስተሳሰብ ከአሥር ዓመት በኋላም የተቀየረ አይመስልም፡፡ በ1993 ዓ.ም. የተቋቋመው የፀረ ሙስና ኮሚሽንም ሙስናን በመዋጋት ረገድ ከፍተኛ እምነት ተጥሎበት የነበረ ቢሆንም፣ በአገሪቱ የሚታየው ሙስና በዓይነትና በመጠን [...]
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
Recent Comments