የታሪክ ተጠያቂወች አንሁን፤ ለወቅቱ አገራዊ ጥሪ መነሳት አሁን ነው። ክፍል ስምንት አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ክፍል ስምንት አክሎግ ቢራራ (ዶር)

Dr Aklog Birara

በቁጥር ሰባት የደመደምኩት፤ አገርን ከአስከፊ አደጋ ለመከላከል ከተፈለገ፤ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሰው ርህራሄ ከሌለው፤ ዘርፎ ለዘራፊ ዳራጊ ከሆነ የዘረኛ ስርአት አላቆ ለፍትሃዊ አማራጭ የሚቨጁ አገር አቀፍ ተቋሞችን መገንባት ያስፈልጋል። አለበለዚያ፤ አገራችን ሁልጊዜ ያልተረጋጋ ች ሆና ትቆያለች፤ ህዝቧም በድህነት አለንጋ ሲገረፍ፤ ወጣቱ ሲስደድ ይኖራል። መፍትሄው በእጃችን ነው። ይህን አስፈላጊ ለውጥ ለማድረግ የባህል፤ በመጀመሪያ፤ ያስተሳሰብ፤ የአሰራር፤ የአደረጃጀትና የአመራር ለውጥ መጀመር አለበት (Paradigm shift in thinking, organization and leadership)። ለፍትሃዊ ለውጥ የሚደረግ ጉዞ የማንኛውም አገራዊ የሆነ ተቃዋሚ ግለሰብ፤ የማንኛውም ማህበራዊና የፖለቲካ ድርጂት፤ የማንኛውም ብሄር፤ የማንኛውም ሃይማኖት ተከታይ፤ ወዘተ አላማ መሆን ይኖርበታል። የውጭ ጠላቶች፤ የውስጥ ደጋፊወች ባጠመዱልን “የከፋፍለህ ግዛው ክልል” ወጥመድ ከቆየን አሰቃቂውን የህወሓት/ኢሃዴግ አገዛዝ ለመለወጥ አንችልም። እነ “አቦይ ስብሃት” የሚናገሩት ፕሮፓጋንዳ ይቀጥላል።

ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ